. አጠቃላይ ገጽታ
የወረዳው ዋና ከተማ ሻንቶ ከዞናችን ርዕሰ መዲና ሶዶ በስተሰሜን በ28 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝና የቆዳ ስፋቱም 165 ካሬ ኪ/ሜትር ሲሆን በ22 የገጠር ቀበሌዎች እና በ2 የማዘጋጃ ቤት ከተሞች የተዋቀረ ነው፡፡ በአስተዳደሩ የሚገኙ የኢንቨስትመንት አማራጮች፤ የማዕድን ሀብት ክምችትና የቱሪስት መስህቦች እንደሚከተለዉ ቀርበዋል፡፡
1.1 ከባህር ወለል ከፍታ
ከባህር ወለል በላይ ከ1,500 እስከ 2,000 ሜትር ከፍታ ያላቸው የመሬት ገጾች አሉት፡፡
1.2 የአየር ንብረት
የወረዳው አግሮኢኮሎጂን በተመለከተ 100% ወይና ደጋ ነዉ፡፡ የዓመቱ አማካይ የሙቀት መጠን 17.6--20 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ነው፡፡ አማካይ ዓመታዊ የዝናብ መጠን ከ1000 እስከ 1,400 ሚሊ ሜትር ነው፡፡
1.3 ሥነ-ሕዝብ
በ2009 ዓ.ም ከዞኑ ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በተገኘው የስታትስቲክስ መረጃ መሠረት የወረዳው አጠቃላይ የሕዝብ ብዛት 140,104 ሲሆን የሕዝብ ጥግግት 723 በካሬ ኪ/ሜትር ነው፡፡
. የመሠረተ ልማት አቅርቦት ሁኔታ
2.1 መንገድ
ወረዳው ውስጥ 29 ኪ/ሜትር የጠጠር እና 596.75 ኪ/ሜትር ጥሪጊያ መንገዶች ሲኖሩት በአብዘኛው የወረዳው ቀበሌዎች ከዞንና ከክልል ብሎም ወረዳን ከወረዳ እንዲሁም እያንዳንዱን የገጠር ቀበሌም ጭምር በዋናና በውስጥ ለውስጥ መንገዶች እርስ በእርስ የተገናኘ ነው፡፡
2.2 ስልክ፣ ኢንተርኔት እና የፖስታ አገልግሎት
የሞባይልና የመደበኛ ስልክ አገልግሎት፣ እንዲሁም የኢንተርኔት አገልግሎት የሚሰጡ የግል ንግድ ማዕከላት እየተከፈቱ ይገኛሉ፡፡ አንድ የፖስታ አገልግሎት ሰጪ ተቋም በሻንቶ ከተማ ይገኛል፡፡
2.3 መብራት
በወረዳው ውስጥ የሚገኙ የከተማ አከባቢዎች 24 ሰዓት የሃይደሮ ኤሌክትሪክ ኃይል መብራት አገልግሎት ያገኛሉ፡፡
2.4 የመጠጥ ውኃ አቅርቦት
የመጠጥ ውኃ አቅርቦትን በተመለከተ በእጅ ፓምፕ የሚሠራ የእጅ ጉድጓድ ( ) 35፣ በእጅ ፓምፕ የሚሠራ ጥልቅ ጉድጓድ ( ) 80፣ ጥልቅ ጉድጓድ ስርጭት ( ) 4፣ ምንጭ በቦታው ማጎልበት ( ) 2 ይገኛሉ፡፡ የወረዳው የመጠጥ ውኃ ሽፋን 66.14% ሲሆን በዘርፉ ያለውን ከፍተኛ ችግር ለማቃለል የጥልቅ ጓድጓድ ውኃ አገልግሎት ለመስጠት በተለያዩ ቀበሌዎች መስመር እየተዘረጋ ይገኛል፡፡
2.5 የገንዘብ ተቋማት፡-
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ቪዥን ፈንድ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም፣ ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም እንዲሁም ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት እየተከፈቱ ይገኛሉ፡፡
. የማህበራዊ አገልግሎት
3.1 ጤና
3.2 ትምህርት
መዋዕለ ሕጻናት ት/ቤት --------------------------- 3
አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (1-4ኛ ክፍል) -------------- 1
አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (1-8ኛ ክፍል) -------------- 24
ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት (9-10ኛ ክፍል) ------------ 2
መሰናዶ (11-12ኛ ክፍል) --------------------------- 1
. በመስኖ የሚለማ የእርሻ መሬት ሁኔታ
ወረዳው ካለው የከርሰ ምድርና የገጸ ምድር ውኃ አቅርቦት ለአብነት ወንዞች (ወዴባ፣ ጋሞ፣ እና ማጥኔ ወንዞች) ከመኖሩ አንጻር እስካሁን በመስኖ የለማ መሬት አለ ለማለት የሚያስደፍር ሁኔታ ባይኖርም ወረዳው ከፍተኛ ለመስኖ አገልግሎት ሊውል የሚችልና በቅርብ ጥልቀት የሚገኝ የከርሰ ምድር ውኃ ፖቴንሻል መኖሩ፣ ከፍተኛ የዝናብ መጠን መኖሩ እና ለም ዐፈር መኖሩ ለእርሻ ኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡
. በወረዳው የሚመረቱ ዋና ዋና ምርቶች
5.1 ዓመታዊ ሰብሎች
በቆሎ፣ ጤፍ፣ ማሽላ፣ ስንዴ፣ ቦሎቄ፣ ገብስ፣ የሥራ ሥር ሰብሎች (ድቡልቡል ድንች፣ የወላይታ ድንች፣ ስኳር ድንች፣ ጎዳሬ)፣ አትክልት (ቀይ ሽንኩርት፣ ቲማትም)፣ ቅመማ ቅመም ምርት (በርበሬ)፣ ሸንኮራ አገዳ፣
5.2 ቋሚ ሰብሎች
ፍራፍሬ (ሙዝ፣ ማንጎ፣ አቮካዶ)፣ እንሰት፣ ቡና፣
. ለኢንቨስትመንት የተዘጋጀ መሬት
ተ.ቁ
ለኢንዱስትሪ በሄ/ር
ለንግድ፣ ለአገልግሎት፣ በሄ/ር
ለከተማ ግብርና በሄ/ር
ለማህበራዊ አገልግሎት በሄ/ር
1
50
7.54
29.12
1.83
ምንጭ፡- ሻንቶ ከተማ ማዘጋጃ ቤት እና የወረዳው እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽ/ቤት
ማሳሰቢያ፡- ከወረዳው ከተማ ልማት ጽ/ቤት እና ከሻንቶ ማዘጋጃ ቤት በተገኘው መረጃ መሠረት ከ88 ሄ/ር በላይ መሬት ለተለያዩ አገልግሎቶች በከተማው መሠረታዊ ፕላን መሠረት የተዘጋጀ መሆኑን ታሳቢ ሊደረግ ይገባል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ወረዳው በዞናችንም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ በህዝብ ጥግግት ከፍተኛ በመሆን የመጀመሪያው ደረጃ የያዘ ስለሆነ አርሶ አደሩ ገበያ ተኮር የሆኑ ምርቶች ምርታማነትን በማሳደግና በተፋሰስ የለሙ ቦታዎችን በአግባቡ ለአትክልትና ፍራፍሬ፣ ለንብ ማነብ፣ ለበግ ማሞከት፣ ለእንስሳት ዕርባታና ድለባ፣ እንዲሁም ለኢንዱስትሪ ግብዓት የሚሆኑ ምርቶችን በበቂ ሁኔታ ለማቅረብ ያሉትን ምቹ ሁኔታዎችን መጠቀም ያስፈልጋል፡፡
. ለኢንቨስትመንት ያለው አመቺነት
7.1 ለግብርና
7.2 ለአግሮ ኢንዱስትሪ
7.3 ለማህበራዊ አገልግሎት
የወረዳው የጤና ሽፋን 86% ብቻ መሆኑ በተለይም በላቦራቶሪ እና በግል ፋርማሲ ተቋማት ሽፋን ክፍተት መኖሩን ያሳያል፤
የመዋዕለ ሕጻናት እና የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ተቋማት ብዛት ዝቅተኛ መሆኑ እንዲሁም በከፍተኛ የት/ት ተቋማት ወይም ኮሌጆች በወረዳው ውስጥ ያለመኖር ለግል ባለሀብት በመስኩ መሰማራት አመችነቱን ይጠቁማል፡፡
7.4 ለሆቴል፣ ለሪዞርት፣ ለሎጅ፣ ለመዝነኛ ፓርክ እና ቱሪዝም አገልግሎት
7.5 ለማዕድን፣ ኢነርጅ እና ለኮንስትራክሽን ዘርፍ
. የኢንቨስትመንት አማራጭ ዕድሎች
8.1 ግብርና ዘርፍ
8.2 በማህበራዊና በአገልግሎት ዘርፍ
8.3 በኢንዱስትሪ ዘርፍ
የኢንዱስትሪ ፖቴንሻል ሰርቨይ / / ጥናት መሠረት በከተማው ውስጥ
ብሎኬት እና ሌሎች የግንባታ ዕቃዎችን ማምረት፣
Copyrights 2019. . All Rights Reserved.
Developed by SNNPRS-SITB & SNNPRS-wza