1.5.1 የግብርናና ገጠር ልማት ዘርፍ፡- ይህ ዘርፍ የዞኑን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማፋጠን ወሳኝ ሚና ያለው ሲሆን የገጠር ልማት ፖሊሲና ስትራቴጂን መሠረት በማድረግ በተደረጉት እንቅስቃሴዎች የምግብ ዋስትናን በዘላቂነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ ከዚህም ባሻገር ለአገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ገበያ ጥራ ቸውን የጠበቁ የግብርና ምርቶች እንዲመረቱና የአርሶ አደሩ ኑሮ እንዲሻሻል በማድረግ በባለፉት ዓመት አበረ ች ውጤቶች ሊመዘገቡ ችለዋል፡፡ በዚሁም መሠረት በመሬት አጠቃቀምና በሌሎችም ያለው ሁኔታ እንደሚከተለው ነው፡፡
1.5.1.1. የመሬት አጠቃቀም፡- ዞኑ ካለው የመሬት ሀብት ውስጥ 65% የ ረሰ፣ 5.4% ሊ ረስ የሚችል፣ 7.6% ግጦሸ፣ 11.8% ደን፤ ቁጥቋጦና ጥሻ እንዲሁም 3.5% ለተለያዩ ግልጋሎቶች የሚውል ነው፡፡ የገጠር እርሻ መሬትን ከያዙት አርሶ አደሮች ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል ደረጃ በጥምር እርሻና እርባታ ሥራ የሚተዳደሩ ናቸው፡፡ ወደ 6.7 በመቶ የሚሆነዉ መሬት አገልግሎት የማይሰጥ ነዉ፡፡
1.5.1.2 የመሬት ይዞ ፡- በዞናችን ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ የ2008 ዓ.ም መረጃ መሠረት የአርሶ አደርን የመሬት ይዞታ በአምስት ደረጃ ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡ ይኸውም፡-
1.5.2 የሚመረቱ ዋና ዋና ሰብሎች / ) በዞኑ የሚመረቱ የሰብል ዓይነቶች እንደየአግሮ ኢኮሎጂውና የአየር ንብረት ቀጠናዎቹ ይለያያሉ፡፡
በመሆኑም በዞኑ ጐላ ብለው የሚ ዩት አግሮ ኢኮሎጂዎችና የአየር ንብረቶች በሦስት የተከፈሉ ናቸው፡፡ እነዚህም፡-
በአጠቃላይ ለኤክስፖርት የሚውሉ ሰብሎች ምቹ ሁኔታዎች ቢኖሩም ለሀገር ውስጥና በአለም ገበያ ላይ ተወዳዳሪ ሊያደርጉ የሚችሉ ሰብሎች ለገበያ በማቅረቡ በኩል በተወሰኑ ሰብሎች /ቡና፣ ጥራጥሬ፣ ስንዴ/ ያሉ ቢሆንም ካለን እምቅ ሀብት ( ) አንጻር አጠቃቀም ዝቅተኛ ስለሆነ ከፍተኛ ሥራ ይጠበቃል፡፡
በዞኑ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ሰብሎች በላቀ ደረጃ የሚያመርቱ ወረዳዎችን በስፔሻላይዜሽን ኘሮግራም በማቀፍና ተስማሚ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን በማቅረብ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ጥረት ተደርጓል፡፡ እንደ አካባቢያዊ ተጨባጭ ሁኔታ የተሻለ ውጤት በሚያስገኘው የሰብል ዓይነት ላይ ትኩረት በማድረግ በገበያ ላይ ከፍተኛ ተፈላጊነትና አዋጭ የሆኑና በወጪ ገበያ ላይ ተፈላጊነት ያላቸውንና የውጭ ምንዛሪ የሚያሰገኙ እንዲሁም ለሀገር ውስጥ ገበያና ፋብሪካዎች በጥሬ ዕቃነት ሊውሉ የሚችሉ የሰብል ዓይነቶች እንደ ሥነ-ምህዳር ሁኔታ በተመረጡ ወረዳዎች በመመረት ላይ ይገኛሉ፡፡
1.6. የ ንስሳት ሀብት፡-
የእንስሳት ሀብትን በተመለከተ በልማት አከባቢ ያለው እንቅስቃሴ በአርሶ አደሮች ደረጃ ተወስኖ የሚካሄድና የግጦሽ መሬቱም ለእርሻ አገልግሎት እየዋለ በመሄዱ በእንስሳት እርባታው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ቢያደርስም የዞናችን ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ የ2008 በጀት ዓመት መረጃ መሠረት በዞናችን የተለያዩ የ ንስሳት ዓይነቶች በስፋት እንደሚገኙ መረጃዎች ያመለክ ታሉ ፡፡ የተሰበሰበዉ የዞኑ እንሰሳት ሀብት መረጃ እንደሚያመለክተዉ በዞኑ ዉስጥ 1,218,743 የዳልጋ ከብት፣ 372,157 በግ፣ 288,552 ፍየሎች እና 94,815 የጋማ ከብቶች ይገኛሉ፡፡ ከዶሮም አንጻር በተገለጸዉ ዓመት ከ1 ሚሊዮን በላይ ዶሮዎች እንደሚገኙ መረጃዉ ያመለክታል፡፡ በተጨማሪም ዞኑ ባሉት የ ንስሳት ሀብት /በዓይነት በመጠን/ ለጠቅላላው ክልሉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡
እንስሳት ተዋጽኦ ልማት ዞናችን ሰፊ የእንስሳት ሀብት የሚገኝ በመሆኑና በአገር ውስጥ ታዋቂ የሆኑትን የቦረና ዝሪያ ያላቸውን የዳልጋ ከብቶች እና ከፍተኛ የወተት ምርት የሚሰጡ ሆሊስቴይን፣ ጄርሲ፣ የመሳሰሉትን ከውጭ ሀገር በማስገባት ዝሪያቸውንም በዘመናዊ የሰዉ ሰራሽ ድቀላ ዘዴ በማሻሻል ሰፊ የእርባታ ሥራ ማከናወንና የእንስሳት ተዋጽኦውንም በስፋት ማቀነባበር ይቻላል፡፡ የአካባቢው ሕብረተሰብ ካለው ልምድ፣ ዞናችን ካለው አመቺ የአየር ፀባይና የመኖ አቅርቦት አንፃር ትኩረት ተሰጥቶት ከተሰራ የእንስሳት ተዋጽኦ ምርትን እስከ ውጭ ገበያ ለማቅረብ አስተማማኝ እምቅ ሀብት አለው፡፡
የንብ እርባ ን ሥራ ለማዞሄድ የተሰጠው ትኩረት አነስተኛ ቢሆንም የ ርባ ውን ሥራ ለማዞሄድ አዞባቢዎቹ ከፍተኛ አመቺነት አላቸው፡፡ ይሁንና ከዘርፉ ሊገኝ የሚችለውን ምር ማነት ለማሳደግ የተሻሻሉ አሰራሮችን መጠቀም ወሳኝነት አለው፡፡ በዚሁም መሠረት የአርሶ አደሩን ግንዛቤ የማሳደግ ሥራ በዋነኛነትም የተለያዩ ሥልጠናዎችን በመስጠትና የተሻሻሉ የማንቢያ ዕቃዎችን መጠቀም ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ናቸው፡፡ ይሁንና ባህላዊ የንብ እርባታ በተሻሻለው አረባብ ዘዴ ቢተካና የተሻሻሉ የማር ቀፎዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ለአርሶ አደሩ ቢቀርቡ የማር እና የሰም ምርትን ለማሳደግ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ እንዳለ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በ2008 በጀት ዓመት 7368.89 ኩንታል ማር እና 57.27 ኩንታል የሰም ምርት እንደተገኘ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
1.7 ለገበያ እየቀረቡ ያሉ ምርቶችን በተመለከተ
ዞናችን እስካሁን ለዓለም ገበያ የተለያዩ ምርቶችን እያቀረበ ያለ ሲሆን በዋነኝነት ሊጠቀሱ የሚችሉት፣
ሀ/ በሰብል ልማት፡- አገሪቱ ወደ ዉጭ ከሚትልካቸዉ ሰብሎች ዋነኛዉ የቡና ምርት ሲሆን ይ ም ከአገሪቱ ለዓለም ገበያ ከሚቀርበው ምርት ከ40-45% ይሸፍናል፡፡ ከአቅርቦት አንፃር በተደረገው የልማት እንቅስቃሴ ከፍተኛ መሻሻል የተገኘ ሲሆን ከዚሁ አንፃር በዞናችን በታጠበና በደረቅ መልክ በ2008 ምርት ዘመን 483 812.75 ኩ/ል ቡና ለማምረት ተችሏል፡፡ የተሻሻለ የቡና ዘር ተጠቅሞ ችግኝ ከማፍላት አንጻር በ2007/8 ዓ.ም 17 ሚሊዮን ችግኝ ማፍላት የተቻለ ሲሆን ከዚሁ ዉስጥ ወደ 11.6 ሚሊዮን ተከላ ተካሂዷል፡፡ የቅመማ ቅመም ምርትን በተመለከተ ከ2003-2008 ዓ.ም በአማካይ 98,761.39 ቶን፤ የአገዳና ብርዕ ሰብል ምርት በቶን 127,191 ቶን፤ ጥራጥሬ ምርት 55,310 ቶን፤ ሰሊጥ 20.44 ቶን፤ አትክልት ምርት 18,329.4 ቶን እንዲሁም ፍራፍሬ ምርት 31,990 ቶን ወደ ማዕከላዊ ገበያ ቀርቧል፡፡
ለ/ ከ ንስሳት ተዋጽኦ ውጤቶች አ ያ፡- ከ2003-2008 ዓ.ም ባሉት ዓመት በአማካይ መረጃ መሠረት የሥጋ ምርት 8 330.2 ቶን፤ የማር ምርት 258.23 ቶን፤ የሰም ምርት 40.87 ቶን፤ ዓሳ ምርት 239.45 ቶን፤ ቅቤ ምርት 1 019 ቶን፤ የቁም እንስሳት በቁጥር 467,014 እና በቆዳና ሌጦ ምርት በቁጥር 177 363 ለማዕከላዊ ገበያ ቀርቧል፡፡
1.8. የኤክስቴንሽን አገልግሎት ስርጭትን በተመለከተ፡-
የተሻሻሉ የግብርና ዘዴዎችን ወደ አርሶ አደር በተቀላጠፈ መልኩ ለማሰረጽና ምርትና ምር ማነትን ለማሳደግ እንዲቻል የልማት ሠራተኞች በግብርና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የሰለጠኑ ሲሆን በሥራም ላይ ያሉት ባለሙያዎች በየወቅቱ የተለያዩ ሥልጠናዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም በ2008 መጨረሻ የልማት ሠራተኞች ቁጥር ወደ 1 495 ማድረስ ተችሏል፡፡ በዚ ም መሠረት በ2008 ዓ.ም መረጃ መሠረት የልማት ሠራተኛና የአርሶ አደሮች ጥምር 1፡221 ለማድረስ ተችሏል፡፡
የገበሬ ማሰልጠኛ ማዕከላትን በተመለከተ በ2008 ዓ.ም መረጃ መሠረት 302 የተገነቡ፣ 281 አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ ሲሆን 35 የሚገነቡ፣ በአጠቃላይ በተለያየ ደረጃ ላይ ያሉ 337 የገበሬ ማሰልጠኛ ማዕከላት ይገኛሉ፡፡ በማዕከላቱም 273,980 አርሶ አደሮች ሥልጠና ወስደዋል፡፡
1.9. የግብዓት አቅርቦትና ሥርጭትን በተመለከተ፡-
የምርጥ ዘር አቅርቦትና ስርጭት በ2008 የምርት ዘመን መኸር ወቅት ስንዴ 1,699.5 ኩ/ል፤ ጤፍ 708.77 ኩ/ል፤ ቦሎቄ 2115.6 ኩ/ል፤ ድ/ድንች 375 ኩ/ል እና የጓሮ አትክልት ዘር 546.3 ኪ/ግ ምርጥ ዘር ቀርቧል፡፡
በ2008 በጀት ዓመት በልግ ወቅት በቆሎ 6,366 ኩ/ል፤ ቦሎቄ 2168.8 ኩ/ል፤ ሰሊጥ 62 ኩ/ል፤ ማሽላ 30 ኩ/ል፤ ድ/ድንች 880 ኩ/ል፤ ጎዳሬ 4,000 ኩ/ል፤ ስ/ድንች 16.168 ሚሊዮን ቁርጥራጭ፤ ካሳቫ 1.67 ሚሊዮን ቁርጥራጭ፤ እና የጓሮ የአትክልት ዘር 8,736 ኪ/ግ ምርጥ ዘር ቀርቧል፡፡ ከዚሁም በተጨማሪ የማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጭትን ስንመለከት በ2008 በበልግና የመኸር አዝመራ ወቅት ዳፕና ኤንፕኤስ 198,287 ኩ/ል፤ ዩሪያ 96,617 ኩ/ል መድረሱን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
በልማት አከባቢዎች ያለውን ዘመናዊና የተሻሻሉ የማንቢያ ዕቃዎች ስርጭትን ስንመለከት እስከ ሚያዚያ 2009 ዓ.ም ድረስ በ14ቱ የአስተዳደር መዋቅሮች በአጠቃላይ 47,938 ባህላዊ ቀፎ፣ 6,229 ሽግግር ቀፎ፣ 4,152 ጨፈቃ ቀፎ እና 6,250 ጀርመን ቀፎ በድምሩ 64,568 የንብ ቀፎዎች ስርጭት እንደተከናወነ ከተገኘው መረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡
1.10. የምርትና ምር ማነት የማሣደግ ሂደትን በተመለከተ፡-
የኤክስቴንሽን አሰራሩንም ሆነ ምርትንና ምር ማነትን የማሳደጉን ሂደት ውጤ ማ ለማድረግ ሞዴል አርሶ አደሮች በተወሰኑ የምግብ ሰብሎች የተጀመረው የምር ማነት ማሳደግ ፓ ጅ ወደ ሁሉም አርሶ አደሮች እንዲዳረስ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ሲሆን በ2008 ዓ.ም በዋና ዋና ሰብሎች ዓመ ዊ ምርት በበልግ እርሻ ብቻ ምርቱን 31.468 ሚሊዮን ኩንታል ሊደርስ ችሏል፡፡ የቡና ምርትን ለማሳደግ ከተሰሩት ሥራዎች አንዱ የአዲስ ቡና ተከላን ማካሄድ ሲሆን በ2007/8 የምርት ዘመን 17 ሚሊዮን ችግኞች ፈልተዉ 11.6 ሚሊዮን ተከላ ተካሂዷል፡፡ በአጠቃላይ ምርትና ምር ማነት በአዝርዕት ልማት ማሳደግ እንደተቻለ ከቀረቡ መረጃዎች መረዳት ይቻላል፡፡ ይኸውም በተሟላ በቆሎ ፓ ጅ 50 ኩ/ል በሄ/ር፣ ጤፍ 16 ኩ/ል በሄ/ር፣ ማሽላ 17 ኩ/ል በሄ/ርእ ና ገብስ 17.0 ኩ/ል በሄ/ር ምር ማነ ቸውን ማሳደግ ተችሏል፡፡ የተሻሻሉ የሰብል ዝ ያዎችን አቅርቦት ለማሻሻል በተደረገው እንቅስቃሴ በተካሄዱት የምርምር ሥራዎች የተለያዩ የሰብል ዝ ያዎች ለአርሶ አደሩ እንዲደርሱ ተደርገዋል፡፡ የዶሮ ስጋና የ ንቁላል ምርትን ለማሳደግ በተሰሩት ስራዎችም ምርታማነትን ከፍ ማድረግ ተችሏል፡፡
1.11. የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃን በተመለከተ፡-
ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው የማገዶና የግንባታ ቁሳቁስ ፍላጐት ከሚለማው የደን ሀብት መጠን በላይ በመሆኑ በደን ሀብታችን ላይ እያደረሰ ያለው ጫና ከፍተኛ ነው፡፡ ይህንን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት በ2008 በህብረተሰብ ተሳትፎ 97.7 ሚሊዮን ችግኝ ማፍላት የተቻለ ሲሆን 69.6 ሚሊዮን ችግኞች ተተክለዋል፡፡ ከዚሁ በተጨማሪ በተለያዩ አካባቢዎች ሕብረተሰቡን በማሳተፍ 183.03 ሄ/ር መሬት ላይ የሚገኝ የተፈጥሮ ደን እየተጠበቀ ይገኛል፡፡ ሰዉ ሰራሽ ደን ከመመዝገብና ከመጠበቅ አንጻር 1,962 ሄ/ር ደን እንዲጠበቅ ተደርጓል፡፡
በ2008 ዓ.ም 379 ተፋሰሶች በመለየት 93 415.6 ሄ/ር መሬት ላይ የተለያዩ የአፈርና ውሃ ጥበቃና ደን ልማት ሥራዎች የተካሄዱ ሲሆን ለግብርናው ልማት የበለጠ አስተዋጽኦ ሊሰጡ የሚችሉ መሬቶች እየተጠበቁና እየለሙ ይገኛሉ፡፡ በውሃ ማሰባሰብም ተግባር በአርሶ አደር ቤተሰብ ደረጃና በማህበረሰብ ደረጃ አገልግሎት የሚሰጡ የተለያዩ የውሃ ማሰባሰብ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ በ2008 ዓ.ም መረጃ መሰረት 3 450 የቤተሰብ ገንዳዎች፣ 3 333 አነስተኛ የ ጅ ጉድጓዶች፣ 1 923 የተለያዩ የወንዝ መጥለፍ ሥራዎችና 267 የማህበረሰብ ኩሬ ቁፋሮ ተከናዉነዋል፡፡
ተቁ
የሰብል ዓይነት
የተዘራ መሬት መጠን በሄክታር
የምርት መጠን በኩንታል
ምርታማነት (ኩንታል/ሄክታር)
1
በቆሎ
25629
1673682
65
2
ማሽላ
3507
55235
16
3
ጤፍ
31943
538980
18
4
ስንዴ
7903
376532
48
5
ገብስ
3753
97431
26
6
ቦሎቄ
70146
1907856
27
7
ባቄላ
4875
81048
16.63
8
ሽምብራ
1356
20367
15
9
አተር
3522
58925
10
አኩሪ አተር
226
2644
12
11
ለውዝ
200
25
ቅመማ ቅመም
392
2493
13
ሰሊጥ
2378.25
9799
14
ሥራ ሥር ምርቶች
73061
22193243
304
እንሰት
11560
2057591
178
አትክልት
4284
917456
214
17
ፍራፍሬ
8509
141889
166
ምንጭ፡- የዞኑ እርሻና ተፈ/ሀብት ልማት መምሪያ
1.12 የመስኖ ልማት
የመስኖ ልማት እንቅስቃሴን በተመለከተ ዋነኛ ተግባር የነበረው አነስተኛ ወንዞችን በመጥለፍ ለአርሶ አደሩ ጥቅም የሚሰጡበትን መንገድ ማመቻቸት ነ ፡፡ በዚህም መሰረት በ2008 ዓ.ም መሬት በመስኖ የማልማት አቅም ባላቸው 29 የመስኖ ኘሮጀክቶች ላይ ዝርዝር ጥናቶች በማድረግ 4 986.55 ሄ/ር መሬትን በመስኖ የማልማት፤ ከ55,000 በላይ አባወራዎች ተጠቃሚ ሊያደርጉ ለሚችሉ የመስኖ አዉ ሮች የጥገና ሥራዎች በመከናን ላይ ይገኛል፡፡
1.13 ምግብ ዋስትና ኘሮግራም
በዞኑ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለውን የምግብ ዋስትና ችግር ለማሰወገድ እንዲቻል በፈዴራልና በክልሉ መንግስት የተለያዩ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎችንና ኘሮግራሞች ተዘጋጅተው ተግባራዊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል፡፡
በ2008 በዞኑ ወደ 199,782 የሚጠጋ ሕዝብ ስር ለሰደደ የምግብ ዋስትና ችግር የተጋለጠ በመሆኑ ይህንን ችግር ለዘለቄታው ለማስወገድ እንዲቻል ልማታዊ የሴፍቲኔት ኘሮግራም፣ ቤተሰብን መሰረት ያደረገ የግብርና ምርትና ገቢ ማሻሻያ ኘሮግራም ተዘጋጅቶ ተግባራዊ በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡ በዚሁ መሰረት በ12 ወረዳዎች 199,782 አርሶ አደር አደሮችን በሴፍቲኔት ኘሮግራም የታቀፈ የሴፍቲኔት ኘሮግራም ተጠቃሚዎችን በቤተሰብ ፓኬጅ በማሳተፍ የራሳቸውን የምግብ ዋስትና እንዲያረጋግጡ ለማስቻል ብድር ተሰጥቷቸዋል፡፡
በአጠቃላይ በዞኑ ካሉት ተጨባጭ የችግሮች ስፋት አኳያ የተሰሩት ሥራዎች በቂ ባለመሆናቸው የተጠናከረና የተቀናጀ ሥራ መሥራትን የሚጠይቅ ይሆናል፡፡
1.14 ጤና
የልማት ጥያቄ ሲነሣ በአብዛኛው የማህበራዊና የኢኮኖሚያዊ መሠረተ ልማትን አሻሽሎ ከማቅረብና ሕብረተሰቡ በሰፊው እንዲጠቀም / ንዲገለገል/ ከማድረግ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ከዚሁ አንጻር ለጤና ዘርፍ የሚሰጠው ትኩረት ከሁሉም በላይ ቀዳሚውን ስፍራ ይዞ ይገኛል፡፡ ምክንያቱም ጤንነቱ ያልተጠበቀ ሕዝብ በልማ ዊ እንቅስቃሴ ሊሳተፍ የሚችል ባለመሆኑ ነው፡፡ በአንድ ሕብረተሰብ ውስጥ የጤና አገልግሎት ችግር ወይም በዝቅተኛ ደረጃ ላይ መገኘት ወይም አለመኖር እና ድህነት ቀጥተኛ የሆነ ቁርኝት ያላቸው ክስተቶች ናቸው፡፡
በዞኑ በጤናው አገልግሎት ዘርፍ የሚደረገው እንቅስቃሴ የዘላቂ ልማት ግቦች ከማሳካት አኳያ ቀዳሚ የትኩረት አቅጣጫ የተሰጠው ሲሆን በዚህም አካሄድ አዎን ዊ ለውጥ እንደሚገኝ ይጠበቃል፡፡ ከዚሁ አንጻር በ2008 የዞኑ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መረጃ መሠረት በዞኑ ያለውን የጤና አገልግሎት ተቋማት ስርጭት 7 ሆስፒታሎች /4 የወረዳ ሆስፒታል፣ 1 ማስተማሪያ የመንግስት፤ 1 የግል እና 1 የመያድ/፣ 70 የጤና ጣቢያዎች፣ 361 በላይ የጤና ኬላዎች፣ 14 መካከለኛ ደረጃ ክሊኒኮች (የግል)፣ 160 የመጀመሪያ ደረጃ ክሊኒኮች (የግል) በዞኑ በተለያዩ አካባቢዎች ተሰራጭተው የጤና አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ ሲሆን የዞኑ አማካይ የጤና አገልግሎት ሽፋን 94.65% ነው፡፡
በ2008 ዓ.ም በዞናችን ውስጥ በሚገኙ የጤና ተቋማት የተሰማሩት የጤና ባለሙያዎች ብዛት 1 964 ሲሆኑ ከነዚህም ውስጥ የጠቅላላ ሀኪም ብዛት 108፣ የነርሶች ብዛት 1 171፣ የፋርማሲስት ብዛት 175፣ የጤና መኮንን ብዛት 226፣ የሳኒቴሪያን ብዛት 70 እንዲሁም የላብራቶሪ ቴክኒሻኖች ብዛት 214 ነው፡፡
በተመሣሣይ መልኩ መሠረ ዊ የጤና እንክብካቤን በሕብረተሰቡ ዘንድ እንዲሰረጽ ከማድረግ አኳያ የጤና ኤክስቴንሽን ኘሮግራም ተዘርግቶ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ይገኛል፡፡ በዚህም መሠረት በ2008 ቁጥራቸው ከ837 በላይ የሆኑ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች በየቀበሌያቱ ተመድበው ሥራ እያካሃዱ ይገኛል፡፡ በ2008 ዓ/ም ከጤና አገልግሎት ተቋማትና ከጤና ባለሙያዎች ብዛት አንጻር በዞኑ ያለውን የአገልግሎት ሽፋን በምንመለከትበት ጊዜ የሆስፒ ል አገልግሎት ሽፋን ለ280 915 ሰዎች፣ የጤና ጣቢያ አገልግሎት ሸፋን 28 091 ሰዎች እና የጤና ላ የአገልግሎት ሸፋን 5 477 ሰዎች የደረሰ ሲሆን የጤና ባለሙያዎችና የሕዝብ ብዛት ጥምር ን በተመለከተ አንድ ሀኪም ለ18 207 ሰዎች፣ አንድ የጤና መኮንን ለ8 700፣ አንድ ፋርማሲስት ለ11 236 ሰዎች፣ አንድ ነርስ ለ1 679 ሰዎች፣ አንድ ላብራቶሪ ቴክኒሻን ለ9 188፣ እና አንድ ሳንተሪያን ለ28 091 ሰዎች አገ/ት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
በሌላ በኩል በአሁኑ ጊዜ በዓለም ትልቅ ሥጋት ሆኖ የሚገኘውና በተለይም በሀገራችን ካለው ዝቅተኛ የማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት አንጻር ከፍተኛ ተጽፅኖ እያሳደረ የሚገኘው የኤች.አይ ቪ /ኤድስ ወረረሽኝ ነው፡፡ ይህንን ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ዞኑ ትኩረት ሰጥቶት በየመሥሪያ ቤቶች ሥራውን የሚሰራ መዋቅር እንዲካተት ከማድረግ ጀምሮ የተንቀሳቀስ ያለ ቢሆንም ከችግሩ አሰከፊነትና ስፋት አንጻር ተከታታይና የማያቋርጥ ሥራ የሚጠይቅ ነው፡፡ አሁን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አኳያ በዞኑ የኤች.አይ ቪ/ኤድስን ወረርሽኝ ከመከላከልና ከመቆጣጠር ጋር በተያያዘ የተሰሩ ያሉት ሥራዎች በተመለከተ በሁሉም ጤና ጣቢያዎችና ሆስፒታሎች የደም ምርመራና የምክር አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ተቋቁመው አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ ይሁንና በፀረ ኤች አይ ቪ/ኤድስ መድ ኒት አጠቃቀም ሆነ በደም ምርመራና በምክር አገልግሎት የተጠቃሚው ቁጥር ከችግሩ ስፋት አንጻር በሚ ይበት ጊዜ በጣም ዝቀተኛ በመሆኑ በዚህ ዙሪያ ያለውን የግንዛቤ ጉድለትና ሌሎች አሉ ዊ ተጽዕኖ ያላቸውን አመለካከቶች ለማሻሻል በሁሉም ቦ ና በሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል ተጠናክሮ መከናወን ያለበት ተግባር ነው፡፡
በሌላ በኩል የ ናቶችና ሕጻናት ጤንነት በመንከባከብ እንዲሁም በቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ዘርፍም በዞኑ ኘሮግራሞች ተነድፈው ተግባራዊ እንቅስቃሴ የተደረገ ከመሆኑም ባሻገር በአገልግሎት አሰጣጡም ረገድ ዕድሜያቸው በ2008 የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ተጠቃሚ እናቶች ብዛት 288,914፤ በእናቶችና ህጻናት እንክብካቤ 409 023 እናቶች እንዲሁም በአ ባቢ ንጽህና ዙሪያ 635 030 ሰዎች ግንዛቤ ተፈጥሮላቸዋል፡፡
1.15 ትምህርት
በአንድ ሕብረተሰብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማምጣት ትኩረት ሊሰጣቸው ከሚገባው የማህበራዊ አገልግሎቶች አንዱ የትምህርት ዘርፍ ነው፡፡ የትምህርት አገልግሎት በሕብረተሰብ የኑሮ ሂደት ውስጥ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ሁሉ ተግባራዊ ሊሆን የሚችልና አስተዋጽኦው የዕድገት ለውጥ ማምጣት የሚችል በመሆኑ የአገልግሎቱ አድማስ ሰፊ ነው፡፡ ስለሆነም ከትምህርት አገልግሎት ጋር በተያያዘ በአንድ ሀገር፣ በአንድ ክልል ወይም በአንድ ማሕበረሰብ ውስጥ ያለው ሁኔታ የሚ የው ከስርጭት /ከብዛት/፣ ከትምህርት ደረጃዎች ስብጥርና ከትምህርት ጥራት አኳያ ተነጻ ሮ ሊሆን ይገባል፡፡
በዞኑ የትምህርት አገልግሎትን በተመለከተ ከመረጃዎች ማረጋገጥ እንደሚቻለው በተለያየ ደረጃ የሚገኙ ቁጥራቸው ከ500 በላይ የሚሆኑ የመንግሥትና የግል የትምህርት ተቋማት በ2008 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የትምህርት አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኙ ተመልክቷል፡፡ ከ ነዚህ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች /1-4፣ 5-8፣ 1ኘ8/ ቁጥር 493፣ የ2ኛ ደረጃ /9ኘ10/ ት/ቤቶች 45፣ የመሰናዶ /11-12/ ት/ቤቶች 21፣ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት 4 /ሶዶ ፖሊ፤ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ፤ ቦዲቲ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ እና አረካ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ/ ይገኛሉ፡፡
በየትምህርት ደረጃው የዕድሜ ክልላቸው ለሚፈቅድላቸው ዜጐች የትምህርት አገልግሎት በማዳረስ ረገድ በዞኑ በ2008 ዓ.ም የተመዘገበው የትምህርት ሽፋን እንደሚያመለክተው በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት /ከ1 8/ ጥቅል ተሳትፎ 111.7% ሲሆን በ2ኛ ደረጃ /9 12/ ት/ቤት ደግሞ ጥቅል ተሳትፎ 49.9% ነው፡፡ በተመሣሣይ መልኩ በሴት ተማሪዎች ተሳትፎም እንደዚሁ በአሁኑ ጊዜ በመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት /ከ1ኘ8/ 106% ደርሷል፡፡
ይሁን እንጂ የትምህርት አገልግሎት የሚጠበቅበትን ውጤት ሊያስመዘግብ የሚችለው የትምህርት ቤቶችን ቁጥር በማብዛት ብቻ ሳይሆን በ ትምህርት ቤቶች ትምህርት ጥራትን መሠረት አድርጐ በሚካሄድ የትምህርት አሰጣጥ ስርጭት ሲ ገዝ እንደሆነ የሚ ወቅ ጉዳይ ነው፡፡ በመሆኑም የትምህርት አሰጣጥ ጥራትን ለመፈተሽ ከሚወሰዱት መለኪያ ነጥቦች መካከል የሰለጠኑ የመምህራን ብዛት ስርጭት፣ የተማሪ-አስተማሪ ጥምረት፣ የተማሪ-የመማሪያ ክፍል ጥምረትና የመጻህፍት-ተማሪ ጥምረት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
ከዚህ አንጻር በዞኑ ያለውን ሁኔታ በምንመለከትበት ጊዜ በ2008 ዓ.ም በመጀመሪያ ደረጃ በ1ኛ ሳይክል /1ኘ4/ ት/ቤቶች የተማሪ መምህራን ጥምርታ 1 መምሀር ለ87 ተማሪዎች፣ 2ኛ ሳይክል /5ኘ8/ 1 መምህር ለ44 ተማሪዎች፤ በ2ኛ ደረጃ /9-10/ እና 11-12 ትምህርት ቤቶች እንደ ቅደም ተከተላቸው 1 መምህር ለ37 ተማሪዎች፣ 1 መምህር ለ31 ተማሪዎች ነው፡፡ እንዲሁም የተማሪው ቁጥር ከመማሪያ ክፍሎች ብዛት ጋር ሲነጻጸር በመጀመሪያ ደረጃ በ1ኛ ሳይክል የመማሪያ ክፍል ተማሪዎች ጥምር 1፡82፣ በሁለተኛ ሳይክል 1፡62 እና በሁለተኛ ደረጃ 9-10 ት/ቤቶች 1፡64 ሲሆን በ11-12 ት/ቤቶች 1፡53 ሆኖ በሀገር አቀፍ/በትምህርት ሚ/ር የተቀመጠው ወሰን ወይም ልክ ግን በመጀመሪያ ደረጃ /1-8/ ት/ቤቶች 1 የመማሪያ ክፍል ለ50 ተማሪዎች በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች /9-12/ ደግሞ 1 የመማሪያ ክፍል ለ40 ተማሪዎች ነው፡፡
ስለሆነም በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተቀመጠው የመማሪያ ክፍል ተማሪዎች ጥምር መለኪያ አንጻር በዞኑ ያለው ሁኔታ ከተወሰነው ገደብ በላይ ከ50 እስከ 82 በሚደርስ የተማሪ ቁጥር በአንድ የመማሪያ ክፍል ውስጥ የሚማር በመሆኑ በትምህርት አሰጣጥ ጥራት ላይ የራሱ የሆነ አሉ ዊ ተጽዕኖ ያደርሳል፡፡ በሌላ በኩል የመማሪያ መጻ ፍትን ለተማሪዎች በበቂ ሁኔታ ለማዳረስ ከፍተኛ እንቅስቃሴ በመደረግ ላይ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በሁሉም ደረጃዎች ለሚገኙ ተማሪዎች የመጻህፍት ተማሪ ጥምርታ 1፡1 ደረጃ ላይ ለማድረስ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል፡፡
1.16 መንገድና ትራንስፖርት፡-
በአሁኑ ጊዜ በዞኑ ያለው የመንገድ አገልግሎት ሽፋን ቀደም ሲል ከነበረው የተሻሻለ ቢሆንም ከአገልግሎቱ ወሳኝነት አንጻር ግን ገና በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ነው፡፡ የ2008 ዓ/ም የዞኑ መንገድ ልማትና ትራንስፖርት መምሪያ መረጃዎች እንደሚያረጋግጠው በዞኑ ያለውን የመንገድ ዝርጋታ በየዓይነቱ ስንመለከት አስፋልት መንገድ 189.2 ኪ.ሜ፣ ጠጠር መንገድ 144.5 ኪ.ሜ፣ አፈር መንገድ 7087.8 ኪ.ሜ እና ጥርጊያ መንገድ 2406.37 ኪ.ሜ በጠቅላላው 9494.21 ኪ.ሜትር ርዝመት ያለው መንገድ የሚገኝ መሆኑን መረጃዎች ያመለክ ሉ፡፡
በሌላ በኩል በትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍም በዞኑ የየብስ ትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ አው ሮች ያሉት ሲሆን የየብስ አገልግሎት በተመለከተ ከላይ በዝርዝር በተቀመጡት መንገዶች አማካኝነት አገልግሎቱን በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
1.17 ቴሌኮሙኒ ሽንና ፖስታ አገልግሎት፡-
በቴሌኮሙኒ ሽን አገልግሎት ዘርፍ ባለፉት ዓመታት የ የው ዕድገት በሀገር አቀፍ ደረጃ የጐላ የመሆኑን ያህል በዞኑም በተመሣሣይ መልኩ የቴክኖሎጂ ስርጭት ዕድገት ተጨባጭ ለውጦች ያስመዘገበ መሆኑ ይታመናል፡፡ በዞኑ 15ቱም ከተሞች የአውቶማቲክ ስልክ ተጠቃሚ ሲሆኑ የኢንተርኔት አገልግሎትም እየተስፋፋ ይገኛል፡፡ በፖስታ አገልግሎት ረገድም እንደዚሁ በዞኑ በ2008 ዓ.ም በተለያየ ደረጃ ላይ ያሉ 15 የፖስታ አገልግሎት ማዕከላት ይገኛሉ፡፡
1.18 የመጠጥ ውሃ መስኖና ኢነርጂ አቅርቦት
1.18.1 የመጠጥ ዉሃ
በንጹህ የመጠጥ ውሀ አቅርቦት ዘርፍ በመንግስት ከሚገነቡት የውሃ ተቋማት በተጨማሪ ሕብረተሰቡንና መንግስ ዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በማሳተፍ በፊት ዝቅተኛ የነበረው የዞኑ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋን በ2008 የበጀት ዓመት ወደ 61.72% ላይ ይገኛል፡፡ የመጠጥ ውሃ አቅርቦቱ በከተማና በገጠር ተለይቶ በሚ ይበት ጊዜ ደግሞ በከተማ 59.8% ሲሆን በገጠሩ ክፍል 61.9% ሽፋን እንዳለ መረጃዎች ያረጋግጣሉ፡፡ ከመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋን ጋር በተያያዘ ያለውን ሁኔ ለማሻሻል እስከ 2008 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ የተገነቡትን ተቋማት በተመለከተ ምንጮች በቦ ዉ 330 አገልግሎት የሚሰጡና 28 አገልግሎት የማይሰጡ፣ የ ጅ ውሃ ጉድጓዶች 158 አገልግሎት የሚሰጡና 25 አገልግሎት የማይሰጡ፣ መለሰተኛ የውሃ ጉድጓዶች 294 አገልግሎት የሚሰጡና አገልግሎት የማይሰጡ 47፣ ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች 63 አገልግሎት የሚሰጡና አገልግሎት የማይሰጡ 16 ተገንብተዋል፡፡ ይሁን እንጂ በአያያዝ፣ በአጠቃቀም እንዲሁም ጥገና ላይ የሕብረተሰብ ተሳትፎ ዝቅተኛ በመሆኑና በዚህም የተነሣ ያለው የባለቤትነት ስሜት አናሣ በመሆኑ ከተገነቡት የውሃ ተቋማት መካከል በአማካኝ በ2008 ከ11% በላይ አገልግሎት የማይሰጡ በመሆኑ ይህም በዞኑ የሚደረገውን የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋን የማሻሻል እንቅስቃሴ ላይ አሉ ዊ ተጽዕኖ አሳድ ል፡፡ ስለዚህም ለመጠጥ ውሃ አቅርቦት መሻሻል ከሚደረገው የውሃ ተቋማት ግንባታ ጐን ለጐን የተገነቡት የውሃ ተቋማት በጥንቃቄ ተይዘው የሚጠበቅባቸውን አገልግሎት እንዲሰጡ የማድረግ ሥራ በተጠናከረ መልኩ መሰራት አለበት፡፡
ከመስኖ ተቋማት አንጻር በዞኑ ክረምት ከበጋ ማልማት የሚያስችሉ ወንዞች መኖራቸዉ የሚ ወቅ ሲሆን በሁምቦ 6፤ በሶዶ ዙሪያ 5፤ በቦሎሶ ሶሬ 3፤ በዱጉና ፋንጎ 3፤ በኪንዶ ኮይሻ 3፤ በአጠቃላይ ወደ 29 የሚደርሱ ዘመናዊ የመስኖ ተቋማት ያሉ ሲሆን የከርሰ ምድር ዉሃን በማዉጣት በመስኖ ማምረት የሚቻልባቸዉም አካባቢዎች በስፋት ይገኛሉ፡፡
1.18.2 የኢነርጂ አገልግሎት፡-
በሕብረተሰቡ ውስጥ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴን ለማገዝ ወሳኝ ድርሻ ካላቸው ቅድመ ሁኔ ዎች ወይም አገልግሎቶች መካከል የኢነርጂ / ይል/ አቅርቦት መመቻቸት ዋነኛው ነው፡፡ ኃይል በተለያየ የቴክኖሎጂ ዓይነት የሚመረት እንደመሆኑ አጠቃቀሙ እንደዚሁ ለተለያዩ አገልግሎቶች ነው፡፡
በዚሁ መሰረት ከኤሌክትሪክ፣ ከባዩ ጋዝና ከማገዶ የሚመነጩ ኃይሎችን የዞኑ ሕብረተሰብ ለተለያዩ ተግባራት እየተጠቀመባቸው የሚገኝ ሲሆን የአጠቃቀሙ ሁኔታ ሲ ይ ከዞኑ ዋና አስተዳደር ጽ/ቤት የተገኘዉ መረጃ እንደሚያመለክተዉ 46 የማዘጋጃ ቤት ከተሞች የሀይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልገሎት እንደሚያገኙ እንደ አጠቃላይ 100% የዞኑ ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ናቸው፡፡
1.19 ንግድ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት፡-
በኢንዱስትሪው ክፍለ ኢኮኖሚ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው የምጣኔ ሀብት እድገት ለማምጣት፣ የዞኑን የንግድ፣ የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት ልማቶችን ለማፋጠን፣ ከተሞች ለመኖሪያና ለምጣኔ ሀብት እድገት ምቹ እንዲሆኑ ለማድረግ በንግድ ኢንዱስትሪ እና በከተማ ልማትና ቤቶች ልማት ሴክተር በርካታ እንቅስቃሴዎች ተደርገው አመርቂ ውጤት ተገኝቷል፡፡
በኢንዱስትሪ ልማት በክልሉም ሆነ በዞኑ ያለው ዕድገት በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ነው፡፡ ኢንዱስትሪዎች ከባድና ቀላል ኢንዱስትሪ በሚል በሁለት ምድብ ተከፍለው የሚ ዩ ሲሆን እንደሀገራችን ባሉት ታዳጊ ሀገሮች የሚኖሩት ኢንዱስትሪዎች በአብዛኛው በቀላል ኢንዱስትሪ የሚመደቡ ናቸው፡፡
ከዚህ አንጻር በዞኑ ያሉትን ኢንዱስትሪዎች በተመለከተ የዞኑ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ በ2008 ከተሰበሰበዉ መረጃ ለማረጋገጥ እንደተቻለው በቀላል ኢንዱስትሪዎች የሚመደቡ የብረታ ብረት ሥራ፣ የቡና መፈልፈያ ወይም መቀሸሪያ፣ የ ንጨት ሥራና የንጹህ መጠጥ ዉሃ ማሸጊያ ወዘተ ፋብሪካዎች በዞኑ በተለያዩ ቦ ዎች ይገኛሉ፡፡ ከዞኑ ንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያ የተገኘዉ መረጃ እንደሚያመለክተዉ በ2008 ዓ.ም 6048 አነስተኛ ኢንዱስትሪዎች የነበሩ ሲሆን ከዚሁ ቁጥር ከአራት ሺህ በላይ የሚሆኑት በሶዶ ከተማ ይገኛሉ፡፡
1.20 ቱሪዝም፡-
ዞኑ የተለያየ የአየር ንብረትና የመሬት አቀማመጥ ሥነ ምህዳር ያለው በመሆኑ አካባቢው ለተለያዩ ዓይነት ዕፅዋትና እንስሳት መገኛ ምቹ እንዲሆን አስችሎታል፡፡ ዞኑ ለበርካታ ዕፅዋትና እንስሳት ምቹ የመኖሪያ ዞን ሲሆን ይህም የቱሪዝም ኢንዱስትሪን በዞኑ ለማስፋፋት አመቺ ሁኔ ን ፈጥሯል፡፡ በተመሣሣይ መልኩ ዞኑ በተፈጥሮ ያገኛቸውና ጐብኝን የሚስቡ ሥፍራዎች ያሉት ሲሆን፣ እነዚህ ሥፍራዎች ለመዝናኛነት በጣም ምቹ ከመሆናቸውም ባሻገር በየአካባቢው የሚገኙት ፍል ውሀዎች፣ ቀዝቃዛ ምንጮችና የማዕድን ውሃዎች ለልዩ ልዩ ዓይነት በሽ ዎች በፈውስነት እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡
ሰው ሰራሽ ከሆኑትና ለቱሪስት መስህብነት ሊያገለግሉ ከሚችሉትም ታሪካዊ ቅርሶች መካከል ረጅም ዕድሜ ያስቆጠሩ ሀይማኖ ዊ ገዳማት፣ እንዲሁም ዋሻዎችና የተለያዩ የስዕል ቅርጾች የተቀረጸባቸው ትክል ድንጋዮችና እንጨቶች በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች ይገኛሉ፡፡
በአጠቃላይ ዞኑ ለቱሪዝም ኢንዱስትሪ አመቺ ሊሆኑ የሚችሉ ሀብቶች ያሉት ሲሆን እነዚህን ሀብቶች ከመጠቀም አንጻር የሚገኝበት ደረጃ ግን ወደ ኋላ የቀረ መሆኑን ያለው መረጃ ያመለክ ል፡፡ ከተገኙ መረጃዎች ለማረጋገጥ እንደተቻለው በ2009 ዓ.ም እስከ መጋቢት ወር መጨረሻ ድረስ ዞኑን የጐበኙ ቱሪስቶች ቁጥር 184,098 ሲሆኑ ከ ነዚህ ውስጥ አብዛኛዎቹ ጐብኚዎች 158,234 የሀገር ውስጥ ጐብኚዎች እንደሆኑና የውጭ ሀገር ጐብኚዎች ደግሞ 25,864 /14%/ ብቻ እንደሆኑ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ እንዲሁም ከቱሪስት የገባው ገቢ ብር 26,300,000.00 እንደሆነ ከዞኑ ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሚኒ ሽን ጉዳዮች መምሪያ የተገኙ መረጃዎች ያሳያል፡፡
ሠንጠረዥ 2፡- በዞኑ የአሥር ዓመት የሀገር ዉስጥና የዉጭ ሀገር ቱሪስት ፍሰት መረጃ
ተ/ቁ
ዓመት
የሃገር ዉስጥ ቱሪስት
የዉጭ ሀገር ቱሪስት
የገባ ገቢ
2000
30,878
2,106
1,110,171
2001
42,772
3,301
1,243,043
2002
44,879
3,103
1,458,459
2003
9,141
3,641,634
2004
50,271
11,754
5,692,517
2005
59,923
12,816
9,112,314
2006
80,383
13102
13,403,623
2007
86,530
18211
14,342,813
2008
62,265
39,072
16,144,980.6
2009
158,234
25,864
26,300,000
ምንጭ፡- የዞኑ ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮምኒኬሸን መምሪያ
ከላይ በዝርዝር ለመመልከት እንደተቻለዉ ቱሪስት ፍሰትና የገባ ገቢ ከዓመት ዓመት እያደገ መሆኑን መረጃዉ ያመለክታል፡፡ ይሁንና በጐብኚዎች ቁጥርም ሆነ ገቢን በማሳደግ በኩል መሻሻል እንዳለ ያለው ሁኔታ የሚያመለክት ሲሆን በቱሪዝም ኢንዱስትሪ በኩል ያለውን እምቅ ሀብት ለመጠቀም ዞኑ ምቹ ሁኔ ንዳለው መረዳት ይቻላል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በዞናችን ውስጥ የቱሪስት ቆይታ ጊዜ እንዲራዘም ለማድረግና ለቱሪስቶች በቂ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ዝቅተኛ፣ መካከለኛ እንዲሁም ባለ አንድና ባለሁለት ኮከብ ሆቴሎች በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች ያለመገኘት ችግር በስፋት ይነሳል፡፡
Copyrights 2019. . All Rights Reserved.
Developed by SNNPRS-SITB & SNNPRS-wza