. አጠቃላይ ገጽታ
የኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ዋና ከተማ በሌ ከዞኑ ርዕሰ መዲና ሶዶ በስተምዕራብ በ37 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝና የቆዳ ስፋቱም 526.3 ካሬ ኪሜትር ሲሆን በ23 የገጠር ቀበሌዎች እና በሦስት የማዘጋጃ ቤት ከተሞች (በሌ፣ ሃናዜ እና ሶርቶ ማዘጋጃ ቤት) የተዋቀረ ነው፡፡ በአስተዳደሩ የሚገኙ የኢንቨስትመንት አማራጮች፤ የማዕድን ሀብት ክምችትና የቱሪስት መስህቦች እንደሚከተለዉ ቀርበዋል፡፡
1.1 ከባህር ወለል ከፍታ
ከባህር ወለል በላይ ከ600 እስከ 2,280 ሜትር ከፍታ ያላቸው የመሬት ገጾች አሉት፡፡
1.2 የአየር ንብረት
የወረዳው አግሮኢኮሎጂን በተመለከተ 72% ቆላ፣ 20% ወይና ደጋ እና 8% ደጋ ነዉ፡፡ የዓመቱ አማካይ የሙቀት መጠን 12.6--25 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ነው፡፡ አማካይ ዓመታዊ የዝናብ መጠን ከ1,401 እስከ 1,600 ሚሊ ሜትር ነው፡፡
1.3 ሥነ-ሕዝብ
በ2009 ዓ.ም ከዞኑ ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በተገኘው የስታትስቲክስ መረጃ መሠረት የወረዳው አጠቃላይ የሕዝብ ብዛት 139,662 ሲሆን የሕዝብ ጥግግት 258 በስኳየር ኪ/ሜትር ነው፡፡
. የመሠረተ ልማት አቅርቦት ሁኔታ
2.1 መንገድ
የወረዳውን ዋና ከተማ በሌ ከሶዶ- ዳውሮ ታርጫ አቋርጦ የሚያልፍ የአስፋልት መንገድ የተዘረጋ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ 59.9 ኪ/ሜትር የጠጠር እና 496 ኪ/ሜትር ጥሪጊያ መንገድ የተለያዩ የወረዳ ቀበሌዎችን እና አጎራባች ወረዳዎችን እርስ በርስ የሚያገናኝ መንገዶች አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
2.2 ስልክ፣ ኢንተርኔት እና የፖስታ አገልግሎት
የሞባይልና የመደበኛ ስልክ አገልግሎት፣ እንዲሁም የኢንተርኔት አገልግሎት የሚሰጡ የግል ንግድ ማዕከላት እየተከፈቱ ይገኛሉ፡፡ አንድ የፖስታ አገልግሎት ሰጪ ተቋም በበሌ ከተማ ይገኛል፡፡
2.3 መብራት
በወረዳው ውስጥ የሚገኙ የከተማና ማዘጋጃ ቤት ያላቸው ቀበሌ አስተዳደር አከባቢዎች 24 ሰዓት የሃይደሮ ኤሌክትሪክ ኃይል መብራት አገልግሎት ያገኛሉ፡፡
2.4 የመጠጥ ውኃ አቅርቦት
የመጠጥ ውኃ አቅርቦትን በተመለከተ በእጅ ፓምፕ የሚሠራ በእጅ ፓምፕ የሚሠራ ጥልቅ ጉድጓድ ( ) 1፣ ጥልቅ ጉድጓድ ስርጭት ( ) 1፣ የምንጭ ውኃ ስርጭት ( ) 40፣ ምንጭ ማጎልበት ( ) 38 ይገኛሉ፡፡ የወረዳው የመጠጥ ውኃ ሽፋን 82.45% ነው፡፡
2.5 የገንዘብ ተቋማት፡-
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም እንዲሁም ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት እየተከፈቱ ይገኛሉ፡፡
. የማህበራዊ አገልግሎት
3.1 ጤና
3.2 ትምህርት
መዋዕለ ሕጻናት ት/ቤት -------------------------- 2
አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (1-4ኛ ክፍል) -------------- 3
አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (1-8ኛ ክፍል) -------------- 40
ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት (9-10ኛ ክፍል) ------------ 4
መሰናዶ (11-12ኛ ክፍል) --------------------------- 1
የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋም------ ----------- 1
. በመስኖ የሚለማ የእርሻ መሬት ሁኔታ
በወረዳው ውስጥ 3 የመስኖ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ በመሆናቸው የአከባቢው አርሶ አደር ተጠቃሚ ሲሆን ለአብነት ኦንጎቶ መስኖ በቦርኮሼ ቀበሌ (70 ሄ/ር)፣ ባሊያ መስኖ በሞልቲቾ ቀበሌ (100 ሄ/ር) እና ለፍያ መስኖ በሙንዴና ቀበሌ (560 ሄ/ር) የመስኖ ፕሮጀክቶች ምርትና ምርታማነት ከማሳደግ አልፎ ለሀገርቱ ኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ፡፡ ይሁን እንጂ ወረዳው ካለው የከርሰምድርና የገጸምድር ውኃ አቅርቦት ለአብነት ወንዞች (ኦሞ፣ ጋሙዋ፣ ጋጉራ፣ ኬላ፣ ፍንቻዋ፣ ኦንጎቶ፣ ባሊያ እና ሳንኩራ) ከመኖሩ አንጻር እስካሁን በመስኖ የለማው መሬት መጠን በጣም ዝቅተኛ ከመሆኑም ባሻገር ወረዳው ከፍተኛ ለመስኖ አገልግሎት ሊውል የሚችል የውኃ ፖቴንሻል እንዳለ፣ ከፍተኛ የዝናብ መጠን መኖሩ እና ለም ዐፈር መኖሩ ለእርሻ ኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡
. በወረዳው የሚመረቱ ዋና ዋና ምርቶች
5.1 ዓመታዊ ሰብሎች
በቆሎ፣ ማሽላ፣ ጤፍ፣ ስንዴ፣ ሰሊጥ፣ ገብስ፣ ቦሎቄ፣ ባቄላ፣ አተር፣ ማሾ፣ የሥራ ሥር ሰብሎች፣ አትክልት (ቀይ ሽንኩርት፣ ቲማትም)፣ ቅመማ ቅመም (ዝንጅብል፣ በርበሬ)
5.2 ቋሚ ሰብሎች
ፍራፍሬ (ሙዝ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ፣ አቮካዶ)፣ ካሳቫ፣ ሽፈራው፣ ጃትሮፓ (ቆቦ)፣ እንሰት፣ ቡና፣
. ለኢንቨስትመንት የተዘጋጀ መሬት በሄ/ር
ተ.ቁ
የቀበሌው ስም
(ልዩ መንደር)
ለኢንዱስትሪ
ለንግድ፣ ለማህበራዊ አገልግሎት
ለገጠር እርሻ ልማት ሊውል የሚችል መሬት
1
በሌ ከተማ
50 ሄ/ር
16.7 ሄ/ር
------
2
ማንአራ ቀበሌ
-----
400 (ለሰብል ልማት)
3
ፋጀና ማታ ቀበሌ
150 (ለሰብል ልማት)
4
ሀናዜ ቀበሌ
170 (ለሰብል ልማት)
5
ኪንዶ ሀንጋላ ቀበሌ
140 (ለሰብል ልማት)
6
ሙንዴና ቀበሌ
220 (ለሰብል ልማት)
7
ፈጨና ቀበሌ
430 (ለአትክልትና ፍራፍሬ ልማት)
8
ባዴ ወይዴ
250 >
9
ሶርቶ
280 >
10
ጨራቾ
230 >
11
ሴሬ አታላቻ
293 >
ድምር
50
16.7
2,563 ሄ/ር
ምንጭ፡- በሌ ከተማ ማዘጋጃ ቤት እና የወረዳው እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽ/ቤት
ማሳሰቢያ፡- ለገጠር እርሻ ኢንቨስትመንት የተለዩ ቦታዎችን በተመለከተ ከወረዳዉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽ/ቤት ለኢንቨስትመንት ሊዉል የሚችል የወል መሬት ከላይ በሠንጠረዡ የተመለከተው ሰርቨይ ተደርጎ የተካለለ ሲሆን ከበሌ ማዘጋጃ ቤት በተገኘው መረጃ መሠረት 66.7 ሄ/ር ለተለያዩ አገልግሎቶች በከተማው መሠረታዊ ፕላን መሠረት የተዘጋጀ መሆኑን ታሳቢ ሊደረግ ይገባል፡፡
. ለኢንቨስትመንት ያለው አመቺነት
7.1 ለግብርና
7.2 ለአግሮ ኢንዱስትሪ
7.3 ለማህበራዊ አገልግሎት
የወረዳው የጤና ሽፋን 93.90% ቢሆንም በላቦራቶሪ እና በግል ፋርማሲ ተቋማት ሽፋን ክፍተት መኖሩን ያሳያል፤
የመዋዕለ ሕጻናት እና የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ተቋማት ብዛት ዝቅተኛ መሆኑ እንዲሁም በከፍተኛ የት/ት ተቋማት ወይም ኮሌጆች በወረዳው ውስጥ ያለመኖር ለግል ባለሀብት በመስኩ መሰማራት አመችነቱን ይጠቁማል፡፡
7.4 ለሆቴል፣ ለሪዞርት፣ ለሎጅ፣ ለመዝነኛ ፓርክ እና ቱሪዝም አገልግሎት
7.5 ለማዕድን፣ ኢነርጂ እና ለኮንስትራክሽን ዘርፍ
ለኮንስትራክሽን የሚያገለግሉ ጥሬ ዕቃዎች በአከባቢዉ በበቂ ሁኔታ መገኘታቸዉ፣ ግራናይት፣ ነጭ ድንጋይ ለግንባታ አገልግሎት የሚውል በሞልቲቾ እና ፋጀና ማታ ቀበሌ፣ ጥቁር ድንጋይ ለጠጠር ምርት የሚሆን በሶርቶ ቀበሌ፣ ትራካይት እና ባዛልትክ ድንጋይ /ለኮብል ስቶንና ለኮንክሪት አገልግሎት/ የሚሆን ድንጋይ በሙንዴና ቀበሌ፣ የመሳሰሉት በከፍተኛ መጠን መኖሩ፤
. የኢንቨስትመንት አማራጭ ዕድሎች
8.1 ግብርና ዘርፍ
8.2 በማህበራዊና በአገልግሎት ዘርፍ
8.3 በኢንዱስትሪ ዘርፍ፡- የኢንዱስትሪ ፖቴንሻል ሰርቨይ / / ጥናት መሠረት በከተማው ውስጥ
Copyrights 2019. . All Rights Reserved.
Developed by SNNPRS-SITB & SNNPRS-wza