. አጠቃላይ ገጽታ
የኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ ዋና ከተማ ሃላሌ ከዞኑ ርዕሰ መዲና ሶዶ በስተምዕርብ የሚትገኝ ሲትሆን ከሶዶ በገሱባ መንገድ 64 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ስትገኝ እንደዚሁም ከሶዶ በበሌ መንገድ 87 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚትገኝ ናት፡፡ የወረዳው የቆዳ ስፋቱም 380.5 ካሬ ኪ/ሜትር ሲሆን በ19 የገጠር ቀበሌዎች እና በአራት የማዘጋጃ ቤት ከተሞች (ሃላሌ፣ ጎጮ፣ ዋሙራ እና ላሾ ማዘጋጃ ቤት) የተዋቀረ ነው፡፡ በአስተዳደሩ የሚገኙ የኢንቨስትመንት አማራጮች፤ የማዕድን ሀብት ክምችትና የቱሪስት መስህቦች እንደሚከተለዉ ቀርበዋል፡፡
1.1 ከባህር ወለል ከፍታ
ከባህር ወለል በላይ ከ500 እስከ 2,800 ሜትር ከፍታ ያላቸው የመሬት ገጾች አሉት፡፡
1.2 የአየር ንብረት
የወረዳው አግሮኢኮሎጂን በተመለከተ 17.6% ቆላ፣ 64.8% ወይና ደጋ እና 17.6% ደጋ ነዉ፡፡ የዓመቱ አማካይ የሙቀት መጠን 15.1--27.5 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ነው፡፡ አማካይ ዓመታዊ የዝናብ መጠን ከ1,400 እስከ 1,600 ሚሊ ሜትር ነው፡፡
1.3 ሥነ-ሕዝብ
በ2009 ዓ.ም ከዞኑ ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በተገኘው የስታትስቲክስ መረጃ መሠረት የወረዳው አጠቃላይ የሕዝብ ብዛት 125,441 ሲሆን የሕዝብ ጥግግት 330 በስኳየር ኪ/ሜትር ነው፡፡
. የመሠረተ ልማት አቅርቦት ሁኔታ
2.1 መንገድ
የወረዳውን ዋና ከተማ ሃላለ ከሶዶ-በሌ-ሃላለ እና ከሶዶ-ገሱባ-ሃላለ በሁለት በኩል አቋርጦ የሚያልፍ የጠጠር መንገድ የተዘረጋ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ 70.7 ኪ/ሜትር የጠጠር እና 296.17 ኪ/ሜትር ጥሪጊያ መንገድ የተለያዩ የወረዳ ቀበሌዎችን እና አጎራባች ወረዳዎችን እርስ በርስ የሚያገናኝ መንገዶች አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
2.2 መደበኛ ስልክ እና ሞባይል አገልግሎት
የሞባይልና የመደበኛ ስልክ አገልግሎት የወረዳው ከተሞች ያገኛሉ፡፡
2.3 መብራት
በወረዳው ውስጥ የሚገኙ የከተማና ማዘጋጃ ቤት ያላቸው አስተዳደር አከባቢዎች 24 ሰዓት የሃይደሮ ኤሌክትሪክ ኃይል መብራት አገልግሎት ያገኛሉ፡፡
2.4 የመጠጥ ውኃ አቅርቦት
የመጠጥ ውኃ አቅርቦትን በተመለከተ በእጅ ፓምፕ የሚሠራ የምንጭ ውኃ ስርጭት ( ) 49፣ ምንጭ በቦታው ማጎልበት ( ) 15 ይገኛሉ፡፡ የወረዳው የመጠጥ ውኃ ሽፋን 52.64% ነው፡፡
2.5 የገንዘብ ተቋማት፡-
በወረዳው ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ብቻ የሚገኝ ሲሆን ዘመናዊ የፋይናንስ ተቋማት (ባንኮችና ኢንሹራንሶች) ባለመኖሩ ለሌሎች አከባቢ ህብረተሰብ አርኣያ ሊሆን የሚችል ከፍተኛ የቁጠባ ባህልን ያዳበረው የአከባቢው ህብረተሰብ ያለ በመሆኑ የግሉ ፋይናንስ ተቋማት ቢቋቋሙ አዋጭነቱ ከፍተኛ ነው፡፡
. የማህበራዊ አገልግሎት
3.1 ጤና
3.2 ትምህርት
መዋዕለ ሕጻናት ት/ቤት -------------------------- 1
አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (1-4ኛ ክፍል) -------------- 2
አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (1-8ኛ ክፍል) -------------- 33
ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት (9-10ኛ ክፍል) ------------ 3
መሰናዶ (11-12ኛ ክፍል) --------------------------- 1
. በመስኖ የሚለማ የእርሻ መሬት ሁኔታ
ወረዳው ካለው የመሬት አቀማመጥ አንጻር ምንም እንኳን ለልማት ሊውሉ የሚችሉ ወንዞች ለአብነት (ኦሞ እና ደሜ) ቢኖሩም የከርሰ ምድርና የገጸ ምድር ውኃን ለመስኖ ለመጠቀም ከፍተኛ አቅም የሚጠይቅ በመሆኑ እስካሁን ድረስ በመንግስትም ሆነ በግል ባለሀብት የተሞከረ ጥረት የለም፡፡
. በወረዳው የሚመረቱ ዋና ዋና ምርቶች
የአገዳ ሰብሎች (በቆሎ፣ ማሽላ)፣ የጥራጥሬ ሰብሎች (ቦሎቄ፣ ባቄላ፣ አተር)፣ የብርዕ ሰብሎች (ጤፍ፣ ስንዴ፣ ገብስ)፣ የሥራ ሥር ሰብሎች (ስኳር ድንች፣ ካሳቫ፣ ጎዳሬ)፣ የቅባት ሰብሎች (ለውዝ)፣ ፍራፍሬ ሰብሎች (አፕል፣ ማንጎ፣ አናናስ፣ አቦካዶ፣ ሙዝ)፣ አትክልት (ቀይ ሽንኩርት፣ ቲማትም)፣ ቅመማ ቅመም (ዝንጅብል፣ በርበሬ)፣ ቡና እና አሪት
. ለኢንቨስትመንት የተዘጋጀ መሬት በሄ/ር
ተ.ቁ
የቀበሌው ስም
(ልዩ መንደር)
ለኢንዱስትሪ
ለኮኮብ ሆቴል፣ ለሪል ስቴትና ለማህበራዊ አገልግሎት
ለከተማ ግብርና
ለገጠር እርሻ ልማት ሊውል የሚችል መሬት
1
ሃለሌ/ሲሜ ዶላዬ መንደር
3.48
7.44 ሄ/ር
6 ሄ/ር
------
2
ሼላ ሳዴ ቀበሌ ባላካ አከባቢ
-----
1,000 ሄ/ር (ለሰብል ልማት)
3
ዜቦ ቀበሌ ኃይሌ መንደር ኦሞ ወንዝ ዳር
300 ሄ/ር (ለሰብል ልማት)
4
ዛሮ ቀበሌ ኤታ መንደር
100 ሄ/ር (ለሰብል ልማት)
5
በቦሳ ማንኣራ፣ ሲሜ ዶላዬ፣ ኪንዶ ማንደና፣ ሼላ መቄራ፣ ዘይራዳ እና በሃላሌ 02 ቀበሌ
2,600 ሄ/ር ለድንጋይ ከሰል (ነጻ የወል መሬት እና የአርሶ አደር ይዞታን የሚያካትት)
ምንጭ፡- ሃላሌ ከተማ ማዘጋጃ ቤት እና የወረዳው እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽ/ቤት
ማሳሰቢያ፡- ለገጠር እርሻ ኢንቨስትመንት የተለዩ ቦታዎችን በተመለከተ ከወረዳዉ ዋና አስተዳዳር ጽ/ቤት ለሰብል ልማት ኢንቨስትመንት ሊዉል የሚችል የወል መሬት ከላይ በሠንጠረዡ የተመለከተው ሰርቨይ ተደርጎ የተካለለ ሲሆን ከፍተኛ የድንጋይ ከሰል ክምችት ያለባቸው 6 ቀበሌያት የሚያካልልና በሰንሰለት ተሳስሮ ያለው በግል ድርጅቶች ተጠንቶ በክልልና በፌዴራል መንግስት ደረጃ ሊለማ እንደሚችል ዕውቅና የተሰጠው በመሆኑ በአሁኑ ወቅት አንድ የግል ድርጅት በ7 ሄ/ር የወል መሬት ተረክቦና ፈቃድ አውጥቶ ወደ ልማት እንቅስቃሴ እየገባ ያለ ሲሆን ሌሎች ባለሀብቶችም በዘርፉ ለመሰማራት ምቹ ሁኔታዎች እንዳሉ ሊታወቅ ይገባል፡፡
. ለኢንቨስትመንት ያለው አመቺነት
7.1 ለግብርና
7.2 ለአግሮ ኢንዱስትሪ
7.3 ለማህበራዊ አገልግሎት
የወረዳው የጤና ሽፋን 81.07% ብቻ መሆኑ በተለይም በላቦራቶሪ እና በግል ፋርማሲ ተቋማት ሽፋን ክፍተት መኖሩን ያሳያል፤
የመዋዕለ ሕጻናት እና የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ተቋማት ብዛት ዝቅተኛ መሆኑ እንዲሁም በከፍተኛ የት/ት ተቋማት ወይም ኮሌጆች በወረዳው ውስጥ ያለመኖር ለግል ባለሀብት በመስኩ መሰማራት አመችነቱን ይጠቁማል፡፡
7.4 ለሆቴል፣ ለሪዞርት፣ ለሎጅ፣ ለመዝነኛ ፓርክ እና ቱሪዝም አገልግሎት
7.5 ለማዕድን፣ ኢነርጂ እና ለኮንስትራክሽን ዘርፍ
ለድንጋይ ከሰል የሚሆንና ከፍተኛ ክምችት ያለው በስድስት ቀበሌዎች መኖሩ፣ ለኮንስትራክሽን የሚያገለግሉ ጥሬ ዕቃዎች በአከባቢዉ በበቂ ሁኔታ መገኘታቸዉ፣ ነጭ ድንጋይ፣ ጥቁር ድንጋይ ለጠጠር ምረት የሚሆን በዋሙራ ቦርኮሼ ቀበሌ እና አሸዋ በደሜ እና ኦሞ ወንዝ፣ የመሳሰሉትን በቅርብ ርቀት የማግኘት ዕድሉ ሰፊ ነው፡፡
. የኢንቨስትመንት አማራጭ ዕድሎች
8.1 ግብርና ዘርፍ
8.2 በማህበራዊና በአገልግሎት ዘርፍ
8.3 በኢንዱስትሪ ዘርፍ-፡ የኢንዱስትሪ ፖቴንሻል ሰርቨይ / / ጥናት መሠረት በወረዳው ውስጥ
Copyrights 2019. . All Rights Reserved.
Developed by SNNPRS-SITB & SNNPRS-wza