• Call Us
  • +251465512106

ዞናዊ "የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል" በጋራ የመመስረት የህዝበ ውሳኔ ምርጫ ቅስቀሳ መድረክ እየተካሄደ ነው

ዞናዊ "የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል" በጋራ የመመስረት የህዝበ ውሳኔ ምርጫ ቅስቀሳ መድረክ እየተካሄደ ነው

ወላይታ ሶዶ፤ ጥር 16/2015 በወላይታ ዞን ዞናዊ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋራ የመመስረት የህዝበ ውሳኔ ምርጫ ቅስቀሳ መድረክ የፌደራል፣ የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

የደቡብ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተስፋዬ ይገዙ አምስት ዞኖችና ስድስት ልዩ ወረዳዎች በየምክር ቤቶቻቸው የወሰኑት ወሳኔ በማስመልከት የሚደረግ ህዝበ ውሳኔ መሆኑን ገልጸዋል።

የመድረኩ አስፈላጊነት የአመራር ጥበብ ለማጎልበት፣ የአመለካከትና የተግባር አንድነትም በማጠናከር ህዝበ ውሳኔው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሚያስችል ነው።

የሠላም አብሳሪና የምስራች ነጋሪ የሆነችውን ነጭ ርግብ ህዝቡ በመምረጥ አዲሱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን እንዲመሰረቱ ጥሪ ቀርቧል።

በመድረኩ የፌደራል፣ የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የወረዳና ከተማ አስተዳደር አስተባባሪ አካላት ተገኝተዋል።