የኦሞ ጊቤ ወንዝ ተፋሰስ በአገሪቱ ደቡባዊ ምዕራብ አካባቢ የሚገኝ ነው፡፡ የተፋሰሱ አጠቃላይ የቆዳ ስፋት 79 000 ሰኩየር ኪ.ሜ ሲሆን በ40 271 ሰሜን እስከ 90 301 ሰሜን ላቲቲዩድና 350 ምስራቅ እስከ 380 ምስራቅ ሎንግቲዩድ መካከል ይገኛል፡፡ የተፋሰሱ አዋሳኞች በምዕራብ ባሮ አኮቦ ወንዝ ተፋሰስ፣ በሰሜን አባይ ወንዝ ተፋሰስ፣ በምሥራቅ የአዋሽ ወንዝ ተፋሰስና ስምጥ ሸለቆ እንዲሁም በደቡብ ንያና ሱዳን ናቸው፡፡ ተፋሰሱ ሁለት ክልሎችን /ኦሮሚያንና ደ/ብ/ብ/ሕ/ክልልን ያቅፋል፡፡ በተፋሰሱ ማስተር ኘላን ጥናት ላይ እንደተመለከተው በተፋሰሱ ዉስጥ የተካተቱ የዞናችን ወረዳዎች መረጃ እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡
ሠንጠረዥ 3፡- በኦሞ ጊቤ ተፋሰስ ውስጥ የሚገኙ ወረዳዎች
ተ.ቁ
ወረÄ
በተፋሰሱ የተካተተው የወረዳ ስፋት በካሬ ኪ/ሜትር
በተፋሰሱ የተካተተው ስፋት በመቶ¾
1
ኦÍ
567
1ዐ;
2
ኪንዶ ኮይሻ
825.6
3
ሶዶ ዙሪÃ
356.93
7;
4
ቦሎሶ ሶÊ
543.5
ድምR
2293.0
- - , 2004
ማሳሰቢያ፡- የተፋሰስ ጥናቱ በክልል በኩል ሲካሄድ የዞናችን አዲስ ወረዳዎች አልተዋቀሩም፤ አሁን ባለዉ አወቃቀር ቦሎሶ ቦምቤና ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳዎች ሙሉ በሙሉ በተፋሰሱ ዉስጥ ናቸዉ፡፡
ኦሞ ጊቤ ተፋሰስን የሚፈጥሩት ከተፋሰሱ ሰሜናዊና ምዕራባዊ ክፍሎች የሚፈሱት የግልገል ጊቤና ጎጀብ ወንዞችና ሌሎችንም አነስተኛ ገባር ወንዞችን በመያዝ ሲሆን የተፋሰሱ መጨረሻ የቱርካና ሐይቅ ነው፡፡ በተፋሰሱ ውስጥ የሚገኙ አብዛኞቹ ወንዞች የዞኖችን፣ የልዩ ወረዳዎችንና የወረዳዎችን አስተዳደራዊ ወሰን ለመለየት ያገለግላሉ፡፡
የተፋሰሱ የመሬት አቀማመጥ በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች የሚከፈል ሲሆን በሰሜናዊ የተፋሰሱ ክፍል የሚገኙ ከፍተኛ ቦ ዎች / / እና በደቡባዊ ክፍል የሚገኙ ዝቅተኛ ቦ ዎች / / ናቸው፡፡ እንደ መሬት አቀማመጡ የአየር ንብረቱም የተለያየ ሲሆን በከፍተኛ ቦ ዎች እርጥበታማ፤ ሞቃትና / / በዝቅተኛ ቦ ዎች ደግሞ ደረቃማ ሞቃት / / የአየር ንብረት ዓይነት የሚስተዋልበት ነው፡፡
የወላይታ ዞን የሚገኘው ከተፋሰሱ ደቡብ ምስራቅ ሲሆን ከኦሞ ጊቤ ተፋሰስ 26ዐዐ ስ የር ኪ/ሜትር ቦታ የሚሸፍን ሲሆን ይህም ከዞኑ የቆዳ ስፋት 58% በተፋሰስ ውስጥ የሚካተት ነው፡፡ በዞን ውስጥ ከሚገኙት 12 ወረዳዎች ውስጥ አምስቱ ኪንዶ ኮይሻ፣ ኦፋ፣ ቦሎሶ ሶሬ፣ ቦሎሶ ቦምቤ እና ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳዎች ሙሉ ለሙሉ በተፋሰሱ ውስጥ ሲገኙ ሶዶ ዙሪያ 7ዐ% በተፋሰስ ውስጥ ይገኛል፡፡ የከፍታ ልዩነቱም ከ5ዐዐ-2958 ሜትር ከባህር ወለል በላይ ነው፡፡
በዞኑ በተፋሰሱ ወረዳዎች የተለያዩ የግብርና ምርቶች የሚመረቱ ሲሆን በዋነኛነት በቆሎ፣ ቦሎቄ፣ እንሰት፣ ጤፍ፣ ስንዴ፣ ማሽላ፣ ዝንጅብል፣ ገብስ፣ የሥራ ሥር ተክሎች፣ የተለያዩ የጥራጥሬ ምርቶች ከቋሚ ተክሎች ቡናና ቅመማ ቅመም፣ እንደሚመረት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በተፋሰሱ የቅመማ ቅመምና የፍራፍሬ ሰብሎችን የምመረት ሲሆን በሌሎች ቆላማ ቦ ዎች ማለትም ቦሎሶ ቦምቤ፣ ኦፋ እና ኪንዶ ኮይሻ ወረዳዎች ጥጥ በስፋት ሊለማባቸው ይችላል፡፡
በተፋሰሱ ውስጥ የኢንዱስትሪ ልማትን ማካሄድ የሚቻል ሲሆን የሶዶ ከተማ ካለው የመሠረተ ልማት አቅርቦት አንፃር በተሻለ ደረጃ ላይ የሚገኝ በመሆኑ አካባቢው ካለውእ ምቅ ሀብት አንፃር የቆዳና ሌጦ፣ የአግሮ ኢንዱስትሪ፣ የኮንስትራክሽን ተቋማት ማቋቋሙ ይቻላል፡፡
በተፋሰሱ በርካታ የኢንዱስትሪና የግንባታ ማዕድናት እንደሚገኙ ታውቋዋል፡፡ በተለይም በኪንዶ ዲዳዬ የድንጋይ ከሰል እንደሚገኙ ታውቋል፡፡
በጊቤ ተፋሰስ ወረዳዎች የተለያዩ የቱሪዝም መስህብነት ያላቸው ሥፍራዎች ያሉ ሲሆን ከ ነዚህም መካከል በሶዶ ዙሪያ ወረዳ ዋሻዎች፣ የዳሞታ ስላሴ ቤተክርስቲያን ገዳም ፀበል፣ በኪንዶ ኮይሻ ወረዳ የተለያዩ ዋሻዎችና የጥን ዊ ንጉሣዊ ቤተሰብ መገልገያ ዕቃዎችና ቅሪተ አካላት፣ በኦፋ ወረዳ ዋሻዎች ትክል ድንጋይ ፏፏቴዎችና የጥንት ነገሥ ት ጌጣጌጥ የሚገኙ ሲሆን ከፍተኛ የቱሪስት መስህብነት ያለው የአጆራ ፏፏቴም በቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ይገኛል፡፡
Copyrights 2019. . All Rights Reserved.
Developed by SNNPRS-SITB & SNNPRS-wza