የወላይታ ዞን ሕዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር መርሃግብር 10ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።
ወላይታ ሶዶ ፣ የካቲት 30/2015 ዓ.ም (ወላይታ ዞን መ/ኮሚዩኒኬሽን ጉ/መምሪያ)
የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ካሰች ኤልያስ ጉባኤ መክፈቻ ሲያደርጉ በዞኑ የተጀመሩ ኦዲት ግኝት ገንዘቦችን የማስመለስ ሥራ ያለበት ደረጃ መገምገሙን ፤ ምክር ቤቶችን የማጠናከር ሥራ መሰራቱ ፤ የተለያዩ በጎ ተግባራት ሥራዎች መከናወናቸዉን፤ ኑሮ ዉድነትን ለመቅረፍ በዋናነት የተያዘዉን የማምረት ሥራ ወጤታማነት ያለበት ደረጃ በዝርዝር መገምገሙን ጠቅሰዉ በምክር ቤቱ የሚደረገው ክትትልና ቁጥጥር ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አንስተዋል።
የዚህ ዙር ምክር ቤት ጉባኤ በሰሜኑ ሀገራችን ክፍል የተጀመረው ጦርነት በሰላም ለመፍታት የተደረገ ስምምነት ወቅት መሆኑ፤ የሶዶ ከተማ ከሌዊ እስኬ ግብርና ኮሌጅ ያለዉ አስፋልት ጥያቄ ምላሽ ያገኘበት ጊዜ የሚደረግ ጉባኤ መሆኑ ልዩ ያደርጋል ብለዋል።
ጉባኤው በሁለት ቀናት ቆይታው የምክር ቤቱ የ2015 ዓ.ም የ6 ወራት አፈፃፀም ፣ የወላይታ ዞን አስተዳደር ምክር ቤት የስድስት ወራት አፈጻጸም ፣ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2015 ዓ.ም የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት አፈጻጸም እና የተለያዩ ሹመቶችን ተወያይቶ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
Copyrights 2019. . All Rights Reserved.
Developed by SNNPRS-SITB & SNNPRS-wza