• Call Us
  • +251465512106

የወላይታ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ

የወላይታ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ የተቋቋመበት ዋናው ዓላማ በዞናችን ሳይንስና ቴክኖሎጂን ማልማትና በሁሉም ወረዳ/ከተማ በስፋት በመጠቀም የህብረተሰቡን ኑሮ ማሻሻልና መኢቴ ለዞናችን እድገት የሚሰጠውን ድጋፍ ማሳደግ ነው፡፡ እንዲሁም የ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍን በማሳደግና በፖለቲካዊ ፣ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ያለውን አስተዋጾ በማጎልበት ዞናችን የፈጣን ልማትና እድገት ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡ በመሆኑም  የዞናችን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ  ከዞን  እስከ ቀበሌ ባሉ መንግስታዊ ተቋማት ውስጥ የሚሰጠው አገልግሎት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈና የተደራጀ እንዲሆንና አገልግሎት አሰጣጡ ዘመናዊ ቀልጣፋና ውጤታማ በማድረግ መልካም አስተዳደርን ማስፈንና የሀብት ብክነትን መቀነስ ነው፡፡ በተጨማሪም በህብረተሰቡ ውስጥ ዘመናዊ የመረጃ ቴክኖሎጂን በመዘርጋትና በማስፋፋት ህብረተሰባችን የግብርና፣የገበያ፣ የጤና፣ የትምህርትና ሌሎች መረጃዎችን በአቅራቢያው እንዲያገኙ በማድረግ በገጠርና በከተማው ህብረተሰብ መካከል ያለውን የዘመናዊ መረጃ ቴክኖሎጂ ክፍተት ማጥበብ ነው፡፡

ራዕይ

  • የዞናችንን ህብረተሰብ ኑሮና ሕይወት በሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የተደገፈ ሆኖ ማየት፤

ተልዕኮ

ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂን በማልማትና በሁሉም ሥፍራ በስፋት በመጠቀም የሕብረተሰቡን ኑሮ ማሻሻልና ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ለዞናችን ህብረተሰብ መንግሥት የሚሰጠውን ድጋፍ ማሳደግ፤