• Call Us
  • +251465512106
ጠ/ሚ ዐቢይ የገበታ ለሀገር ኮይሻ ፕሮጀክት አካል የሆነውን ሐላላ ኬላ ሪዞርት መርቀው ከፈቱ

ጠ/ሚ ዐቢይ የገበታ ለሀገር ኮይሻ ፕሮጀክት አካል የሆነውን ሐላላ ኬላ ሪዞርት መርቀው ከፈቱ

ወላይታ ሶዶ፣ ሚያዝያ 23/2015 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የገበታ ለሀገር ኮይሻ ፕሮጀክት አካል የሆነውን ሐላላ ኬላ ሪዞርት መርቀው ከፈቱ።

በምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባደረጉት ንግግር በጊቤ ሦስት የኃይል ማመንጫ አመካኝነት ከተፈጠረው ሰው ሰራሽ ሃይቅ ዳርቻ የሚገኘው የሀላላ ካብ በ'ገበታ ለሀገር' ኮይሻ ኮሪደር ፕሮጀክት አካል በሆነው ሃላላ ኬላ ሪዞርት ውስጥ ተካቶ የለማ ድንቅ የቱሪስት መስህብ ስፍራ መሆኑን ተናግረዋል።

ሀላላ ኬላ ሪዞርት ከመዝናኛ ስፍራነቱ በተጨማሪ ታሪካዊና ባህላዊ ሙዚየሞችና የምርምር ማዕከላትን ያካተተ መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኘው የዳውሮ ዞን ለአይን የሚማርኩ መልከዓ ምድር፣ ታሪካዊና ባህላዊ መስህቦች ባለቤት ስለመሆኑም አንስተዋል።

ኢትዮጵያውያን ለብዙ ስራዎች አእምሯችሁ እንዲከፈት የህዝብና አካባቢ ሰላም በእጅጉ በሚገኝበት የዳውሮ ዞን…Read More

የፌዴራል ህዝብ ተወካይ ምክር ቤት አባልና የክልል ምክር ቤት ተወካዮች አጆራ ፏፏቴ ጎበኙ።

የፌዴራል ህዝብ ተወካይ ምክር ቤት አባልና የክልል ምክር ቤት ተወካዮች አጆራ ፏፏቴ ጎበኙ።

የፌዴራል ህዝብ ተወካይ ምክር ቤት አባልና የክልል ምክር ቤት ተወካዮች በወላይታ ዞን በቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ በሚገኘው አጆራ ፏፏቴ ጎብኝተዋል።

የፌዴራል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በበኩላቸው አጆራ ፏፏቴ የተለየ የገቢ ምንጭና ለተመልካች ማራኪ እንደሆነ በትኩረት ይሰራል ነው ያሉት።

በጉብኝቱ የፌዴራል ተወካዮች ምክር ቤት አባል ፣የከተማ መሠረተ ልማት ኮሚቴ ኢ/ር አልማዝ አሳሌ ጨምሮ በፌደራልና በክልል የህዝብ ተወካዮች የምክር ቤት አባላት፣የወረዳ አስፈፃሚ አካላት ተሳትፈዋል።

Read More
የወላይታ ዞን ሕዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር መርሃግብር 10ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።

የወላይታ ዞን ሕዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር መርሃግብር 10ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ወላይታ ሶዶ ፣ የካቲት 30/2015 ዓ.ም (ወላይታ ዞን መ/ኮሚዩኒኬሽን ጉ/መምሪያ)

የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ካሰች ኤልያስ ጉባኤ መክፈቻ ሲያደርጉ በዞኑ የተጀመሩ ኦዲት ግኝት ገንዘቦችን የማስመለስ ሥራ ያለበት ደረጃ መገምገሙን ፤ ምክር ቤቶችን የማጠናከር ሥራ መሰራቱ ፤ የተለያዩ በጎ ተግባራት ሥራዎች መከናወናቸዉን፤ ኑሮ ዉድነትን ለመቅረፍ በዋናነት የተያዘዉን የማምረት ሥራ ወጤታማነት ያለበት ደረጃ በዝርዝር መገምገሙን ጠቅሰዉ በምክር ቤቱ የሚደረገው ክትትልና ቁጥጥር ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አንስተዋል።

የዚህ ዙር ምክር ቤት ጉባኤ በሰሜኑ ሀገራችን ክፍል የተጀመረው ጦርነት በሰላም ለመፍታት የተደረገ ስምምነት ወቅት መሆኑ፤ የሶዶ ከተማ ከሌዊ እስኬ ግብርና ኮሌጅ ያለዉ አስፋልት ጥያቄ ምላሽ ያገኘበት ጊዜ የሚደረግ ጉባኤ መሆኑ ልዩ ያደርጋል ብለዋል።

ጉባኤው በሁለት ቀናት ቆይታው የምክር ቤቱ የ2015…Read More

"የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ተልዕኮ የዕለት ጉርስ ከመሸፈን ባሻገር ሀብት በመፍጠር ላይ የተመሠረተና ለቤተሰብ፣ ለማኅበረሰብና ለሀገር የሚበቃ ተልዕኮ ነው" የኢፌዴሪ የሥራና ክሂሎት ሚንስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል

"የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ተልዕኮ የዕለት ጉርስ ከመሸፈን ባሻገር ሀብት በመፍጠር ላይ የተመሠረተና ለቤተሰብ፣ ለማኅበረሰብና ለሀገር የሚበቃ ተልዕኮ ነው" የኢፌዴሪ የሥራና ክሂሎት ሚንስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለ4ኛ ዙር የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች የሚሰጠው ሀገር አቀፍ ስልጠና በወላይታ ሶዶ ከተማ ተጀምሯል።

ወላይታ ሶዶ፣ የካቲት 14/2015 (ወ/ዞ/መ/ኮ/ጉ/መምሪያ) የኢፌዴሪ የሥራና ክሂሎት ሚንስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል በቪርቿል(ዙም ቴክኖሎጂ) ለሠልጣኞች ባስተላለፉት መልዕክታቸው የሠልጣኞች ተልዕኮ የዕለት ጉርስ ለመሸፈን ሳይሆን ሀብት በመፍጠር ላይ የተመሠረተና ለቤተሰብ፣ ለማኅበረሰብና ለሀገር የሚበቃ ተልዕኮ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ወ/ሮ ሙፈሪያት አክለውም አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን መፍጠር ማጠናከርና ማስፋት የወደፊት የሀገሪቱን ዕጣ ፈንታ የሚወስንና ሀገራችን ያለመችውን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማምጣት ሚናው ከፍተኛ ነው ብለው ትኩረት በተሰጣቸው የግብርና፣ የኢንዱስትሪ፣ የቱሪዝም የማዕድን፣ የሰው ኃይል…Read More

በዘንድሮ በግማሽ በጀት ዓመት ለ5 ሺ 549 ዜጎች በከተሞች ተቋማዊና መሠረተ ልማት ፕሮግራም የስራ ዕድል እንደተፈጠረ ተገለጸ ።

የካቲት 13/2015 ዓ/ም

በዘንድሮ በግማሽ በጀት ዓመት ለ5 ሺ 549 ዜጎች በከተሞች ተቋማዊና መሠረተ ልማት ፕሮግራም የስራ ዕድል እንደተፈጠረ ተገለጸ ።

በዛሬው ዕለት በወላይታ ሶዶ ከተማ የደቡብ ክልል የ2015 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የከተሞች ተቋማዊና መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም /UIIDP/ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተካሂዷል ።

በመድረኩ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ይገዙ ባስተላለፉት መልዕክት ስኬታማ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝበ ውሳኔ እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ስራ በተሰራበት ማግስት የተካሄድ መድረክ መሆኑ ለየት ያደርገዋል ብለዋል ።

የከተማና መሠረተ ልማት ሚንስትር በግማሽ ዓመቱ ባደረገው የአፈጻጸም ግምገማ የደቡብ ክልል ከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ቢሮ ሁለተኛ ደረጃ ያገኘ ሲሆን ለዚህ ደረጃ የተጉ አመራሮችና መዋቅሮችን አመስግነዋል ።

በግማሽ ዓመቱ በከተሞች ሁለንተናዊ ፋይዳ ያላቸው በርካታ መሠረተ ልማቶች…Read More

የህዝበ ውሳኔ ድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ በሠላምና በስኬት እንዲጠናቀቅ ላስቻሉ አካላት እወቅናና ምስጋና ተሰጠ

የህዝበ ውሳኔ ድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ በሠላምና በስኬት እንዲጠናቀቅ ላስቻሉ አካላት እወቅናና ምስጋና ተሰጠ

የወላይታ ዞን አስተዳደር ህዝበ ውሳኔ ድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ በሠላምና በስኬት እንዲጠናቀቅ ላስቻሉ አካላት የእወቅናና ምስጋና ሰጥቷል።

በእውቅናና ምስጋና መርሃግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የደቡብ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ተስፉዬ ይገዙ ብርዱና ፀሐይ ሳይበግረው ከሌሊቱ 11:00 ጀምሮ ተሰልፎ ድምጽ የሰጠውና በሠላም እንዲጠናቀቅ ያደረገው ህዝባችን ትልቅ ክብር ይገበዋል ብለዋል።

በየደረጃው ያለው ፖለቲካ አመራር በተደራጀና በተቀናጀ ሁኔታ በመሰራት በስኬት እንዲጠናቀቅ ያሳየው ትጋትና ቁርጠኝነት የሚመሰገንና የሚደነቅ ነው ያሉት።

በዞናችን ለፀጥታ ስጋት የሚሆኑ ብዙ ችግሮችን በመከላከልና ህዝቡን በማስተባበር የመሩና የተጉ የፀጥታ አካላትን አመስግነዋል።

አያይዘውም አንድም የፀጥታ ችግር ሳይከሰት ህዝበ ውሳኔው የድምጽ አሰጣጥ በስኬት እንዲጠናቀቅ ለፀጥታ ስራ አጋዥ የሆኑ አካላት ያሳዩት ትብብር ምስጋና…Read More

በደቡብ ክልል 6 ዞኖችና 5 ልዩ ወረዳዎች የተካሔደው ሕዝበ ውሳኔ ድምጽ አሰጣጥ ተጠናቆ ቆጠራ ተጀምሯል

ጥር 29/2015

በደቡብ ክልል 6 ዞኖችና 5 ልዩ ወረዳዎች የተካሔደው ሕዝበ ውሳኔ ድምጽ አሰጣጥ ተጠናቆ ቆጠራ ተጀምሯል - ምርጫ ቦርድ

በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች የተካሄደው የሕዝበ ውሣኔ ድምፅ አሰጣጥ ሒደት ተጠናቆ ቆጠራ መጀመሩን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

ቦርዱ በክልሉ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ ዞኖች እና ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮና ደራሼ ልዩ ወረዳዎች ላይ ዛሬ የተካሄደውን የሕዝበ ውሣኔ ድምፅ መስጠት ሂደትን በተመለከተ ዛሬ ማምሻውን መግለጫ ሰጥቷል።

የድምጽ አሰጣጥ መርሐ ግብሩ ዛሬ ከማለዳ 12 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ ሁለት ሰዓት በ31 ማዕከላት ሥር በሚገኙ 3 ሺህ 771 ምርጫ ጣቢያዎች መከናወኑን የብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ገልፀዋል።

በአብዛኛው ምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ መስጠቱ ሂደት 12 ሰዓት ላይ ተጠናቆ ምርጫ ጣቢያዎች እንዲዘጉ መደረጉንም ነው የተናገሩት።…Read More

የህዝበ ውሳኔ ምርጫ በሰላም መጠናቀቁን አስመልክቶ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ ያስተላለፉት መልዕክት

የህዝበ ውሳኔ ምርጫ በሰላም መጠናቀቁን አስመልክቶ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ ያስተላለፉት መልዕክት

ወላይታ ሶዶ፣ ጥር 29/2015 (ወ/ዞ/መ/ኮጉ/ መምሪያ)

የተከበራችሁ፦

ሠላም ወዳድ የወላይታ ህዝቦች፣የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ሴቶች እና ወጣቶች ፣ አመራር አካላት፣

የፀጥታና ሰላም ተቋማት፣የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች፣የምርጫ አስፈፃሚ ተቋማት፣ ሲቪክ አደረጃጀቶች ፣

ክቡራትና ክቡራን፦

ከሁሉ አስቀድሜ የህዝቦቻችንን የአደረጃጀት ጥያቄ ተከትሎ ተጠቃሚነታቸውን ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ታልሞ በየደረጃው በሚገኙ የህዝብ ምክር ቤቶች ይሁንታ በማግኘት የተፈፀመው ታሪካዊው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምስረታ ህዝበ ውሳኔ ምርጫ በወላይታ ዞን በሰላም መጠናቀቁን በዞናችን አስተዳደርና በራሴ ስም አበስራለሁ።

እንኳን ደስ አላችሁ!!እንኳን ደስ አለን!!!

በዚህ አጋጣሚ ምርጫው በዞናችን ባሉ…Read More

በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች የሕዝበ- ውሳኔ ድምፅ አሰጣጥ ስነ-ስርዓት ተጀመረ

በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች የሕዝበ- ውሳኔ ድምፅ አሰጣጥ ስነ-ስርዓት ተጀመረ

አርባ ምንጭ ጥር 29 ቀን 2015 (ኢዜአ)..በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች የሕዝበ- ውሳኔ ድምፅ አሰጣጥ ስነ-ስርዓት መጀመሩን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የህዝብ ውሳኔ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ዋና አስተባባሪ ወይዘሪት መቅደስ መኮንን ለኢዜአ እንዳሉት የድምጽ አሰጣጥ መርሃ ግብሩ ዛሬ ከማለዳ 12 ሰዓት ጀምሮ እየተካሄደ ያለው በ31 ማዕከላት ሥር በሚገኙ 3 ሺህ 771 ምርጫ ጣቢያዎች ነው።

ህዝብ ውሳኔ የሚካሄድባቸው አካባቢዎች ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦና ጎፋ ዞኖች እንዲሁም ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮና ደራሼ ልዩ ወረዳዎች መሆኑን ጠቁመዋል።

በእነዚህ አካባቢዎች ህዝበ ውሳኔውን ለማስፈጸም ቦርዱ ባለፉት አራት ቀናት ለድምፅ አሰጣጥ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችን ሙሉ ለሙሉ አሰራጭቷል ብለዋል።…Read More

ዞናዊ "የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል" በጋራ የመመስረት የህዝበ ውሳኔ ምርጫ ቅስቀሳ መድረክ እየተካሄደ ነው

ዞናዊ "የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል" በጋራ የመመስረት የህዝበ ውሳኔ ምርጫ ቅስቀሳ መድረክ እየተካሄደ ነው

ወላይታ ሶዶ፤ ጥር 16/2015 በወላይታ ዞን ዞናዊ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋራ የመመስረት የህዝበ ውሳኔ ምርጫ ቅስቀሳ መድረክ የፌደራል፣ የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

የደቡብ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተስፋዬ ይገዙ አምስት ዞኖችና ስድስት ልዩ ወረዳዎች በየምክር ቤቶቻቸው የወሰኑት ወሳኔ በማስመልከት የሚደረግ ህዝበ ውሳኔ መሆኑን ገልጸዋል።

የመድረኩ አስፈላጊነት የአመራር ጥበብ ለማጎልበት፣ የአመለካከትና የተግባር አንድነትም በማጠናከር ህዝበ ውሳኔው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሚያስችል ነው።

የሠላም አብሳሪና የምስራች ነጋሪ የሆነችውን ነጭ ርግብ ህዝቡ በመምረጥ አዲሱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን እንዲመሰረቱ ጥሪ ቀርቧል።

በመድረኩ የፌደራል፣ የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የወረዳና ከተማ አስተዳደር አስተባባሪ አካላት ተገኝተዋል።

Read More