• Call Us
  • +251465512106

የወላይታ ዞን  ዋና አስ/ጽ/ቤት

የወላይታ ዞን ዋና አስ/ጽ/ቤት  ሀላፊ አቶ ጻድቁ ፈለቀ ፋልታሞ 

የወላይታ ዞን  ዋና አስ/ጽ/ቤት በወረዳ/ከተማ አሰ/ጽ/ቤት  ባሉ መዋቅሮች የተቋማት የሪፎርም ሥራዎችን በመተግበርና በማስተግበር አገ/ት አሠጣጥ ቅልጥፍናና ውጤታማነትን በማሳደግ የመንግስት ደንቦችና መመሪያዎች አፈፃፀም ተገልጋዩን ህብረተሰብ  የሚያረካ ሆኖ እንድገኝ በማድረግ በልማትና በዴሞክራሲ ሥራዓት ግንባታ እንዲሁም የመልካም አሰ/ር ችግሮችና ፀረ- ኪራይ ሰብሳቢነት ላይ በሚደረገው ትግል የሚኖረውን ተሳትፎ ማሳደግ አንዱና ዋናው ግብ እንደመሆኑ መጠን የተቋሙ ዕቅድ በተቋም የማስፈጸም አቅም ግንባታ፣ የመልካም አሰ/ር እና ለተገልጋዩ ህብረተሰብ በሚሰጠው አገልግሎት የትኩረት መስኮች እያንዳንዱን ትኩረት መስክ  የሚያሳኩ ግቦችን በማዘጋጀት ፣ ግቦችን የሚያሳኩ ዋና ዋና ተግባራት፣ መለኪያዎችና ዒላማዎችን በማስቀመጥ ወደ ተግባር ገብተናል፡፡

    በዚህም በተቋሙ ባሉት ሠራተኞች እና በወረዳ/ ከተማ  አሰ/ጽ/ቤት ባሉት ሠራተኞች ዘንድ የሚታየውን የአመለካከት ፣ የክህሎትና የአደረጃጀት ችግሮችን በመፈታት የለውጥ ሠራዊት በመገንባት ፣ ኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባራትን ለመዋጋት ያስችላሉ ተብለው የተጀመሩ የመልካም አሰ/ርና የፀሬ- ኪራይ ሰብሳቢነት ንቅናቄ ሥራዎች እንዱሁም የሰው ሀብት ሥራ አመራር ሥራዎችን መተግበር ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ በአገ/ት አሠጣጥ ቀልጣፋንና ውጤታማነት እንድሁም የመልካም አሰ/ር ችግሮች ዙሪያ ቀላል ግምት የማይሰጣቸው ለውጦች እየተመዘገበ  ይገኛሉ፡፡