የምግብ ዓይነቶችና አሠራሮች እንደየአከባቢው ይለያያሉ፡፡ በዚህ ጽሑፍ የወላይታ ብሔር ባህላዊ የምግብ ዓይነቶችና አዘገጃጀቶቹን በአጭሩ ለማስቃኘት ይሞከራል፡፡
ወላይታዎች የሚመገቧቸው የምግብ ዓይነቶች በሁለት ይመደባሉ፡፡ የመጀመሪያውና አብዛኛውን ጊዜ ለእንግዳ፣ ለክብረ በዓላት፣ ለተለያዩ ድግሶች የሚሰናዱ ተወዳጅና የሚጥም ምግብ ወይም በብሔሩ ቋንቋ (ማልኦ ቁማ) ሲሆን ሁለተኛው ዘወትር የሚመገቧቸው እና ከበዓላት ቀን ውጭ በአዘቦት ቀን የሚሆኑ ምግቦችን (ማሱኳ ቁማ) የሚባሉት ናቸው፡፡ እነዚህም የምግብ ዓይነቶች በየክፍላቸው ቀጥለን በዝርዝር እናያቸዋለን፡፡
ተወዳጅና የሚጥም ምግብ "ማልኦ ቁማ" ማለት በወላይታ ለተለያዩ ድግሶች ለሰርግ፣ ለግርዛት፣ ለክብር እንግዳ መቀበያ እና ለክብረ በዓላት ጊዜ የሚሰጥ የምግብ ዓይነቶች ናቸው፡፡
ይህ ተወዳጅና የሚጥም ምግብ የሚሰራው በአከባቢው ከሚገኙ ከተለያዩ ነገሮች ነው፡፡ እነዚህም፡-
የእንስሳት ተዋጽኦች ስንል ለምግብነት የምንጠቀማቸው እንስሳት በሬ፣ በግ፣ ፍየል፣ ዶሮ እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ የነዚህ ተዋጽዎች በሁለት እንከፍላለን፡፡
የሥጋ ተዋጽዎች
የሥጋ ተዋጾዎች አብዛኛውን ጊዜ ሥጋ ብቻውንና ከሌሎች እህሎች ጋራ ተቀላቅሎ ይዘጋጃሉ፡፡ እነዚህም
"ቶልሱዋ" (ጥሬ ሥጋ)፡- ከበሬ ሥጋ ምርጥ ብልቶች "ገዳ፣ ሻኛ"… ተብሎ በመስቀያ ላይ ወይም በብሔሩ ቋንቋ "ኮጫ" ላይ ተሰቅሎ አሊያም እንደ ሁኔታው በሰፌድ፣ በትሪ ሊቀርብ ይችላል፡፡ ከቁርጥ ሥጋ "ቶልሱዋ" ጋር በማባያነት የሚቀርቡት በስሱ የተጋገረ የበቆሎ እና የቆጮ ቂጣና "ዳታ" በርበሬ በሁለት መልክ ተዘጋጅቶ ይቀርባል፡፡ ይህ የሚሰራው አብዛኛውን ጊዜ ለ"ግፋታ" (ዓመት መለወጫ) በዓል ቀንና ለተለያዩ ድግሶች ሊቀርብ ይችላል፡፡ ሌላው ቶልሱዋ ለዘመን መለወጫ ሲቀርብ "ሙቿ፣ ባጭራ" አብሮ ይቀርባል፡፡ እነዚህ ተጨማሪ ምግቦች ለሌላ ድግሶችና ክብረ በዓላት ላያስፈልጉ ይችላሉ፡፡
"ዳታ በርበሬ" በወላይታ በጣም ታዋቂና ለቁርጥ ሥጋ እንደ ማባያነት ተወዳጅ ሆኖ የሚቀርብ ነው፡፡ ዳታ በርበሬ አዘገጃጀቱ በሁለት ዓይነት ነው፡፡ በርበሬው በነጭ ሽንኩርትና ከሌሎች ቅመሞች ጋር ተድጦ ብቻውን ቅቤው በጣም ስለሚጨመርበት በቋንቋው በርበሬ ተብሎ ይዘጋጃል፡፡ ሁለተኛው በርበሬው ላይ ከቅቤ በተጨማሪ "ማንጣ" ወይም ከወተት አንጀት በሚወጣ ፈሳሽ አጣፍጠው የሚሰሩት ነው፡፡ ሁለት ዓይነት የሚዘጋጀው አብዛኛውን ጊዜ ለዓመት መለወጫ "ግፋታ" ጊዜ ነው፡፡
የወተት ተዋጾኦች
የወተት ተዋጾዎች የምንላቸው ትኩስ ወተት፣ አሬራ፣ አይብና ቅቤ ናቸው፡፡ እነዚህንም አብዛኛውን ጊዜ "ለማልኦ ቁማ" ሥራ የምንጠቀማቸው ሲሆን ከዚህ ውስጥ ቅቤ በሁሉም የምግብ ዓይነቶች ውስጥ ይጨመራል፡፡ በዚህ ክፍል ከአይብ የሚሰሩ ምግቦችንና አይነታቸውን በዝርዝር እናያለን፡፡
አይብ ማለት አሬራ ወተት እሳት ዳር ተጥዶ የሚወጣ የምግብ አይነት ነው፡፡ ከአይብ አራት አይነት ምግብ ይሰራበታል፡፡ እነሱም፡-
"ሎጎሙዋ" (አይብ በበሰለ ሥጋ) - የምንለው ከሥጋዎቹ መሀል ምርጥ ቀይ ሥጋ ተመርጦ ይዘለዘልና ይበስላል፡፡ ከበሰለ በኋላ ደቀቅ ተደርጎ ይከተፋል፡፡ ከዚያም ቅቤና ቅመም ተጨምሮ ሥጋው እሳት ላይ ከተንተከተከ በኋላ ወጥቶ አይብ ይጨመርበታል፡፡ ይህ የሚሰራው አብዛኛውን ጊዜ ለሠርግ፣ ለመልስ፣ ለግርዛትና ዘመድ ቤት ለመውሰድ የሚሠራ የምግብ አይነት ነው፡፡
"ጉጉዋ" (አይብ በጥሬ ሥጋና በጥሬ ቅቤ) - ማለት ምርጥ ቀይ ሥጋ በጥሬው በሚገባ ተከትፎ ምንም እሳት ሳይነካው ከአይብ ጋር ይቀላቀላል፤ ቅቤውም በጥሬ ይጨመርበታል፡፤ ይህ የሚሰራው አብዛኛውን ጊዜ ለመድሓኒትነትና ለግንባታ ነው፡፡ ይሀው ምግብ ለብርድ/ውጋት ለሚያማቸውና ለአራስ ሴቶች ይሰራል፡፡
2. የእንሰት ተዋጾዎች
የእንሰት ተዋጾዎች "ማልኦ ቁማ" ወይም ተወዳጅና የሚጥም ምግብ ከሚሰራባቸው ተዋጾዎች አንዱ ነው፡፡ የእንሰት ተዋጾዎች የምንላቸው እንሰቱ ከተፋቀ በኋላ የሚገኙ ናቸው፡፡ እነሱም፡- እትማ፣ ጎዲያ እና ጎላ ናቸው፡፡ ከነዚህ የሚሰሩ የምግብ አይነቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
3.ከተለያዩ የእህል ዘሮች
4. የሥራ ሥር ምግቦች
አብዛኛው ጊዜ የሥራ ሥር ምግቦች ለማሱካ ወይም ዘወትር የሚበሉ ምግቦች ቢሆኑም "ለማልኦ ቁማ" ወይም ለተወዳጅ ምግብነትም የሚያገለግሉ፡፡ እነሱም፡-
2. "ማሱካ ቁማ" (በአዘቦት ቀን የሚዘወተሩ ምግቦች)
"ማሱካ ቁማ" ማለት አብዛኛውን ጊዜ ተዘውትሮ የሚመገቧቸውና የተለመዱ ምግቦች እንደማለት ነው፡፡ እነዚህ "ማሱካ ቁማ" ወይም በአዘቦት ቀን የሚመገቧቸው የዘውትር ምግቦች ሲሆኑ የሚጋገሩ፣ የሚቀቀሉ እና የሚቆሉ ተብሎ በሶስት ከፍለን እናያቸዋልን፡፡
የሚጋገሩ የምንላቸው አብዛኛውን ጊዜ የተለያዩ እህሎች ተፈጭተው የሚጋገሩትን (oyitta) ያጠቃልላል፡፡ የሚቀቀሉ ቦዬ፣ ቦይና፣ ሹካሪያ፣ ድንች፣ ኮካ የመሳሰሉት ሲሆኑ ሶስተኛው ተቆልቶ የሚበሉ ናቸው፡፡ ከጤፍ ውጭ በማንኛውም እህል በጥሬው ተቆልቶ ይበላል፡፡ እነዚህ በአጠቃላይ በማንኛውም ሰው ቤት በአዘቦት ቀን የምናገኛቸው ምግቦች ናቸው፡፡
በአጠቃላይ በወላይታ ባህላዊ የምግብ አይነቶችንና አዘገጃጀቱን ከሞላ ጎደል ለመጥቀስ ተሞክሯል፡፡ ከፍ ብሎ ከተጠቀሱት የምግብ ዓይነቶች በተጨማሪ ሌሎችን የምግብ ዓይነቶች አንዱን የምግብ ዓይነት ከሌላው ጋር በማቀላቀል እጅግ በጣም ብዙ የምግብ አይነቶች ሊሰሩ እንደሚችሉ ለመጠቆም እንወዳለን፡፡
እነዚህ ባህላዊ ምግቦች በኢኮኖሚና በቴክኖሎጂ እድገት ምክንያት እየቀሩ ያሉ የምግብ ዓይነቶች በሳይንሳዊ አመጋገብ ዘዴ በመታገዝ ምርምር ማካሄድና በጽሑፍ በማስቀመጥ ለቀጣይ ትውልድ እንዲተላለፍ ቢደረግ ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለን እናምናለን፡፡
Copyrights 2019. . All Rights Reserved.
Developed by SNNPRS-SITB & SNNPRS-wza