• Call Us
  • +251465512106

በዞኑ ዉስጥ የሚገኙ ዋና ዋና የማዕድን ሀብት ክምችት፡-

በዞናችን ዉስጥ በተለያዩ ወረዳ አስተዳደሮች ለተለያየ የልማት አገልግሎት የሚዉሉ የማዕድን ሀብት ክምችት ያለ ሲሆን ለብሎኬት ማምረቻ አገልግሎት የሚዉል ፑሚስ፤ ለግንባታ አገልግሎትና ለመንገድ ግንባታ የሚዉል ሰኮሪያ፣ ለኮብል ስቶን ሥራ ሊዉል የሚችል ባዛልት፤ ትራካይት፤ ለመስተዋት ሥራ የሚያገለግል አብዚድያን፤ ለግንባታ ሥራ የሚያገለግል ራዮላይት፤ አሸዋ፤ ግራናይት፤ የተለያየ ዓይነትና ቀለም ያለዉ ድንጋይ ክምችት፤  ለኃይል ማመንጫ የሚሆን የድንጋይ ከሰል እንደሚገኙ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ በሁምቦ ወረዳ ሰሜናዊ አባያ ሀይቅ ጫፍ ፍል ውሃ ባለበት አካባቢ መጠኑ ለጊዜው ያልታወቀ ኢፒተርማል የወርቅ ክምችት እንዳለ በስምጥ ሸለቆ ሀይቆች ተፋሰስ ጥናት ተጠቁሟል፡፡