• Call Us
  • +251465512106

በኦፋ ወረዳ አስተዳደር

 . አጠቃላይ ገጽታ

የኦፋ ወረዳ ዋና ከተማ ገሱባ ከዞኑ ርዕሰ መዲና ሶዶ በስተምዕራብ በ33 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝና የቆዳ ስፋቱም 385.4 ካሬ ኪ.ሜትር ሲሆን በ22 የገጠር ቀበሌዎች የተዋቀረ ነው፡፡ በአስተዳደሩ የሚገኙ የኢንቨስትመንት አማራጮች፤ የማዕድን ሀብት ክምችትና የቱሪስት መስህቦች እንደሚከተለዉ ቀርበዋል፡፡

1.1 ከባህር ወለል ከፍታ

ከባህር ወለል በላይ ከ501 እስከ 2,900 ሜትር ከፍታ ያላቸው የመሬት ገጾች አሉት፡፡

1.2 የአየር ንብረት

የወረዳው አግሮኢኮሎጂን በተመለከተ 24.4% ቆላ፣ 60.1% ወይና ደጋ እና 15.5% ደጋ ነዉ፡፡ የዓመቱ አማካይ የሙቀት መጠን 17.6--22.5 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ነው፡፡ አማካይ ዓመታዊ የዝናብ መጠን ከ1,400 እስከ 1,600 ሚሊ ሜትር ነው፡፡

1.3 ሥነ-ሕዝብ

በ2009 ዓ.ም ከዞኑ ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በተገኘው የስታትስቲክስ መረጃ መሠረት የወረዳው አጠቃላይ የሕዝብ ብዛት 138,427 ሲሆን የሕዝብ ጥግግት 349 በስኳየር ኪ/ሜትር ነው፡፡

  . መሠረተ ልማት

2.1 መንገድ

የወረዳውን ዋና ከተማ ገሱባ ከሶዶ-ሳውላ አቋርጦ የሚያልፍ የጠጠር መንገድ የተዘረጋ ሲሆን ደረጃውን የጠበቀ የአስፋልት መንገድ ደረጃ ለማሳደግ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተሠሩ ይገኛሉ፤ ከዚህም በተጨማሪ 201.5 ኪ/ሜትር የጠጠር እና 453 ኪ/ሜትር ጥሪጊያ መንገድ የተለያዩ የወረዳ ቀበሌዎችን እና አጎራባች ወረዳዎችን እርስ በርስ የሚያገናኝ መንገዶች አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡   

2.2 ስልክ፣ ኢንተርኔት እና የፖስታ አገልግሎት

የሞባይልና የመደበኛ ስልክ አገልግሎት፣ እንዲሁም የኢንተርኔት አገልግሎት የሚሰጡ የግል ንግድ ማዕከላት እየተከፈቱ ይገኛሉ፡፡ አንድ የፖስታ አገልግሎት ሰጪ ተቋም በገሱባ ከተማ ይገኛል፡፡

2.3 መብራት

በወረዳው ውስጥ የሚገኙ የከተማ ማዘጋጃ ቤት አስተዳደር አከባቢዎች 24 ሰዓት የሃይደሮ ኤሌክትሪክ ኃይል መብራት አገልግሎት ያገኛሉ፡፡

2.4 የመጠጥ ውኃ አቅርቦት

የመጠጥ ውኃ አቅርቦትን በተመለከተ በእጅ ፓምፕ የሚሠራ የእጅ ጉድጓድ (                                    ) 2፣ በእጅ ፓምፕ የሚሠራ ጥልቅ ጉድጓድ (                                   ) 29፣ ጥልቅ ጉድጓድ ስርጭት (                       ) 3፣ የምንጭ ውኃ ስርጭት (                         ) 15፣ ምንጭ ማጎልበት (           ) 58 ይገኛሉ፡፡ የወረዳው የመጠጥ ውኃ ሽፋን 68.56% ሲሆን በዘርፉ ያለውን ከፍተኛ ችግር ለማቃለል የጥልቅ ጓድጓድ ውኃ አገልግሎት ለመስጠት በተለያዩ ቀበሌዎች መስመር እየተዘረጋ ይገኛል፡፡

2.5 የገንዘብ ተቋማት፡-

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም እንዲሁም ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት እየተከፈቱ ይገኛሉ፡፡

   . የማህበራዊ አገልግሎት

3.1 ጤና

  • ሆስፒታል /        / ------------------------ 1 (በግንባታ ላይ ያለ)
  • ጤና ጣቢያ /             / ------------- 4
  • ጤና ኬላ /           / ------------------ 27
  • የመጀመሪያ ደረጃ ክሊንክ /      / ------- 10 (የግል)  
  • መድኃኒት ቤት /        / --------------- 4 (የመንግስት)
  • መድኃኒት መደብር --------------------------- 1 (የግል)
  • ላቦራቶሪ --------------------------------------- 4 (የመንግስት)
  • የጤና ሽፋን ---------------------------------- 87.1%

3.2 ትምህርት

መዋዕለ ሕጻናት ት/ቤት --------------------------  1

አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (1-4ኛ ክፍል) -------------- 7

አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (1-8ኛ ክፍል) -------------- 26

ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት (9-10ኛ ክፍል) ------------ 3

መሰናዶ (11-12ኛ ክፍል) --------------------------- 1

የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ፖሊቴክኒክ ----------- 1

  . በመስኖ የሚለማ የእርሻ መሬት ሁኔታ

በወረዳው ውስጥ 3 የመስኖ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ በመሆናቸው የአከባቢው አርሶ አደር ተጠቃሚ ሲሆን ለአብነት ቡሻ መስኖ በቡሻ ቀበሌ (200 ሄ/ር)፣ መንኢሳ መስኖ በዳቃያ ቀበሌ (200 ሄ/ር) እና ወዮ መስኖ በጋልዳ ቀበሌ (150 ሄ/ር) የመስኖ ፕሮጀክቶች ምርትና ምርታማነት ከማሳደግ አልፎ ለሀገርቱ ኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ፡፡ ይሁን እንጂ ወረዳው ካለው የከርሰምድርና የገጸምድር ውኃ አቅርቦት ለአብነት ወንዞች (መንኢሳ፣ ደሜ እና ጎገራ/ሊንታላ) ከመኖሩ አንጻር እስካሁን በመስኖ የለማው መሬት መጠን በጣም ዝቅተኛ ከመሆኑም ባሻገር ወረዳው ከፍተኛ ለመስኖ አገልግሎት ሊውል የሚችል የውኃ ፖቴንሻል እንዳለ፣ ከፍተኛ የዝናብ መጠን መኖሩ እና ለም ዐፈር መኖሩ ለእርሻ ኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡

 . በወረዳው የሚመረቱ ዋና ዋና ምርቶች

ሀ/ ዓመታዊ ሰብሎች

በቆሎ፣ ጤፍ፣ ሰሊጥ፣ ስንዴ፣ ገብስ፣ ቦሎቄ፣ ባቄላ፣ አተር፣ ሽንብራ፣ ማሾ፣ ለውዝ፣ የሥራ ሥር ሰብሎች፣ ጥጥ፣ አትክልት (ቀይ ሽንኩርት፣ ቲማትም)፣ ቅመማ ቅመም (አርቲሜዥያ)

ለ/ ቋሚ ሰብሎች

ፍራፍሬ (ሙዝ፣ ማንጎ፣ አፕል፣ አቮካዶ)፣ ካሳቫ፣ ሽፈራው፣ ጃትሮፓ (ቆቦ)፣ እንሰት፣ ቡና፣

 

  . ለኢንቨስትመንት የተዘጋጀ መሬት

ተ.

ለኢንዱስትሪ  

ለንግድ፣ ለአገልግሎት፣ ለሌሎች  በሄ/ር

ለከተማ ግብርና በሄ/

ለገጠር እርሻ ልማት በሄ/

1

50 ሄ/

35 ሄ/

8

250

  ምንጭ፡- ገሱባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት እና የወረዳው እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ጽ/ቤት

ማሳሰቢያ፡- ለገጠር እርሻ ኢንቨስትመንት የተለዩ ቦታዎችን በተመለከተ በማንቻ ጎገራ ቀበሌ ልዩ ስሙ አጉሜ እና ጉሉዋ በተባለው 200 ሄ/ር እንዲሁም 50 ሄ/ር መሬት ከጃትሮፓ ባዮ ፍዩል የተቀማ እና ሰርቨይ ተደርጎ በኢንቨስትመንት መሬት ባንክ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ከገሱባ ማዘጋጃ ቤት በተገኘው መረጃ መሠረት ከ93 ሄ/ር በላይ መሬት ለተለያዩ አገልግሎቶች በከተማው መሠረታዊ ፕላን መሠረት የተዘጋጀ መሆኑን ታሳቢ ሊደረግ ይገባል፡፡

   . ለኢንቨስትመንት ያለው አመቺነት

7.1 ለግብርና

  • ሰፊ በመስኖ የሚለማ የአርሶ አደር ማሳ እና የወል መሬት መኖሩ፣
  • ዓመታዊ አማካይ የዝናብ መጠን ከፍተኛ መሆኑ፣
  • በወረዳው ዓመቱን ሙሉ የማይደርቁ ወንዞች ማለትም መንኢሳ ወንዝ፣ ደሜ ወንዝ እና ጎገራ/ሊንታላ ወንዝ እንዲሁም በተፋሰስ የለሙና የተካለሉ ሰፊ ቦታዎች ያሉት በመሆኑ በንብ ማነብ፣ በበሬ ድለባ፣ በበግ ማሞከት፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት፣ በዘመናዊ እንሰሳት ዕርባታ፣ ለዶሮ ዕርባታ እንዲሁም ዓሳ ዕርባታ በሰው ሰራሽ ኩሬ ለማካሄድ ምቹ መሆኗ፣
  • በልማት ሥራ ላይ ለማዋል በቂ የሰው ኃይል /የተማረ እና የጉልበት/ መኖሩ፣
  • በለሙ ተፋሰሶች እና በአርሶ አደር ማሳ የተሻሻለ መኖ፣ ምጥን መኖ፣ የተለያዩ የሰብል ተረፈ ምርቶች፣ የተፈጥሮ ግጦሽ መኖ አቅርቦት መኖሩ፤
  • እንስሳት ዕርባታ እና ድለባ ለማካሄድ ከፍተኛ የቀንድ ከብት ክምችት፣ ውኃ እና የግብይት ማዕከላት መኖሩ፤ በዞን አቀፍም ሆነ ሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የገበያ ፍላጎት መኖሩ፤
  • ለፍየሎች የቅንጠባ መኖዎች ያለባቸው ሰፋፊ የተፈጥሮ ደኖች መኖራቸው፤
  • የተሻሻለ የእንስሳት ዝሪያ እየተስፋፋ መሆኑ (በሰው ሰራሽ ዘዴ በማዳቀል)፤
  • ከፍተኛ የሀገረሰብና የተሻሻለ የበግ፣ የፍየል እና የዶሮ አቅርቦት መኖሩ፤
  • ለንብ አበባ ቀሰማ ምቹ የሆኑ የተፈጥሮ ደኖች፣ በለሙ ተፋሰሶች፣ የፍራፍሬ ዛፎች መኖራቸው፤
  • የአፕል ማንጎ ለማዳቀል የአፕል ችግኝ ማባዣ ጣቢያ መኖሩ (ያክማ፣ ኦሜ ቦሎላ፣ ዎሼ አልዳዳ፣ ወዘተ) ለኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ የተመቻቹ ሁኔታዎች ናቸው፡፡

7.2 ለአግሮ ኢንዱስትሪ

  • ከአርሶ አደሩ የሚገኙትን የግብርና ምርቶችን (በአውትግራውር ከአርሶ አደሩ ጋር ትስስር በመፍጠር) በጥሬ ዕቃነት ተጠቅሞ በማቀነባበር እስከ ውጪ ገበያ ድረስ ለሚያቀርቡ ባለሀብቶች መሬቱ አመቺነት ያለው በመሆኑ ያለውጣውርድ ማግኘት ይቻላል፤
  • ለተለያዩ ፋብሪካዎች በጥሬ ዕቃነት ሊያገለግሉ የሚችሉ የግብርና ምርቶች የሆኑ እንደ ቦቆሎ፣ ቡና፣ ሾንኮራ አገዳ፣ አቮካዶ፣ ማንጎ፣ አፕል፣ ቲማቲም፣ ጥጥ፣ ሙዝ፣ ቦሎቄ እና እንስሳት ሀብት በቅርብ መገኘታቸዉ፤
  • ለእንስሳት መኖ ዝግጅት ምቹ ሁኔታ (አልፋአልፋ፣ ሉሲኒያ፣ ላብላብ፣ አኩሪ አተር፣ የርግብ አተር፣ ኤሌፈንት ሳር፣ ዴሾ ሣር፣ ወዘተ በአሁኑ ወቅት በተፋሰስ በለሙ ቦታዎች በስፋት እየተመረተ በመሆኑ እንዲሁም በቀላሉ ሊለማ የሚችልና በቂ የተዘጋጀ ቦታ በመኖሩ፣

7.3 ለማህበራዊ አገልግሎት

የወረዳው የጤና ሽፋን 87.1% ቢሆንም በላቦራቶሪ እና በግል ፋርማሲ ተቋማት ሽፋን ክፍተት መኖሩን ያሳያል፤

የመዋዕለ ሕጻናት እና የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ተቋማት ብዛት ዝቅተኛ መሆኑ እንዲሁም በከፍተኛ የት/ት ተቋማት ወይም ኮሌጆች በወረዳው ውስጥ ያለመኖር ለግል ባለሀብት በመስኩ መሰማራት አመችነቱን ይጠቁማል፡፡

7.4 ለሆቴል፣ ለሪዞርት፣ ለሎጅ፣ ለመዝነኛ ፓርክ እና ቱሪዝም አገልግሎት

  • የተፈጥሮ እግዘር ድልድይ /ጦሣ ዛሪጵያ/ (በዳቃያና ቡሻ ቀበሌ)፣ ከ150 በላይ የሆኑ ቁም ትክል ድንጋይ (ሙሬ በጋልዳ ቀበሌ፣ የማሮ ሳዶ በቃንቆ ቦሻሼ ቀበሌ፣ የወቆ እና ዳልባዛ በጢዳ ቀበሌ፣ ዞጊሳ፣ ኦልባቻ እና የጋዘ ትክል ድንጋይ በኦኮቶ ሴሬ ቀበሌ)፣ ሆሎዞ ተራራ (በያክማ ቀበሌ)፣ የአማዶ ካብ (ዋራዛ ኤሾ፣ ሴሬ ኤሾ፣ ማንቻ፣ ኮዶ፣ ጋልዳ፣ ጥዳ እና ጋርቤ ቀበሌን አቋርጦ የሚያልፍ)፣ ሳኣ ቱሳ (ኮዶ ቀበሌ)፣ ፍል ውኃዎች (በኮዶ ቀበሌ ላሞሬ እና በገሱባ 02 ቀበሌ)፣ ፏፏቴዎች (የአንዳቦ ፏፏቴ እና መንኢሳ ፏፏቴ)፣ ዋሻዎች (የሀሩሮና፣ አሩጂያ፣ ቦልከሼ፣ ዲንቦሳ፣ ዳዌ፣ ጎንጎሎ እና ኡኬ ዋሻ) እንዲሁም ያክማ አለቋ ኦዶሩዋ (በ1880ዎቹ የወላይታ ሕዝብ በራስ መንገሻ የተመራውን የአጼ ሚኒሊክ ጦርን የንብ መንጋን በመበተን ሙሉ በሙሉ የማረኩበት ታሪካዊ ቦታ) በወረዳው ውስጥ የሚገኙ በመሆናቸው የቱሪስት መስህብነት ደረጃውን ከፍ ያደርጋሉ፡፡
  • በወረዳው ዋና ከተማም ሆነ በሌሎች የማዘጋጃ ቤቶች ውስጥ ደረጃውን የጠበቀ ሆቴል፣ ሎጅ፣ ሪዞርት፣ ፔንሲዮን እና የመዝነኛ ማዕከላት ያለመኖሩ በዘርፉ የገበያ ክፍተት መኖሩን ያሳያል፤     
  • በወረዳው የሚገኙ ሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ የቱሪስት መስህቦች ቁጥር በርካታ በመሆኑ ቱሪስት የመሳብ አቅም ከፍተኛ ስለሆነ እንዲሁም ለዘርፉ ኢንቨስትመንት በቂ የለማ ቦታ የተዘጋጀ በመሆኑ ባለሃብቱ ቢሠማራበት አዋጭ ነዉ፡፡

 7.5 ለማዕድን፣ ኢነርጂ እና ለኮንስትራክሽን ዘርፍ

  • ለኮንስትራክሽን የሚያገለግሉ ጥሬ ዕቃዎች በአከባቢዉ በበቂ ሁኔታ መገኘታቸዉ፣ ነጭ ድንጋይ (1.2 ሄ/ር የሚሸፍን በጋልዳ ቀበሌ እና በገሱባ 02 ቀበሌ)፣ ጥቁር ድንጋይ (1.6 ሄ/ር በማንቻ ቀበሌ እና በሴሬ ኤሾ ቀበሌ)፣ አሸዋ (6000 ካሬ ሜትር)፣ ለኮብል ስቶን የሚሆን ድንጋይ (1 ሄ/ር የሚሸፍን በሴሬ ኤሾ እና በማንቻ ቀበሌ)፣ የመሳሰሉት በከፍተኛ መጠን መኖሩ፤
  • ለጂፕሰም ቦርድ እና ለጠመነ /     / ማምረት ሊውል የሚችል ድንጋይ፣
  • ለግንባታ አገልግሎትና ለኮብል ስቶን ሥራ ሊዉል የሚችል ባዛልትክ ድንጋይ፣

    . የኢንቨስትመንት አማራጭ ዕድሎች

8.1 ግብርና ዘርፍ

  • አትክልትና ፍራፍሬ ልማት (ማንጎ፣ አፕል፣ አቦካዶ፣ ሙዝ፣ ፓፓያ)፣
  • ቅመማ ቅመም (አርቲሜዥያ) ልማት፣
  • የወተትና ሥጋ ከብት ማርባትና ማድለብ፣
  • በዶሮ ዕርባታና እንቁላል ምርት፣ በንብ ማነብ፣ በበግና ፍየል ማሞከት፣
  • የእንስሳት መኖ ዘር ማባዛትና ማልማት፣
  • ለባዮ ዲዝል ምርት የሚሆን የጃትሮፋ ተክል ማልማት፣

8.2 በማህበራዊና በአገልግሎት ዘርፍ

  • በትምህርት ዘርፍ ከመዋዕለ ህፃናት እስከ ኮሌጅ፤
  • በጤና ዘርፍ በክሊኒክ፣ ላቦራቶሪ፣ ፋርማሲ፣ በእንስሳት ህክምና ማዕከላት፣
  • በመዝነኛ አገልግሎት ዘርፍ፡- ሲኒማ ቤቶች፣ ፊልምና ቲያትር ቤቶች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ጂም ቤቶች እና ሌሎች፣
  • በሆቴልና ቱሪዝም ከካፌ እስከ ባለኮከብ ሆቴል፣
  • ለሎጅ፤ ለሪዞርትና መዝናኛ ማዕከል፣

8.3 በኢንዱስትሪ ዘርፍ፡- የኢንዱስትሪ ፖቴንሻል ሰርቨይ /   / ጥናት መሠረት በከተማው ውስጥ

  • ለምግብና ምግብ ውጤቶች ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣
  • ለሥጋና የሥጋ ውጤቶች ማቀነባበሪያ፣
  • የወተትና የወተት ውጤቶች ማቀነባበሪያ፣
  • ለአትክልትና ፍራፍሬ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣
  • ከቅባት እህሎች /ሰሊጥ፣ ኑግ፣ ለውዝ፣ ወዘተ/ ማምረቻ ፋብሪካ፣
  • የማዕድን ውኃ ማሸጊያ፣
  • የእንስሳት መኖ ዘር ማባዣ፣ ማቀነባበሪያና ማሸጊያ ፋብሪካ፣
  • የአፕል ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣
  • አርቲሜዥያ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣
  • የማርና ሰም ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣
  • የብሎኬት እና የጠጠር ማምረቻ፣