የህዝበ ውሳኔ ድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ በሠላምና በስኬት እንዲጠናቀቅ ላስቻሉ አካላት እወቅናና ምስጋና ተሰጠ
የወላይታ ዞን አስተዳደር ህዝበ ውሳኔ ድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ በሠላምና በስኬት እንዲጠናቀቅ ላስቻሉ አካላት የእወቅናና ምስጋና ሰጥቷል።
በእውቅናና ምስጋና መርሃግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የደቡብ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ተስፉዬ ይገዙ ብርዱና ፀሐይ ሳይበግረው ከሌሊቱ 11:00 ጀምሮ ተሰልፎ ድምጽ የሰጠውና በሠላም እንዲጠናቀቅ ያደረገው ህዝባችን ትልቅ ክብር ይገበዋል ብለዋል።
በየደረጃው ያለው ፖለቲካ አመራር በተደራጀና በተቀናጀ ሁኔታ በመሰራት በስኬት እንዲጠናቀቅ ያሳየው ትጋትና ቁርጠኝነት የሚመሰገንና የሚደነቅ ነው ያሉት።
በዞናችን ለፀጥታ ስጋት የሚሆኑ ብዙ ችግሮችን በመከላከልና ህዝቡን በማስተባበር የመሩና የተጉ የፀጥታ አካላትን አመስግነዋል።
አያይዘውም አንድም የፀጥታ ችግር ሳይከሰት ህዝበ ውሳኔው የድምጽ አሰጣጥ በስኬት እንዲጠናቀቅ ለፀጥታ ስራ አጋዥ የሆኑ አካላት ያሳዩት ትብብር ምስጋና አቅርበዋል።
ህዝበ ውሳኔው ፍጹም ዲሞክራሲያዊ፣ ፍታሃዊና ተዓሚን እንደሆነ ለህዝቡ ትክክለኛ መረጃን ተደራሽ ያደረጉ የሚዲያ ተቋማትና ባለሙያዎች ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።
ሀሰተኛ መረጃ የሚሰራጩ አንዳንድ ጽንፈኛ ሚዲያዎችና አካላት እውነትኛና ለህዝቡ የሚጠቀሙ መረጃዎችን እንዲሰራጩና ከእነዚህ ሚዲያዎች መማር እንዳለባቸውም ጭምር መክረዋል።
ለነገ የሚበጅ ሰላምና እና ልማት እንዲሁም ለህዝቡ ጥቅም መሰራት ከሁሉም እንደሚጠበቅበትም አስገንዝበዋል።
ከህዝቡ ጋር ተቀራርበንና ተደጋግፈን በመስራት በሌሎች ሥራዎቻችን ላይም ውጤታማ መሆን እንደምንችል የታየበት ታሪካዊ ምርጫ ነው ብለዋል።
የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ በበኩላቸው ህዝበ ውሳኔው በስኬትና በሠላም እንዲጠናቀቅ መላው የዞኑን ህዝብ፣ የፀጥታ አካላት፣ የሚዲያና ሌሎች አካላት እወቅናና ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
አያይዘውም በዞኑ ህዝብ ስምና በአስተዳደር ስም ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።
Copyrights 2019. . All Rights Reserved.
Developed by SNNPRS-SITB & SNNPRS-wza