አጠቃላይ ገጽታ
6.1.4 በቱሪዝም ዘርፍ
ለቱሪስት መረጃ ማዕከልነት፣ ለጉዞ ወኪልና መኪና አከራይ አገልግሎት፣ በአስመጭና ላኪነት ለሚሰማሩ ድርጅቶች፣
የዳሞት ተራራ እና የፑንዱኒያ ደን ሀብት ልማት፡- በከተማዋ ሰሜናዊ አቅጣጫ የሚገኘው የዳሞት ተራራ የወላይታ ዞን የከርሰምድርና የገጸምድር የውኃ ምንጭና ታርካዊ ፋይዳ ያላቸው በርካታ ቅርሶችን ያቀፈ ተራራ ከመሆኑም በተጨማሪ የልዩ ልዩ ዕጽዋት ዝርያዎች መገኛና በደን የተከበበ ስለሆነ የአከባቢው አየር ንብረት እንዲስተካከል ከማድረግ ባሻገር ለከተማዋ ግርማ ሞገስ አጎናጽፏታል፡፡ ከዚሁ ተራራ ዙሪያ ከሥሩ የሚነሱ ከ26 በላይ ወንዞች ለአከባቢው ጥቅም ከማዋል አልፎ ለጎረበት ወረዳዎችም ተራራው ጫፍ ወጥቶ አጠቃላይ የከተማዋን ገጽታ ጨምሮ የአባያ ሐይቅ እና ሌሎች አጎራባች ከተሞችን መመልከት በከፍተኛ ርቀት አይሮፕላን ላይ ሆኖ እንደማየት ይቆጠራል፡፡ በመሆኑም በተራራው አናት ላይ በሚገኘው ሜዳ ላይ ደረጃውን የጠበቀ የሆቴል፣ የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ የስልጠና ማዕከላት፣ የዱር አራዊት ፓርክ፣ የገመድ ትራንስፖርት / /፣ ወዘተ ጣምራ አገልግሎቶችን ሊሰጥ የሚችል ዘመናዊ ድርጅት ለመስራት ለሚፈልጉ ባለሀብቶች በሀገሪቱ ውስጥ የመጀመሪያ ተወዳዳሪ የማይገኝለት ምርጫቸው ሊሆን ይችላል፡፡
በተጨማሪም የሞቼና ቦራጎ ዋሻ፣ የፑንዱኒያ የባህር ዛፍ ደን ሀብት ልማት እና በዳሞት ተራራ ላይ የሚካሄደው የካርቦን ፕሮጀክት የከተማዋን የቱሪስት መስህብነት ደረጃውን ከፍ ያደርገዋል፡፡
Copyrights 2019. . All Rights Reserved.
Developed by SNNPRS-SITB & SNNPRS-wza