• Call Us
 • +251465512106

የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ አስተዳደር

. አጠቃላይ ገጽታ       

የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ከዞኑ ርዕሰ መዲና ሶዶ በስተሰሜን ምዕራብ በ29 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝና የቆዳ ስፋቱም 271.1 ካሬ ኪሜትር ሲሆን በ27 የገጠር ቀበሌዎች እና በ5 ማዘጋጃ ቤት ከተሞች የተዋቀረ ነው፡፡ በአስተዳደሩ የሚገኙ የኢንቨስትመንት አማራጮች፤ የማዕድን ሀብት ክምችትና የቱሪስት መስህቦች እንደሚከተለዉ ቀርበዋል፡፡

1.1 ከባህር ወለል ከፍታ

ከባህር ወለል በላይ ከ501 እስከ 2,500 ሜትር ከፍታ ያላቸው የመሬት ገጾች አሉት፡፡

1.2 የአየር ንብረት

የወረዳው አግሮኢኮሎጂን በተመለከተ 5% ደጋ እና 95% ወይና ደጋ ነዉ፡፡ የዓመቱ አማካይ የሙቀት መጠን 17.6--22.5 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ነው፡፡ አማካይ ዓመታዊ የዝናብ መጠን ከ1,201 እስከ 1,600 ሚሊ ሜትር ነው፡፡

 

1.3 ሥነ-ሕዝብ

በ2009 ዓ.ም ከዞኑ ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በተገኘው የስታትስቲክስ መረጃ መሠረት የወረዳው አጠቃላይ የሕዝብ ብዛት 219,142 ሲሆን የሕዝብ ጥግግት 788 በካሬ ኪ/ሜትር ነው፡፡

II. የመሠረተ ልማት አቅርቦት ሁኔታ 

2.1 መንገድ

ወረዳው ውስጥ 36.5 ኪሎ ሜትር አስፋልት መንገድ፣ 35.5 ኪ/ሜትር የጠጠር እና 1575 ኪ/ሜትር ጥሪጊያ መንገዶች ሲኖሩት በአብዘኛው የወረዳው ቀበሌዎች ከዞንና ከክልል ብሎም ወረዳን ከወረዳ እንዲሁም እያንዳንዱን የገጠር ቀበሌም ጭምር በዋናና በውስጥ ለውስጥ መንገዶች እርስ በእርስ የተገናኘ ነው፡፡

2.2 ስልክ፣ ኢንተርኔት እና የፖስታ አገልግሎት

የሞባይልና የመደበኛ ስልክ አገልግሎት፣ እንዲሁም የኢንተርኔት አገልግሎት የሚሰጡ የግል ንግድ ማዕከላት እየተከፈቱ ይገኛሉ፡፡ አንድ የፖስታ አገልግሎት ሰጪ ተቋም በወረዳው ዋና ከተማ በሆነችው አረካ ከተማ ውስጥ ይገኛል፡፡

2.3 መብራት

በወረዳው ውስጥ የሚገኙ የከተማ አከባቢዎች 24 ሰዓት የሃይደሮ ኤሌክትሪክ ኃይል መብራት አገልግሎት ያገኛሉ፡፡

2.4 የመጠጥ ውኃ አቅርቦት

የመጠጥ ውኃ አቅርቦትን በተመለከተ በእጅ ፓምፕ የሚሠራ የእጅ ጉድጓድ (hand dug wells fitted with hand pump) 68፣ በእጅ ፓምፕ የሚሠራ ጥልቅ ጉድጓድ (shallow wells fitted with hand pump) 70፣ ጥልቅ ጉድጓድ ስርጭት (deep wells distribution) 8፣ የምንጭ ውኃ ስርጭት (springs with distribution) 7፣ ምንጭ በቦታው ማጎልበት (Spot spring) 63 ይገኛሉ፡፡ የወረዳው የመጠጥ ውኃ ሽፋን 62.34% ሲሆን በዘርፉ ያለውን ከፍተኛ ችግር ለማቃለል የጥልቅ ጓድጓድ ውኃ አገልግሎት ለመስጠት በተለያዩ ቀበሌዎች መስመር እየተዘረጋ ይገኛል፡፡

2.5 የገንዘብ ተቋማት፡-

የወረዳው ነዋሪዎች ዘመናዊ የባንክና ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት አገልግሎትን ከወረዳው ዋና ከተማ አረካ ውስጥ ከሚገኙ የፋይናንስ ተቋማት ያገኛሉ፡፡

III. የማህበራዊ አገልግሎት     

3.1 ጤና

 • ጤና ጣቢያ /Health Center/ ------------- 8
 • ጤና ኬላ /Health Post/ ------------------ 30
 • የመጀመሪያ ደረጃ ክሊንክ /Clinic/ --------- 9 (የግል) 
 • መድኃኒት ቤት /Pharmacy/ --------------- 8 (የመንግስት)
 • መድኃኒት መደብር (Drug Store) ------- 10 (የግል)
 • ላቦራቶሪ --------------------------------------- 8 (የመንግስት)
 • የጤና ሽፋን ----------------------------------- 81.4%

3.2 ትምህርት

መዋዕለ ሕጻናት ት/ቤት --------------------------- 12  

አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (1-4ኛ ክፍል) -------------- 4

አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (1-8ኛ ክፍል) -------------- 35

ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት (9-10ኛ ክፍል) ------------ 3

መሰናዶ (11-12ኛ ክፍል) -------------------------- 2

IV. በመስኖ የሚለማ የእርሻ መሬት ሁኔታ            

በወረዳው ውስጥ 3 የመስኖ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ በመሆናቸው የአከባቢው አርሶ አደር ተጠቃሚ ሲሆን ለአብነት ወይቦ መስኖ በማጣላ ሂምቤቾ ቀበሌ (95 ሄ/ር)፣ ሶኬ መስኖ በጢዮ ሂምቤቾ ቀበሌ (273 ሄ/ር)፣ እና ኢጣና መስኖ በጉሩሞ ኮይሻ ቀበሌ (60 ሄ/ር) የመስኖ ፕሮጀክቶች አገልግሎት እየሰጡ በመሆናቸው ለአከባቢው ማህበረሰብ ምርትና ምርታማነት ከማሳደግ አንጻር አዎንታዊ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛል፡፡ ከዚሁ በተጨማሪ ወረዳው ካለው የከርሰ ምድርና የገጸ ምድር ውኃ አቅርቦት ለአብነት ወንዞች (ወይቦ፣ ጋሞ፣ ሻፋ፣ ሶኬ፣ ቁሌ እና ዎተሬ ወንዞች) ከመኖሩ አንጻር እስካሁን በመስኖ የለማው መሬት መጠን በጣም ዝቅተኛ ከመሆኑም ባሻገር ወረዳው ከፍተኛ ለመስኖ አገልግሎት ሊውል የሚችል የውኃ ፖቴንሻል እንዳለ፣ ከፍተኛ የዝናብ መጠን መኖሩ እና ለም ዐፈር መኖሩ ለእርሻ ኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡

V. በወረዳው የሚመረቱ ዋና ዋና ምርቶች  

51 ዓመታዊ ሰብሎች

በቆሎ፣ ጤፍ፣ ማሽላ፣ ስንዴ፣ ቦሎቄ፣ ባቄላ፣ አተር፣ ሽንብራ፣ ገብስ፣ የሥራ ሥር ሰብሎች፣ አትክልት (ቀይ ሽንኩርት፣ ቲማትም)፣ ቅመማ ቅመም ምርት (ዝንጅብል፣ ዕርድ)፣

5.2 ቋሚ ሰብሎች

ፍራፍሬ (ሙዝ፣ ማንጎ፣ አቮካዶ፣ ፓፓያ፣ ብርቱካን)፣ አናናስ፣ እንሰት፣ ቡና፣

 

 

VI. ለኢንቨስትመንት የተዘጋጀ መሬት፡-

 .ቁ

ለኢንዱስትሪ 

ለኮኮብ ሆቴል፣ ለሪል ስቴትና ለማህበራዊ አገልግሎት  

ለከተማ ግብርና በሄ/ር

ለገጠር እርሻ ልማት በሄ/ር

1

 87.4

------

-----

 135 ሄ/ር

     ምንጭ፡- የወረዳው እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽ/ቤት

ማሳሰቢያ፡- ለገጠር እርሻ ኢንቨስትመንት የተለዩ ቦታዎችን በተመለከተ በተለያዩ የወረዳው ቀበሌዎች ውስጥ ሰርቨይ ተደርጎ የተለየ 135 ሄ/ር የወል መሬት በሶማሞ ጫሬ እና በዱቦ አከባቢ እንዲሁም በሂምቤቾ ከተማ ለኢንዱስትሪ ዞን ተካልሎ ከሚገኘው መሬት በተጨማሪ በወረዳዉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽ/ቤት አማካይነት በተፋሰስ ሊለሙ የሚችሉ በተለያዩ ቀበሌዎች ተጠንቶ የተካለለው ለአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ሊውል የሚችል መሆኑን ታሳቢ ሊደረግ ይገባል፡፡

VII. ለኢንቨስትመንት ያለው አመቺነት

7.1 ለግብርና

 • ሰፊ በመስኖ የሚለማ የአርሶ አደር ማሳ እና የወል መሬት መኖሩ፣
 • ዓመታዊ አማካይ የዝናብ መጠን ከፍተኛ መሆኑ፣
 • በወረዳው ውስጥ ዓመቱን ሙሉ የማይደርቁ ወንዞች ማለትም ወይቦ፣ ጋሞ፣ ሻፋ፣ ሶኬ፣ ቁሌ እና ዎተሬ ወንዞች  በመኖራቸው እንዲሁም በተፋሰስ የለሙና የተካለሉ ሰፊ ቦታዎች ያሉት በመሆኑ በንብ ማነብ፣ በበሬ ድለባ፣ በበግ ማሞከት፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት፣ በዘመናዊ እንሰሳት ዕርባታ፣ ለዶሮ ዕርባታ ለማካሄድ ምቹ መሆኗ፣
 • በልማት ሥራ ላይ ለማዋል በቂ የሰው ኃይል /የተማረ እና የጉልበት/ መኖሩ፣
 • በለሙ ተፋሰሶች እና በአርሶ አደር ማሳ የተሻሻለ መኖ፣ ምጥን መኖ፣ የተለያዩ የሰብል ተረፈ ምርቶች፣ የተፈጥሮ ግጦሽ መኖ አቅርቦት መኖሩ፤
 • እንስሳት ዕርባታ እና የዳልጋ ከብት ድለባ ለማካሄድ ከፍተኛ የቀንድ ከብት ክምችት፣ ውኃ እና የግብይት ማዕከላት መኖሩ፤ በዞን አቀፍም ሆነ ሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የገበያ ፍላጎት መኖሩ፣
 • የተሻሻለ የእንስሳት ዝሪያ እየተስፋፋ መሆኑ (በሰው ሰራሽ ዘዴ በማዳቀል)፤
 • ከፍተኛ የሀገረሰብና የተሻሻለ የበግ እና የዶሮ አቅርቦት መኖሩ፤
 • ለንብ አበባ ቀሰማ ምቹ የሆኑ የተፈጥሮ ደኖች፣ በለሙ ተፋሰሶች፣ የፍራፍሬ ዛፎች መኖራቸው፤
 • ከፍተኛ የወተት ምርት፣ የወተት እና ተዋጽኦ ምርት ፍላጎት እንዲሁም የመስሪያ ቦታና የመሠረተ ልማት አቅርቦት መኖሩ ለኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ የተመቻቹ ሁኔታዎች ናቸው፡፡

7.2 ለአግሮ ኢንዱስትሪ

 • ከአርሶ አደሩ የሚገኙትን የግብርና ምርቶችን (በአውትግራውር ከአርሶ አደሩ ጋር ትስስር በመፍጠር) በጥሬ ዕቃነት ተጠቅሞ በማቀነባበር እስከ ውጪ ገበያ ድረስ ለሚያቀርቡ ባለሀብቶች መሬቱ አመቺነት ያለው በመሆኑ ያለውጣውርድ ማግኘት ይቻላል፤
 • ለተለያዩ ፋብሪካዎች በጥሬ ዕቃነት ሊያገለግሉ የሚችሉ የግብርና ምርቶች የሆኑ እንደ አቮካዶ፣ ቡና፣ ቲማቲም፣ ሙዝ፣ ቦሎቄ እና እንስሳት ሀብት በቅርብ መገኘታቸዉ፤
 • የወተት እና የወተት ተዋጽኦ ለማቀነባበር ከፍተኛ የወተት ምርት መኖሩ፣
 • የሥጋ ምርት (የዳልጋ ከብት፣ የዶሮ፣ ወዘተ) ለማቀነባበር የተሻሻሉ ዝሪያ፣ የተዳቀሉ እና የሀገረሰብ ዘር አቅርቦት መኖሩ፣
 • ምጥን የከብቶች መኖ ለማዘጋጀት በቂ የግብዓት አቅርቦት እና ከፍተኛ የምርት ፍላጎት መኖሩ፤ በአሁኑ ወቅት በተፋሰስ በለሙ ቦታዎች በስፋት እየተመረተ በመሆኑ እንዲሁም በቀላሉ ሊለማ የሚችልና በቂ የተዘጋጀ ቦታ መኖሩ፤  

7.3 ለማህበራዊ አገልግሎት

የወረዳው የጤና ሽፋን 81.4% ብቻ መሆኑ በተለይም በላቦራቶሪ እና በግል ፋርማሲ ተቋማት ሽፋን ክፍተት መኖሩን ያሳያል፤

የመዋዕለ ሕጻናት እና የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ተቋማት ብዛት ዝቅተኛ መሆኑ እንዲሁም በከፍተኛ የት/ት ተቋማት ወይም ኮሌጆች በወረዳው ውስጥ ያለመኖር ለግል ባለሀብት በመስኩ መሰማራት አመችነቱን ይጠቁማል፡፡

7.4 ለሆቴል፣ ለሪዞርት፣ ለሎጅ፣ ለመዝነኛ ፓርክ እና ቱሪዝም አገልግሎት

 • በወረዳው ዋና ከተማም ሆነ በሌሎች የማዘጋጃ ቤቶች ውስጥ ደረጃውን የጠበቀ ሆቴል፣ ፔንሲዮን እና የመዝነኛ ማዕከላት ያለመኖሩ በዘርፉ የገበያ ክፍተት መኖሩን ያሳያል፤
 • በቁጥር በዛ ያሉ የቁም ትክል ድንጋይ (በጫማ ሂምቤቾ ቀበሌ፣ ዎርሙማ፣ አቹራ፣ በአፋማ ባንጫ፣ ጋራ ጎዶ እና በግዶ ሆንቦ ቀበሌ) የሚገኙ፣
 • የወይቦ ፏፏቴ (በማጣላ ሂምቤቾ)፣ ሻጳ ፏፏቴ (በጫማ ሂምቤቾ ቀበሌ) እና የአጃንቾ ፏፏቴ (በአቹራ ቀበሌ)፣
 • ባለ 17 ቧንቧ ተፈጥሯዊ ፍል ውኃ (ጣድሳ ቀበሌ እና በወርሙማ ቀበሌ)፣
 • ታሪካዊ የሆኑ ዋሻዎች ለአብነት የጋላቶ ጎንጎሉዋ (በአቹራ አጉማ ቀበሌ)፣
 • የጣልያን ጦር ምሽግ (አፋማ ባንጫ ቀበሌ)፣
 • የወጣግሾ ተፈጥሮ ደን ልማት (42 ሄ/ር የሚሸፍን በአፋማ ጋሮ ቀበሌ)፣ የዳጌቾ ደን/ፓርክ (ጉሩሞ ኮይሻ)፣ ጉቼ ጋሩዋ (በአፋማ ሚኖ) የመሳሰሉት በወረዳው ውስጥ የሚገኝ በመሆናቸው የቱሪስት መስህብነት ደረጃውን የላቀ ያደርጋሉ፡፡     
 • በወረዳው የሚገኙ ሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ የቱሪስት መስህቦች ቁጥር በርካታ በመሆኑ ቱሪስት የመሳብ አቅም ከፍተኛ ስለሆነ እንዲሁም ለዘርፉ ኢንቨስትመንት በቂ የለማ ቦታ የተዘጋጀ በመሆኑ ባለሃብቱ ቢሠማራበት አዋጭ ነዉ፡፡

7.5 ለማዕድን፣ ኢነርጅ እና ለኮንስትራክሽን ዘርፍ

 • ለኮንስትራክሽን የሚያገለግሉ ጥሬ ዕቃዎች በአከባቢዉ መገኘታቸዉ፣ ነጭ ድንጋይ፣ ጥቁር ድንጋይ፣ ሴሌክቲድ ማቴሪያል የመሳሰሉት በከፍተኛ መጠን መኖሩ፤
 • የታሸገ የማዕድን ውኃ ለማምረት በቂ የከርሰ ምድር ውኃ ምንጮች መኖሩ፤

VIII. የኢንቨስትመንት አማራጭ ዕድሎች

8.1 ግብርና ዘርፍ

 • አትክልትና ፍራፍሬ ልማት (ማንጎ፣ አቦካዶ፣ ሙዝ)፣
 • ቅመማ ቅመም (ዝንጅብል፣ ዕርድ፣ ነጭ ሽንኩርት፣ በርበሬ፣ ቃሪያ) ልማት፣
 • የወተትና ሥጋ ከብት ማርባትና የዳልጋ ከብት ማድለብ፣
 • በዶሮ ዕርባታና እንቁላል ምርት፣
 • የእንስሳት መኖ ዘር ማባዛትና ማልማት፣
 • በንብ ማነብ፣ በበግ ማሞከት፣
 • የአገዳ ሰብሎችን ማምረት፣
 • ቡና እና ሌሎች ገበያ ተኮር ምርቶችን ማምረት፣

8.2 በማህበራዊና በአገልግሎት ዘርፍ

 • በሆቴልና ቱሪዝም ከካፌ እስከ ባለኮከብ ሆቴል
 • በትምህርት ዘርፍ ከመዋዕለ ህፃናት እስከ ኮሌጅ፤
 • በጤና ዘርፍ በክሊኒክ፣ ላቦራቶሪ፣ ፋርማሲ፣ በእንስሳት ህክምና ማዕከላት፣
 • ለሎጅ፤ ለሪዞርትና መዝናኛ ማዕከል

8.3 በኢንዱስትሪ ዘርፍ

 የኢንዱስትሪ ፖቴንሻል ሰርቨይ /   / ጥናት መሠረት በከተማው ውስጥ

 • የዝንጅብል እና ዕርድ ምርት ማቀነባባር፣
 • ለምግብና ምግብ ውጤቶች ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣
 • ለሥጋና የሥጋ ውጤቶች ማቀነባበሪያ፣
 • የወተትና የወተት ውጤቶች ማቀነባበሪያ፣
 • ለአትክልትና ፍራፍሬ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣
 • የእንስሳት መኖ ዘር ማባዣ፣ ማቀነባበሪያና ማሸጊያ ፋብሪካ፣
 • የማዕድን ውኃ ማሸጊያ ፋብሪካ፣
 • በቡና መፈልፈያና ማቀነባበሪያ፣ የጎዳሬ ምርት ማቀነባበር፣