በስምጥ ሸለቆ ሐይቆች ተፋሰስ ዉስጥ መገኘት እንደ አቅም ስታይ፤
የስምጥ ሸለቆ ሀይቆች ተፋሰስ በኢትዮጵያ የስምጥ ሸለቆ ውስጥ በደቡባዊ ጫፍ ላይ የሚገኝ አካባቢ ነው፡፡ ተፋሰሱ ከሰሜናዊ ምሥራቅ እስከ ደቡብ ምስራቅ ባለው አቀማመጡ ከዝዋይ ሐይቅ በስተሜን ጀምሮ የአብያታ፣ የላንጋኖ፣ የሻላ፣ የአዋሳ፣ የአባያና ጫሞ እንዲሁም የጨው ባህር ሀይቆችን ይዞ እስከ ኬንያ ድንበር የሚደርስ አካባቢ ነው፡፡
የተፋሰስ አካባቢው ከ 8030’ ሰሜን እስከ 400 25’ ሰሜን እንዲሁም ከ 360 30’ ምስራቅ እስከ 39030’ ምሥራቅ የሚገኝ ነው፡፡
የተፋሰሱ ጠቅላላ ስፋት ወደ 53,000 ካሬ ኪ/ሜ የሚደርስ ሲሆን በአጠቃላይ ሀገሪቱ ውስጥ ካሉት ተፋሰሶች በመጠናቸው አነስተኛ ከሆኑት መካከል አንዱ ነው፡፡ ተፋሰሱ ከበስተሰሜን አቅጣጫ ከአዋሽ ተፋሰስ ሲዋሰን፣ በስተምዕራብ ከኦሞ ጊቤ፣ በስተምሥራቅና ሰሜን ምሥራቅ አቅጣጫ ደግሞ ገናሌና ዋቢ ሸበሌ ተፋሰሶች እንደ ቅደም ተከተላቸው ያዋስኑታል፡፡
የስምጥ ሸለቆ ሀይቆች ተፋሰስ በሁለት ዋና ዋና የሀገራችን የአስተዳደር ክልሎች ውስጥ ይገኛል፡፡ በኦሮሚያ ክልላዊ አስተዳደር ውስጥ የሚካተቱት የተፋሰሱ አካባቢዎች ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲና ቦረና ሲሆኑ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ አስተዳደር ውስጥ የሚገኙት የተፋሰሱ አካባቢዎች አስር ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ ሲሆኑ እነዚህም የጋሞጎፋ፣ ጌዲኦ፣ ጉራጌ፣ ሲልጢ፣ ሀዲያ፣ ከምባታና ጣምባሮ፣ ሲዳማ፣ ደቡብ ኦሞ፣ የሰገን አከባቢ ህዝቦች፣ ወላይታ ዞን እና የአላባ ልዩ ወረዳ ናቸው፡፡ በደቡብ ክልል ውስጥ የተፋሰሱ ስፋት 32,826 ካሬ ኪ/ሜ ሲሆን ከተፋሰሱ 62 በመቶና ከክልሉ ቆዳ ስፋት ወደ 30 በመቶ የሚያህል ቦታ ይሸፍናል፡፡
በስምጥ ሸለቆ ሀይቆች ተፋሰስ ውስጥ ከሚገኙት ዞኖች መዞከል አንዱ የወላይታ ዞን ሲሆን በዋነኛነት በሦስት አግሮ ኢኮሎጂ የተከፈለ ነው፡፡ ይኸውም ወይና ደጋ 56% ቆላና ደጋማ አዞባቢዎች 35% እና 9% ከዞኑ አጠቃላይ ስፋት ይሸፍናሉ፡፡ ዞኑ ያለው አጠቃላይ የመሬት ስፋት 447 130 ሄ/ር ሲሆን ከዚህም ውስጥ 202 530 ሄ/ር ወይም 45.3% በተፋሰሱ ክልል ውስጥ ይገኛል፡፡
የመሬት አጠቃቀሙንም በሚመለከት በሰብል የተሸፈነው 103 371 ሄ/ር ወይም 51.04ኀ፣ ለግጦሽ የዋለ 20 820 ሄ/ር ወይም 10.3%፣ ደንና ቁጥቋጦ 34 369 ሄ/ር ወይም 16.97% በቀጣይ ሊለማ የሚችል 18 025.2 ሄ/ር ወይም 8.9ኀ፣ ለ ርሻ ልማት ሊውል የማይችል 9 336.6 ሄ/ር ወይም 4.6ኀ፣ ለሌሎች አገልግሎቶች ሊውል የሚችል 16 607.5 ወይም 8.2% ነው፡፡
ስለዚህም በቀጣይ ከሚደረገው የልማት እንቅስቃሴ አንጻር ሊለማ የሚችለው የመሬት መጠን 8.7% ወይም 22 117 ሄ/ር መሆኑን ያለው መረጃ የሚያመላክት ከመሆኑም ባሻገር በቀጣይ በሚዞሄዱት ጥናቶች ለተለያዩ አገልግሎቶች ሊውል የሚችለው መሬት 16 607.46 ሄ/ር እንዳለ መገንዘብ ይቻላል፡፡
ከላይ እንደተገለጸው ተፋሰሱ የተለያዩ የአግሮ ኢኮሎጂ ያለው እንደመሆኑ የሚመረቱትም የሰብል ዓይነቶች በርዞታ ናቸው፡፡ ከዚሁ መሠረት ከመሬት ስፋት አንጻር ከፍተኛውን ድርሻ ይዘው የሚገኙት ሰብሎች ከአገዳ ሰብሎች፡- በቆሎ፣ ማሽላ፣ ከጥራጥሬ ሰብሎች፡- ቦሎቄ፣ አደንጓሬ ከብርዕ ሰብሎች፡- ጤፍ፣ ገብስ ከሥራ ሥር ሰብሎች፡- ስኳር ድንች፣ ድንች፣ ካሳቫ የሚመረቱ ሲሆን ከ ነዚህ በተጨማሪ ሌሎች ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ሰብሎች ጥጥ፣ሰሊጥ፣ ቦሎቄ፣ ለውዝ፣ ዝንጅብል፣ እርድ እና በርበሬ እንደሚመረቱ ያለው መረጃ ያመላክ ል፡፡
በግብርና ልማቱ ሌላው ትኩረት ተሰጥቶት እየተከናወነ ያለው የ ንስሳት ሀብት ልማት ሲሆን ምር ማነ ቸውን ለማሳደግ የተለያዩ ሥራዎች እየተካሄዱ ይገኛሉ፡፡ በየወረዳው ያለው የ ንስሳት ሀብት በዓይነትም ሆነ በመጠን ከፍተኛ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
ሠንጠረዥ 4፡- የ2008 እንስሳት ሀብት ብዛት በዓይነትና በአስተዳደር እርከን
ተ/ቁ
ወረዳ/ከተማ
ዳልጋ ከብት
በግ
ፍየል
ዶሮ
ፈረስ
አህያ
በቅሎ
1
ቦሎሶ ሶሬ
84,391
57,331
8,396
91,375
732
6,223
366
2
ዳሞት ጋሌ
66,971
33,251
5,771
94,320
794
6,708
436
3
ዳሞት ወይዴ
98,596
27,156
29,099
96,772
720
6,123
360
4
ሁምቦ
150,589
31,873
96,971
131,292
1,161
9,876
580
5
ሶዶ ዙሪያ
128,783
35,290
9,013
86,979
831
7,070
415
6
ኪንዶ ኮይሻ
181,441
12,329
34,053
77,224
994
8,446
497
7
ኦፋ
83,741
45,029
11,964
83,970
619
5,264
309
8
ቦሎሶ ቦምቤ
69,010
26,218
31,768
82,646
4,937
290
9
ዳሞት ሶሬ
61,818
29,002
8,153
71,873
598
5,084
299
10
ኪንዶ ዲዳዬ
82,327
11,314
19,935
60,880
506
4,299
253
11
ዳሞት ፑላሳ
62,494
27,861
196
64,070
500
4,253
250
12
ዱጉና ፋንጎ
96,911
21,073
30,164
73,787
1,028
8,743
514
13
ሶዶ ከተማ
13,734
6,973
1,796
21,378
188
1,597
94
14
አረካ ከተማ
8,261
3,121
1,009
6,233
354
837
15
ቦዲቲ ከተማ
29,676
4,336
264
18,447
661
ጠቅላላ ድምር
1,218,743
372,157
288,552
1,061,246
9,612
80,121
5,082
ምንጭ፡- የዞኑ እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት መምሪያ
በተለይም በሁምቦ ወረዳ ከአባያ ሀይቅ ጋር በተገናኘ ዓሣ ማምረት ይቻላል፡፡ በሀይቁ ውስጥ ወደ 21 የሚጠጉ የተለያዩ የዓሣ ዝርያዎች እንዳሉ የሚገመት ሲሆን ዓመ ዊ የማምረት አቅሙ እስከ 600 ቶን እንደሚደርስ ይገመ ል፡፡ ይሁንና በቀጣይ የሚዞሄዱ ሥራዎች በዋነኛነት በማምረት ላይ ብቻ የሚያተኩሩ ሳይሆን ያለው የዓሣ ምርት በመጠንም ሊያድግ በሚችልበት ሁኔታ ላይ ማተኮር ይኖርባቸዋል፡፡
ዝናብን መሠረት አድርጐ ከሚዞሄደው የሰብል ልማት በተጨማሪ የመስኖ ልማት ለማዞሄድ በተፋሰሱ አመቺ ሁኔታ አለ፡፡ ከብላቴ ወንዝ ጋር በተገናኘ ትላልቅና መዞከለኛ የመስኖ ልማት ሥራዎችን በዱጉና ፋንጎና በሁምቦ ወረዳዎች ማዞሄድ ይቻላል፡፡ ዳሞት ወይዴ ወረዳ የቢሳሬ ወንዝ፤ በሁምቦ ወረዳ የሀመሣ፤ ኤላ እና ላሾ ወንዞችን መዉሰድ ይቻላል፡፡
ሠንጠረዥ 5፡ በስምጥ ሸለቆ ሀይቆች ተፋሰስ ውስጥ የሚገኙ የዞናችን ወረዳዎች
ተ.ቁ
ወረዳ
በተፋሰሱ የተካተቱ ወረዳዎች ስፋት በካ/ኪ/ሜ
በተፋሰሱ የተካተተው በመቶኛ
ሶደ ዙሪያ
152.7
30%
279
68%
654.4
78%
776
100%
ድምር
1862.1
41.6%
ምንጭ፡- የክልሉ የኢንዱስትሪ ፓቴንሽያል ጥናት፣ 1997/98 ዓ.ም
ማሳሰቢያ፡- የተፋሰስ ጥናቱ በክልል በኩል ሲካሄድ አዲስ ወረዳዎች አልተዋቀሩም፤ አሁን ባለዉ አወቃቀር ዱጉና ፋንጎ ወረዳ ሙሉ በሙሉ በተፋሰሱ ዉስጥ ናቸዉ፡፡
በተፋሳሱ ከሚገኙ ወረዳዎች የቱሪዝም ልማት አንጻር በተፋሰሱ በሚገኙ ወረዳዎች ከፍተኛ የሆነ የቱሪስት መስህቦች ያሉት ሲሆን በዳሞት ወይዴ የተፈጥሮ ደን ቦ ዎችና የዱር አራዊት /በኤሎራሽ ቀበሌ/፣ በዱጉና ፋንጎ ብላቴ ወንዝ ዳርቻ ፍል ውሀዎችና ትክል ድንጋይ፣ በሁምቦ ፍል ውሀዎች፣ የማዕድን ውሀዎች በአባያ ሐይቅ ዙሪያ፣ የተለያዩ የአርኪዎሎጂ ቦ ዎች፣ በዳሞት ጋሌ እና ዳሞት ፑላሳ ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ደኖች ፺ዴቻና ሞርጂያ፻፣ የወላይታ ንጉሶች የቀብር ቦታ ከጠላት የመከላከያ ቦ ዎች ይገኛሉ፡፡
Copyrights 2019. . All Rights Reserved.
Developed by SNNPRS-SITB & SNNPRS-wza