አጠቃላይ ገጽታ
የዳሞት ሶሬ ወረዳ ዋና ከተማ ጉኑኖ ከዞኑ ርዕሰ መዲና ሶዶ በስተ-ምዕራብ በ17 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኛና የቆዳ ስፋቱም 180.9 ካሬ ኪሜትር ሲሆን በ18 የገጠር ቀበሌዎች እና በ4 የማዘጋጃ ቤት ከተሞች የተዋቀረ ነው፡፡ በአስተዳደሩ የሚገኙ የኢንቨስትመንት አማራጮች፤ የማዕድን ሀብት ክምችትና የቱሪስት መስህቦች እንደሚከተለዉ ቀርበዋል፡፡
1.1 ከባህር ወለል ከፍታ
ከባህር ወለል በላይ ከ1,500 እስከ 2,500 ሜትር ከፍታ ያላቸው የመሬት ገጾች አሉት፡፡
1.2 የአየር ንብረት
የወረዳው አግሮኢኮሎጂን በተመለከተ 7% ደጋ፤ 87% ወይና ደጋ እና 6% ቆላ ነዉ፡፡ የዓመቱ አማካይ የሙቀት መጠን 17.6--22.5 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ነው፡፡ አማካይ ዓመታዊ የዝናብ መጠን ከ1200 እስከ 1,600 ሚሊ ሜትር ነው፡፡
1.3 ሥነ-ሕዝብ
በ2009 ዓ.ም ከዞኑ ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በተገኘው የስታትስቲክስ መረጃ መሠረት የወረዳው አጠቃላይ የሕዝብ ብዛት 134,804 ሲሆን የሕዝብ ጥግግት 723 በካሬ ኪ/ሜትር ነው፡፡
. የመሠረተ ልማት አቅርቦት ሁኔታ
2.1 መንገድ
ወረዳው ውስጥ 57 ኪ/ሜትር የጠጠር እና 365.5 ኪ/ሜትር ጥሪጊያ መንገዶች ሲኖሩት በአብዘኛው የወረዳው ቀበሌዎች ከዞንና ከክልል ብሎም ወረዳን ከወረዳ እንዲሁም እያንዳንዱን የገጠር ቀበሌም ጭምር በዋናና በውስጥ ለውስጥ መንገዶች እርስ በእርስ የተገናኘ ነው፡፡
2.2 ስልክ፣ ኢንተርኔት እና የፖስታ አገልግሎት
የሞባይልና የመደበኛ ስልክ አገልግሎት፣ እንዲሁም የኢንተርኔት አገልግሎት የሚሰጡ የግል ንግድ ማዕከሎች እየተከፈቱ ይገኛሉ፡፡ አንድ የፖስታ አገልግሎት ሰጪ ተቋም በጉኑኖ ከተማ ይገኛል፡፡
2.3 መብራት
በወረዳው ውስጥ የሚገኙ የከተማ አከባቢዎች 24 ሰዓት የሃይደሮ ኤሌክትሪክ ኃይል መብራት አገልግሎት ያገኛሉ፡፡
2.4 የመጠጥ ውኃ አቅርቦት
የመጠጥ ውኃ አቅርቦትን በተመለከተ በእጅ ፓምፕ የሚሠራ የእጅ ጉድጓድ ( ) 17፣ በእጅ ፓምፕ የሚሠራ ጥልቅ ጉድጓድ ( ) 43፣ ጥልቅ ጉድጓድ ስርጭት ( ) 4፣ የምንጭ ውኃ ስርጭት ( ) 3 እና ምንጭ በቦታው ማጎልበት ( ) 63 ይገኛሉ፡፡ የወረዳው የመጠጥ ውኃ ሽፋን 61.76% ሲሆን በዘርፉ ያለውን ከፍተኛ ችግር ለማቃለል የጥልቅ ጓድጓድ ውኃ አገልግሎት ለመስጠት በተለያዩ ቀበሌዎች መስመር እየተዘረጋ ይገኛል፡፡
2.5 የገንዘብ ተቋማት፡-
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም እንዲሁም ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት እየተከፈቱ ይገኛሉ፡፡
. የማህበራዊ አገልግሎት
3.1 ጤና
3.2 ትምህርት
መዋዕለ ሕጻናት ት/ቤት --------------------------- 2
አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (1-4ኛ ክፍል) -------------- 5
አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (1-8ኛ ክፍል) -------------- 20
ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት (9-10ኛ ክፍል) ------------ 3
መሰናዶ (11-12ኛ ክፍል) --------------------------- 1
. በመስኖ የሚለማ የእርሻ መሬት ሁኔታ
በወረዳው ውስጥ 1 የመስኖ ፕሮጀክት ተግባራዊ በመሆኑ የአከባቢው አርሶ አደር ተጠቃሚ ሲሆን ለአብነት ብተቴ መስኖ በጉሩሞ ላዲሳ ቀበሌ (110 ሄ/ር) አገልግሎት እየሰጠ በመሆኑ ለአከባቢው ማህበረሰብ ምርትና ምርታማነት ከማሳደግ አንጻር አዎንታዊ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛል፡፡ ከዚሁ በተጨማሪ ወረዳው ካለው የከርሰ ምድርና የገጸ ምድር ውኃ አቅርቦት ለአብነት ወንዞች (ታካቻ፣ ማሬ፣ አክሪሳ እና ቁሌ ወንዞች) ከመኖሩ አንጻር እስካሁን በመስኖ የለማው መሬት መጠን በጣም ዝቅተኛ ከመሆኑም ባሻገር ወረዳው ከፍተኛ ለመስኖ አገልግሎት ሊውል የሚችል የውኃ ፖቴንሻል እንዳለ፣ ከፍተኛ የዝናብ መጠን መኖሩ እና ለም ዐፈር መኖሩ ለእርሻ ኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡
. በወረዳው የሚመረቱ ዋና ዋና ምርቶች
5.1 ዓመታዊ ሰብሎች
በቆሎ፣ ጤፍ፣ ማሽላ፣ ስንዴ፣ ቦሎቄ፣ ባቄላ፣ አተር፣ ገብስ፣ የሥራ ሥር ሰብሎች፣ አትክልት (ቀይ ሽንኩርት፣ ቲማትም)፣ ቅመማ ቅመም ምርት (ዝንጅብል፣ ዕርድ)፣
5.2 ቋሚ ሰብሎች
ፍራፍሬ (ሙዝ፣ ማንጎ፣ አቮካዶ፣ ፓፓያ፣ ብርቱካን)፣ እንሰት፣ ቡና፣
. ለኢንቨስትመንት የተዘጋጀ መሬት፡-
ተ.ቁ
ለኢንዱስትሪ
ለንግድ፣ ለአገልግሎት፣ ለሎጅ፣ ለሪል ስቴትና ለሌሎች
ለከተማ ግብርና
ለማህበራዊ አገልግሎት
1
20 ሄ/ር
166 ሄ/ር
110.82 ሄ/ር
24 ሄ/ር
ምንጭ፡- ጉኑኖ ከተማ ማዘጋጃ ቤት እና የወረዳው እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽ/ቤት
ማሳሰቢያ፡- ከወረዳው ከተማ ልማት ጽ/ቤት እና ከጉኑኖ ማዘጋጃ በተገኘው መረጃ መሠረት ከ310 ሄ/ር በላይ መሬት ለተለያዩ አገልግሎቶች በከተማው መሠረታዊ ፕላን መሠረት የተዘጋጀ መሆኑን ታሳቢ ሊደረግ ይገባል፡፡
. ለኢንቨስትመንት ያለው አመቺነት
7.1 ለግብርና
7.2 ለአግሮ ኢንዱስትሪ
7.3 ለማህበራዊ አገልግሎት
የወረዳው የጤና ሽፋን 87% ብቻ መሆኑ በተለይም በላቦራቶሪ እና በግል ፋርማሲ ተቋማት ሽፋን ክፍተት መኖሩን ያሳያል፤
የመዋዕለ ሕጻናት እና የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ተቋማት ብዛት ዝቅተኛ መሆኑ እንዲሁም በከፍተኛ የት/ት ተቋማት ወይም ኮሌጆች በወረዳው ውስጥ ያለመኖር ለግል ባለሀብት በመስኩ መሰማራት አመችነቱን ይጠቁማል፡፡
7.4 ለሆቴል፣ ለሪዞርት፣ ለሎጅ፣ ለመዝነኛ ፓርክ እና ቱሪዝም አገልግሎት
7.5 ለማዕድን፣ ኢነርጅ እና ለኮንስትራክሽን ዘርፍ
. የኢንቨስትመንት አማራጭ ዕድሎች
8.1 ግብርና ዘርፍ
8.2 በማህበራዊና በአገልግሎት ዘርፍ
8.3 በኢንዱስትሪ ዘርፍ፡- የኢንዱስትሪ ፖቴንሻል ሰርቨይ / / ጥናት መሠረት በከተማው ውስጥ
Copyrights 2019. . All Rights Reserved.
Developed by SNNPRS-SITB & SNNPRS-wza