በሁምቦ ወረዳ አስተዳደር
. አጠቃላይ ገጽታ
የሁምቦ ወረዳ ዋና ከተማ ጠበላ ከዞኑ ርዕሰ መዲና ሶዶ በስተደቡብ በ18 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝና የቆዳ ስፋቱም 859.4 ካሬ ኪ.ሜትር ሲሆን በ45 የገጠር ቀበሌዎች እና በ6 የማዘጋጃ ቤት ከተሞች (ጠበላ፣ ሆብቻ፣ ፋራቾ፣ አባያ፣ ጉሪቾ፣ ቆሊሾቦ፣ እና ጉቱቶ ማዘጋጃ ቤት) የተዋቀረ ነው፡፡
1.1 ከባህር ወለል ከፍታ
ከባህር ወለል በላይ ከ1,001 እስከ 2,500 ሜትር ከፍታ ያላቸው የመሬት ገጾች አሉት፡፡
1.2 የአየር ንብረት
የወረዳው አግሮኢኮሎጂን በተመለከተ 30% ወይና ደጋ እና 70% ቆላ ነዉ፡፡ የዓመቱ አማካይ የሙቀት መጠን 12.6--20 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ነው፡፡ አማካይ ዓመታዊ የዝናብ መጠን ከ1,000 እስከ 1,600 ሚሊ ሜትር ነው፡፡
1.3 ሥነ-ሕዝብ
በ2009 ዓ.ም ከዞኑ ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በተገኘው የስታትስቲክስ መረጃ መሠረት የወረዳው አጠቃላይ የሕዝብ ብዛት 167,099 ሲሆን የሕዝብ ጥግግት 189 በስኳየር ኪ/ሜትር ነው፡፡
. መሠረተ ልማት አቅርቦት ሁኔታ
2.1 መንገድ
የወረዳውን ዋና ከተማ ጠበላ ከአዲስ አበባ-ሶዶ-አርባምንጭ አቋርጦ የሚያልፍ 36.5 ኪ.ሜትር አስፋልት የተዘረጋ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ 204 ኪ/ሜትር የጠጠር እና 696 ኪ/ሜትር ጥሪጊያ መንገድ የተለያዩ የወረዳ ቀበሌዎችን እና አጎራባች ወረዳዎችን እርስ በርስ የሚያገናኝ መንገዶች አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
2.2 ስልክ፣ ኢንተርኔት እና የፖስታ አገልግሎት
ማይክሮወቭ፣ የሞባይልና የመደበኛ ስልክ አገልግሎት፣ እንዲሁም የኢንተርኔት አገልግሎት የሚሰጡ የግል ንግድ ማዕከላት እየተከፈቱ ይገኛሉ፡፡ አንድ የፖስታ አገልግሎት ሰጪ ተቋም በጠበላ ከተማ ይገኛል፡፡
2.3 መብራት
በወረዳው ውስጥ የሚገኙ የከተማ ማዘጋጃ ቤት አስተዳደር መዋቅሮች 24 ሰዓት የሃይደሮ ኤሌክትሪክ ኃይል መብራት አገልግሎት ያገኛሉ፡፡
2.4 የመጠጥ ውኃ አቅርቦት
የመጠጥ ውኃ አቅርቦትን በተመለከተ በእጅ ፓምፕ የሚሠራ የእጅ ጉድጓድ ( ) 6፣ በእጅ ፓምፕ የሚሠራ ጥልቅ ጉድጓድ ( ) 12፣ ጥልቅ ጉድጓድ ስርጭት ( ) 13፣ የምንጭ ውኃ ስርጭት ( ) 3፣ ምንጭ በቦታው ማጎልበት ( ) 9 ይገኛሉ፡፡ የወረዳው የመጠጥ ውኃ ሽፋን 54.45% ሲሆን በዘርፉ ያለውን ከፍተኛ ችግር ለማቃለል የጥልቅ ጓድጓድ ውኃ አገልግሎት ለመስጠት በተለያዩ ቀበሌዎች መስመር እየተዘረጋ ይገኛል፡፡
2.5 የገንዘብ ተቋማት፡-
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ቪዥን ፈንድ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም፣ ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም እንዲሁም ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት እየተከፈቱ ይገኛሉ፡፡
. የማህበራዊ አገልግሎት
3.1 ጤና
3.2 ትምህርት
መዋዕለ ሕጻናት ት/ቤት -------------------------- 3
አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (1-4ኛ ክፍል) -------------- 1
አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (1-8ኛ ክፍል) -------------- 53
ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት (9-10ኛ ክፍል) ------------ 6
መሰናዶ (11-12ኛ ክፍል) -------------------------- 2
የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋም ------------- 1
. በመስኖ የሚለማ የእርሻ መሬት ሁኔታ
በወረዳው ውስጥ 6 የመስኖ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ በመሆናቸው የአከባቢው አርሶ አደር ተጠቃሚ ሲሆን ለአብነት የአባያ ቢሳሬ (300 ሄ/ር)፣ ኤላ (210 ሄ/ር)፣ ሊንታላ (90 ሄ/ር)፣ ቦሳ (100 ሄ/ር)፣ ላሾ (320 ሄ/ር)፣ እና አባላ ፋራቾ (100 ሄ/ር) የመስኖ ፕሮጀክቶች ምርትና ምርታማነት ከማሳደግ አልፎ ለሀገርቱ ኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ፡፡ ይሁን እንጂ ወረዳው ካለው የከርሰ ምድርና የገጸ ምድር ውኃ አቅርቦት ለአብነት ወንዞች (ኤላ፣ ላሾ፣ ሊንታላ፣ ቢሳሬ፣ ዶንቦባ፣ ቢላቴ፣ ፋራቾ) እንዲሁም የአባያ ሐይቅ ከመኖሩ አንጻር እስካሁን በመስኖ የለማው መሬት መጠን እጅግ በጣም ዝቅተኛ ከመሆኑም ባሻገር ወረዳው ከፍተኛ ለመስኖ አገልግሎት ሊውል የሚችል የውኃ ፖቴንሻል እንዳለ፣ ከፍተኛ የዝናብ መጠን መኖሩ እና ለም ዐፈር መኖሩ ለእርሻ ኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡
. በወረዳው የሚመረቱ ዋና ዋና ምርቶች
5.1 ዓመታዊ ሰብሎች
በቆሎ፣ ማሽላ፣ ጤፍ፣ ማሾ፣ ሰሊጥ፣ ስንዴ፣ ገብስ፣ ቦሎቄ፣ ባቄላ፣ ሽንብራ፣ የርግብ አተር፣ ለውዝ፣ የሥራ ሥር ሰብሎች፣ አትክልት (ቀይ ሽንኩርት፣ ቲማትም)፣ ጥጥ፣ ቅመማ ቅመም (በርበሬ)
5.2 ቋሚ ሰብሎች
እንሰት፣ ፍራፍሬ (ሙዝ፣ ማንጎ፣)፣ ካሳቫ፣ ሽፈራው፣ ጃትሮፓ (ቆቦ)
. ለኢንቨስትመንት የተዘጋጀ መሬት
ተ.ቁ
ለኢንዱስትሪ በሄ/ር
ለንግድ፣ ለአገልግሎት፣
ለማህበራዊ አገልግሎት በሄ/ር
ለገጠር እርሻ ልማት በሄ/ር
1
59.53 ሄ/ር
20.71
1810
ምንጭ፡- ጠበላ ከተማ ማዘጋጃ ቤት እና የወረዳው እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ጽ/ቤት
ማሳሰቢያ፡- ለገጠር እርሻ ኢንቨስትመንት የተለዩ ቦታዎችን በተመለከተ በአባላ ማራቃ ቀበሌ ለ4 ባለሀብቶች ከማስፋፊያም ጭምር የታሰበ 300 ሄ/ር፣ በአባያ ቢሳሬ ቀበሌ በአሁኑ ወቅት ነጻ የሆነ 300 ሄ/ር፣ በአባያ ብላቴ ቀበሌ በአሁኑ ወቅት በህገ ወጥ ሰፋሪዎች እየተወረረ ያለ ከ1000 ሄ/ር በላይ መሬት፣ በአባያ ጮካሬ ቀበሌ 70 ሄ/ር፣ በፋንጎ ገልጨጫ ቀበሌ 50 ሄ/ር፣ በአንካ ኦቻ ቀበሌ 40 ሄ/ር፣ በሴሬ ጣውራታ ቀበሌ 25 ሄ/ር እንዲሁም በደንባ ሎሜ ቀበሌ 25 ሄ/ር ሰርቨይ ተደርጎ ለኢንቨስትመንት አገልግሎት ለማዋል ታሳቢ የተደረገ ነው፡፡
. ለኢንቨስትመንት ያለው አመቺነት
7.1 ለግብርና
7.2 ለአግሮ ኢንዱስትሪ
7.3 ለማህበራዊ አገልግሎት
የወረዳው የጤና ሽፋን 94.11% ቢሆንም በላቦራቶሪ እና በግል ፋርማሲ ተቋማት ሽፋን ክፍተት መኖሩን ያሳያል፤
በትምህርት መስክ በመዋዕለ ሕጻናት፣ በ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች፣ እና በከፍተኛ የት/ት ተቋማትና ኮሌጆች፣ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋም ከማስፋፋት አንጻር ያሉትን ክፍተቶች ለመሙላት የግል ባለሀብት በመስኩ ለመሰማራት አመችነቱን ይጠቁማል፡፡
7.4 ለሆቴል፣ ለሪዞርት፣ ለሎጅ፣ ለመዝነኛ ፓርክ እና ቱሪዝም አገልግሎት
7.5 ለማዕድን፣ ኢነርጂ እና ለኮንስትራክሽን ዘርፍ
. የኢንቨስትመንት አማራጭ ዕድሎች
8.1 ግብርና ዘርፍ
8.2 በማህበራዊና በአገልግሎት ዘርፍ
8.3 በኢንዱስትሪ ዘርፍ፡- በኢንዱስትሪ ፖቴንሻል ሰርቨይ / / ጥናት መሠረት በከተማው ውስጥ፡-
Copyrights 2019. . All Rights Reserved.
Developed by SNNPRS-SITB & SNNPRS-wza