• Call Us
  • +251465512106

የሶዶ ከተማ አስተዳደር

አጠቃላይ ገጽታ

  • ወላይታ ሶዶ ከተማ የወላይታ ዞን መዲና ስትሆን ከሀገሪቱ መዲና አዲስ አበባ በሻሽመኔ በኩል በ390 ኪሎ ሜትር እና በቡታጅራ-ሆሳዕና በኩል 329 ኪ/ሜትር ርቀት በደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ ላይ ትገኛለች፡፡ የከተማዋ ይዞታ በአዲሱ መዋቅራዊ ፕላን መሠረት 9,800 ሄ/ር የተከለለ ነዉ፡፡ ጂአግራፊያዊ አቀማመጧ ሲታይ 80 ሰሜን ላቲዲዩድ እና 370 ምሥራቅ ሎንጊቱድ ክልል ዉስጥ ነዉ፡፡ ከተማዋ የሚትገኝበት አማካይ ከፍታ ከባህር ወለል በላይ 2050 ሜትር ነዉ፡፡ የከተማዉ ህዝብ ብዛት 146,490 እንደሚሆን ከዞናችን ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ የተገኘዉ ስታስቲካዊ መረጃ ያመለክታል፡፡
  • የወላይታ ሶዶ ከተማ የአየር ሁኔታ ወደ ወይና ደጋ ያዘለ ነዉ፡፡ በበጋ ወራት በቀኑ ወቅት ለዘጠኝ ሰዓት ያህል እጅግ አስደሳች የሆነ የፀሐይ ሙቀት ያለ ሲሆን በክረምት ወራት በአማካይ ለአራት ሰዓታት ያህል የፀሐይ ሙቀት ታገኛች፡፡ ዓመታዊ አማካይ የሙቀት መጠን 18 ድ.ሴ. ይደረሳል፡፡ ከተማይቱ ከዳሞት ተራራ ግርጌ የምትገኝ በመሆኗ የአየር ሁኔታ በምሽት ብርዳማ ሲሆን በቀን መካከለኛ ሙቀት ያለዉ ነዉ፡፡ ይህም ሁኔታ ለኑሮ እና ለጤና እጅግ ተስማሚ በመሆኑ በብዙዎቹ ለኑሮ ተመረጭ ከተማ ሆና ትታወቃለች፡፡
  • ወላይታ ሶዶ ከተማ በዓመት ሁለት ወቅቶች በበልግና በክረምት ዝናብ ታገኛለች፡፡ የበልግ ዝናብ ከመጋቢት እስከ ግንቦት የሚቆይ ሲሆን የክረምቱ ደግሞ ከሰኔ እስከ መስከረም የሚቆይ ሆኖ መጠኑም በአማካይ 1,800 ሚሊ ሜትር ነዉ፡፡
  • በዚህ መሠረት ከተማችንን ለነዋሪዎችና ለኢንቨስትመንት ምቹ ለማድረግ መንግስት የቀየሳቸዉን ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች መነሻ የከተማችን ምቹ የአየር ሁኔታ በሁሉም አከባቢ የተዘረጋ በቂ መሠረተ ልማት፣ የተለያዩ የትምህርት ተቋማትና የምርምር ማዕከላት፣ የፌዴራል፣ የክልል የዞን የወረዳና የከተማ መንግስታዊ ተቋማት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በሰባት አቅጣጫ የሚያቀቋርጡ ዘላቂ መንገዶች፣ የዉስጥ ለዉስጥ አስፋልት መንገዶች፣ በአምራች ዕድሜ ክልል ዉስጥ የሚገኙ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር (65%)፣ አስተማማኝ ሠላም፣ የፋይናንስና የትራንስፖርት አገልግሎት መስፋፋት፣ ከገጠሩ ጋር ያለዉ ትስስር እንዲሁም ከሌሎች ትላልቅ ኢንዱስትሪዎች ጋር ሊደጋገፋ የሚችሉ በርካታ እንተርፕራይዞች መኖራቸዉና ሰፊ የገበያ ዕድል ለኑሮና ለኢንቨስትመንት ተመራጭ አድርጓታል፡፡
  • ይህም ባለሰባት በር የንግድና አገልግሎት ማዕከል የሆነችው ሶዶ ከተማ በሰላምና ፀጥታ፣ በተስማሚ አየር ንብረት፣ በተማረ የሰው ኃይል እና የጉልበት ሠራተኛ አቅርቦት፣ በህዝብ ብዛት፣ እንዲሁም የተለያዩ የፌዴራል፣ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳ እና የከተማ አስተዳደር መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት መቀመጫ ማዕከል በመሆኗ ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ያደርጋታል፡፡
  • የመሠረተ ልማት አቅርቦት ሁኔታ፤-
  • 2.1 መንገድ
  • አስፋልት 42.2 ኪ/ሜ፣ ጠጠር መንገድ 4.6 ኪ/ሜ፣ ኮብል ስቶን 68.5 ኪ/ሜ፣ የጥርጊያ መንገድ 53.46 ኪ/ሜ፣
  •      2.2 መብራት፡- የከተማዉ 18 ቀበሊያት እስከ 9 ሜጋ ዋት የሚደርስ የ24 ሠዓት የሃይደሮ ኤሌክትሪክ ኃይል መብራት አገልግሎት ያገኛሉ፡፡
  • 2.3 ስልክ፣ ኢንተርኔት እና የፖስታ አገልግሎት
  • በከተማው ማይክሮወቭ፣ የሞባይልና የመደበኛ ስልክ አገልግሎት፣ እንዲሁም የኢንተርኔት አገልግሎት የሚሰጡ በርካታ የግል ድርጅቶች ይገኛሉ፡፡ አንድ ቋሚ የፖስታ አገልግሎት ሰጪ ተቋም በከተማው ይገኛል፡፡
  • 2.4 የፋይናንስ ተቋማት፡-
  • የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (ዲስትሪክት ጽ/ቤት እና 6 ቅርንጫፎች)፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ ዳሸን ባንክ (ተጨማሪ 1 ቅርንጫፍ)፣ ብርሃን ባንክ፣ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ ኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ፣ አዋሽ ባንክ፣ አብሲኒያ ባንክ፣ ወጋገን ባንክ፣ ሕብረት ባንክ፣ አባይ ባንክ፣ ደቡብ ግሎባል ባንክ፣ አንበሳ ባንክ፣ መድን ኢንሹራንስ፣ ንብ ኢንሹራንስ፣ ብርሃን ኢንሹራንስ፣ ኒያላ ኢንሹራንስ፣ ናይል ኢንሹራንስ፣ ናይስ ኢንሹራንስ፣ አንበሳ ኢንሹራንስ፣ ላይፍ ኤንድ ጀኔራል ኢንሹራንስ፣ ሉሲ ኢንሹራንስ፣ አፍሪካ ኢንሹራንስ፣ ቪዥን ፈንድ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም፣ ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም፣ በድምሩ 15 ባንኮች፣ 10 ኢንሹራንስ ተቋማት እና 2 ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡
  •  
  •  
  •  
  • የማህበራዊ አገልግሎት
  • 3.1 ጤና፡- በጤናው አገልግሎት ዘርፍ የሚደረገው እንቅስቃሴ በከተማው ውስጥ ያለው የጤና አገልግሎት ተቋማት ስርጭት በሚታይበት ጊዜ በቁጥር 2 ሆስፒታል፣ 3 ጤና ጣቢያ፣ 14 መካከለኛ ክሊንክ (የግል)፣ 22 የመጀመሪያ ደረጃ ክሊንክ (የግል)፣ 2 ዲያግኖስቲክ ላቦራቶሪ (የግል)፣ 27 መድኃኒት መደብር/ቤት (የግል) እንዲሁም 6 የጤና ኬላዎች በድምሩ ከ73 በላይ የጤና ተቋማት በመንግስትና በግሉ ዘርፍ በስፋት የከተማው ሕብረተሰብ ተጠቃሚ እንዲሆን በመደረጉ የከተማው የጤና አገልግሎት ሽፋን 53.53% ሊደርስ ችሏል፡፡ 
  • 3.2 ትምህርት፡- በከተማው የትምህርት አገልግሎት ስርጭትን በተመለከተ ከመረጃዎች ማረጋገጥ እንደሚቻለው በተለያየ ደረጃ የሚገኙ ቁጥራቸው ከ30 በላይ የሚሆኑ የመንግስትና የግል የትምህርት ተቋማት በአሁኑ ወቅት የትምህርት አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኙ ተመልክቷል፡፡ ከእነዚህም የትምህርት ተቋማት ውስጥ 5 መዋዕለ ህፃናት ት/ቤት፣ 11 አንደኛ ደረጃ ት/ቤት፣ 8 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት፣ 1 ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ 1 የግብርና ኮሌጅ፣ 3 የግል ኮሌጆች፣ እንዲሁም 1 ዩኒቨርሲቲ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኙ ተረጋግጧል፡፡
  • 3.3. ለሆቴልና ቱሪዝም፤- በከተማዉ ደረጃዉን የጠበቁ ሆቴሎች ብዛት በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ የውጭ ሀገርም ይሁን የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች የቱሪስት ቆይታ ጊዜ እንዲራዘም ለማድረግ አልተቻለም፤ በዘርፉ ለመሠማራት ለሚፈልጉ ባለሀብቶች በቂ ቦታ የተዘጋጀ ስላለ ባለሃብቱ ቢሠማራበት አዋጭ ነዉ፡፡
  •   . ዉሃ፤ ማዕድን እና ኢነርጂ፡- ከኤሌክትሪክ፣ ከማገዶ እና ከባዮ ጋዝ የሚመነጩ ኃይሎችን የከተማው ሕብረተሰብ ለተለያዩ ተግባራት እየተጠቀመባቸው ሲሆን የአማራጭ ኃይልን ከማስተዋወቅ አኳያ የባዮ ጋዝ ማመንጫዎች በውስን ደረጃ ተገንብተው አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለኮንስትራክሽን የሚሆን በቂ የአሸዋ፣ ሴለክቲድ ማቴሪያል፣ የድንጋይ ክምችት መኖሩ እንዲሁም ታሽጎ ለመጠጥ አገልግሎት ሊውል የሚችል የከርሰ ምድር ውኃ ክምችት መኖሩ ከተለያዩ የጥናት ሰነዶች ለማወቅ ተችሏል፡፡
  • 4.1 ዉኃ፡ የከተማውን የመጠጥ ውኃ ሽፋንን ከፍ ለማድረግ መንግስት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት እየሠራ ያለ ሲሆን በአሁኑ ወቅት አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ 5 ጥልቅ ውኃ ጉድጓዶች /የኦቶና፣ የቆንቶ 1፣ 2፣ 3፣ 4፣ እና የወወክማ ውኃ ማጠራቀሚያ ታንከር/፣ የዳሞታ ምንጭ፣ በተክለ ሃይማኖት ገዳም አከባቢ እና በቆንቶ የውኃ ጥራት መቆጣጠሪያ ወይም ማከሚያ ተቋም /                / እንዲሁም የዋና መስመር፣ የውስጥ ለውስጥ  መስመር እና የቦኖ ዝርጋታ በከፍተኛ በጀት ተገንብቷል፡፡
  • በተጨማሪም ዘላቂ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ወይም በተለምዶ ሊቂምሴ ውኃ ፕሮጀክት የዋናው ጥልቅ ጉድጓድ ቁፋሮ፣ የምንጭ ግንባታ፣ የሪዘርቮየር /የውኃ ማጠራቀሚያ/ ግንባታ እና የመስመር ዝርጋታም እየተጠናቀቀ መሆኑ በአሁኑ ወቅት 76% የነበረውን የመጠጥ ውኃ አቅርቦትና ተደራሽነት ሽፋንን ከፍ ከማደረጉም በላይ ለኢንቨስተመንት ፍሰት ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ይታመናል፡፡
  •  . ለኢንቨስትመንት የተዘጋጀ መሬት በሄ/ር 
  • ተ.ቁለኢንዱስትሪ ዞን የተዘጋጀ ለማህበራዊ አገልግሎት (ለጤና፣ ለትምህርት)ለንግድና አገልግሎት ለከተማ ግብርና ለአስተዳደራዊ አገልግሎት ለመኖሪያ አገልግሎት 1295 ሄ/ር221 ሄ/ር63 ሄ/ር1874113 ሄ/ር524 ሄ/ርምንጭ፡- ሶዶ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ዋና ሥራ ሂደት
  • ከላይ በሠንጠረዡ ለመመልከት እንደሚቻለው የከተማ ነዋሪዎችም ሆነ የሀገር ዉስጥ እና የዉጭ ሀገር ባለሃብቶች በከተማችን ኢንቨስት ለማድረግ የቦታ ጥያቄ ለሚያቀርቡ ባለሀብቶች የመኖሪያና ኢንቨስትመንት ቦታዎች ከዚህ በፊት በነበረው የከተማው ማስተር ፕላን መሠረት የተዘጋጁ ሲሆን አዲስ ተጠንቶ ተግባራዊ ለማድረግ በዝግጅት ላይ በሚገኘው የከተማው መዋቅራዊ ፕላን መነሻ ከላይ የተጠቀሱ ቦታዎች ስፋት እንደሚጨምርና ማስተካከያ እንደሚደረግ ታሳቢ ተደርጓል፡፡ በዚህም መሠረት መሬት የማቅረብ /ማዘጋጀት/ ሂደት በየዓመቱ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
  • ከዚህም በተጨማሪ በ2007 ዓ.ም አዲስ በተሻሻለው የከተማው መሬት የሊዝ መነሻ ዋጋ (ብር/በካሬ ሜትር) መሠረት ለኢንዱስትሪ፡- ከፍተኛ፡ 66.50፣ ዝቅተኛ፡ 28፣ ለንግድ፡-  ከፍተኛ፡ 580፣ ዝቅተኛ፡ 208 ብር ለማህበራዊ አገልግሎት፡-  ከፍተኛ፡ 342.90፣ ዝቅተኛ፡ 107.20 ብር ሲሆን ለከተማ ግብርና፡- ከፍተኛ፡ 45፣ ዝቅተኛ፡ 36 ብር ብቻ መሆኑ ለልማታዊ ባለሀብቶች መሬት በዝቅተኛ ዋጋ በማቅረብ ለማበረታታት ከሚደረጉ ጥረቶች አንዱ እንደሆነ ለማወቅ ይቻላል፡፡          
  • ስለሆነም ባለሃብቶች በማንፋክቸሪንግ፣ በከተማ ግብርና፣ በሆቴልና ሪልስቴት፣ እንዲሁም በሌሎች ኢንዱስትሪዎች በመረጡት መስክ ኢንቨስት በማድረግ አስተማማኝና ትርፋማ የገበያ ዕድል ተጠቃሚ በመሆንና የሥራ ዕድል ለዜጎች በመፍጠር ለከተማዉ ብሎም ለሀገርቱ ዕድገት ድርሻቸዉን እንዲወጡ የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊዉን ድጋፍ ለማድረግ ምቹ ሁኔታዎች ተፈጥሯል፡፡ 
  •  
  •  
  •   . ለኢንቨስትመንት ያለዉ አመችነት
  • በሰባት አቅጣጫዎች የሚያቋርጡ ከተማዋን ከሌሎች አጎራባች ዞኖችና ከተሞች ጋር የሚያገናኝ ዘላቂ መንገዶች፣ ከተማውን አቋርጦ እስከ ሞያሌ/ኬንያ ድረስ የሚዘረጋው ዘመናዊ የባቡር መስመር፣ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የኤርፖርት ግንባታ ለማካሄድ ጥናቶች መጀመሩ፣ እንዲሁም በከተማው የዉስጥ ለዉስጥ አስፋልት እና ኮብል ስቶን መንገዶች በስፋት እየተገነቡ መገኘታቸው፣
  • በከተማዋ ምቹ አየር ፀባይ መኖሩ፣
  • የመሠረተ ልማት ደረጃዉ አስተማማኝ መሆኑ፣
  • በርካታ የፋይናንስ ተቋማት ዘመናዊ አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸው፤
  • የተለያዩ የትምህርት ተቋማትና ምርምር ማዕከላት መኖራቸዉ፣
  • በአምራች የዕድሜ ክልል ዉስጥ የሚገኝ በቂ የተማረም ሆነ የጉልበት ሠራተኛ ወይም የሰዉ ኃይልና ያልተበረዘ ሥራ ወዳድ የህዝብ ቁጥር (65%) መኖሩ፣
  • አስተማማኝ ሠላም፣ የፋይናንስና የትራስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መስፋፋት፣
  • ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴና የቱሪዝም ፍሰትን የምታስተናግድ መሆኗ፣
  • ምቹ የኢንቨስትመንት ፖሊሲዎችና አዋጆች በመኖሩ ምክንያት በኢንቨስትመንት ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች/ድርጅቶች የተለያዩ ማበረታቻዎች መኖሩ፣
  • የከተማዉን ዳርቻ ተከትሎ ዓመቱን ሙሉ የማይደርቁ ወንዞች ማለትም የካሊቴ ወንዝ፣ የሐማሣ ወንዝ፣ የሊንታላ ወንዝ እና በሽር ወንዝ ያሉት በመሆኑ በንብ ማነብ፣ በበሬ ድለባ፣ በበግ ማሞከት፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት፣ በዘመናዊ እንሰሳት ዕርባታ፣ ለዶሮ ዕርባታ እንዲሁም ዓሳ ዕርባታ በሰው ሰራሽ ኩሬ ለማካሄድ ምቹ መሆኗ፣
  • ለኮንስትራክሽን የሚያገለግሉ ጥሬ ዕቃዎች በአከባቢዉ በበቂ ሁኔታ መገኘታቸዉ፣
  • ለተለያዩ ፋብሪካዎች በጥሬ ዕቃነት ሊያገለግሉ የሚችሉ የግብርና ዉጤቶች የሆኑ እንደ ቦቆሎ፣ ቡና፣ ማንጎ፣ ብርቱካን፣ ቲማቲም እና እንስሳት ሀብት በቅርብ መገኘታቸዉ፤
  • ከዩኒቨርሲቲ፣ ከማረሚያ ተቋም፣ ከሆስፒታሎች፣ ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት፣ እንዲሁም ከተለያዩ ፋብሪካዎች የሚወገዱ ተረፈ ምርቶች ለእንስሳት ዕርባታና ድለባ፣ ለዓሳማ ዕርባታ፣ ለበግ ማሞከት እና ለዶሮ ዕርባታ ምቹ ሁኔታን መፍጠሩ፤
  • ከብላቴ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል፣ ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ፣ ከግብርና ኮሌጅ፣ በዞን ውስጥ ካሉ ከተማ ቄራዎች፣ በዓመት በዓላት ወቅት ከሚሰበሰበው ምርት፣ እንዲሁም ከአጎራባች ወረዳዎች በቂ የቆዳ እና ሌጦ ምርቶችን ለማግኘት ምቹ ሁኔታ መኖሩ፣
  • ከገጠሩ ጋር ያለዉ ትስስር እንዲሁም ከሌሎች ትላልቅ ኢንዱስትሪዎች ጋር ሊደጋገፍ የሚችሉ በርካታ ኢንተርፕራይዞች መኖራቸዉና ሰፊ የገበያ ዕድል መኖሩ ሶዶ ከተማን ለኑሮና ለኢንቨስትመንት ተመራጭ አድርጓታል፡፡
  • የኢንቨስትመንት አማራጭ ዕድሎች
  • 6.1.1 በከተማ ግብርና ዘርፍ
  • አትክልትና ፍራፍሬ ልማት፣
  • የወተትና ሥጋ ከብት ማርባትና ማድለብ፣ በዶሮ ዕርባታ፣ በንብ ማነብ፣ በበግ ማሞከት፣ የሥጋ ምርት ማቀነባበርና ወደ ዉጪ መላክ፣   
  •  በማህበራዊና በአገልግሎት ዘርፍ
  • በትምህርት ዘርፍ ከመዋዕለ ህፃናት እስከ ኮሌጅ፤
  • በጤና ዘርፍ ከክሊኒክ እስከ ሆስፒታል፣
  • በመዝነኛ አገልግሎት ዘርፍ፡- ሲኒማ ቤቶች፣ ፊልምና ቲያትር ቤቶች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ጂም ቤቶች እና ሌሎች፣
  • በሆቴልና ቱሪዝም ከካፌ እስከ ባለኮከብ ሆቴል፤ ለሎጅ፤ ለሪዞርትና መዝናኛ ማዕከል የሚሆኑ ቦታዎች መዘጋጀታቸው እንደ መልካም አጋጣሚ ሊወሰድ ይችላል፡፡
      1. በኢንዱስትሪ ዘርፍ-፡ የኢንዱስትሪ ፖቴንሻል ሰርቨይ /   / ጥናት መሠረት በከተማው ውስጥ፡-
  • ለምግብና ምግብ ውጤቶች፣ ለሥጋና የሥጋ ውጤቶች ማቀነባበሪያ፣
  • የወተትና የወተት ውጤቶች ማቀነባበሪያ፣
  • ለቆዳና ሌጦ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣
  • ለአትክልትና ፍራፍሬ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ (የቲማትም ሣልሣና ድልህ ማምረቻ)፣
  • ለቡና መፈልፈያና ማበጠሪያ እና የተፈጨ ቡና ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣
  • የዱቀት፣ የፓስታ፣ መኮሮኒ እና ተያያዥ ምርቶች ኮምፕለክስ፣
  • የዘይት መጭመቂያ ፋብሪካ፣
  • ለሳሙና፣ ለዴተሪጀንት እና ሌሎች የውቤትና ንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች ፋብሪካ፣
  • ለህንጻ ቁሳቁሶች /ቆርቆሮ፣ ምስማር፣ ሽቦ፣ ብረታብረት፣ ወዘተ/ ማምረቻ ፋብሪካ፣
  • ለጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ፋብሪካ፣
  • ከቃጫ የሸራና ጆኒያ ማምረቻ ፋብሪካ፣
  • የቀለም ማምረቻ ፋብሪካ፣
  • ከተረፈ ምርትና ከተፈጥሮ ሀብት ሙጫ እና ኮላ ማምረቻ ፋብሪካ፣
  • ለቤትና ቢሮ ዕቃዎች ማምረቻ ፋብሪካ፣
  • የሐር ክር /ድርና ማግ/ ማምረቻ ፋብሪካ፣
  • ኦርጋኒክ ማዳበሪያ ፋብሪካ፣
  • ለፐልፕና ወረቀት መምረቻ ፋብሪካ፣
  • የወዳደቁ ወረቀቶችን በጥቅም ላይ ማዋል /               /፣
  • የወዳደቁ ፕላስትኮችን በጥቅም ላይ ማዋል /                       /፣
  • ከካሳቫ፣ ጎዳሬ እና ቦዬ የአልኮልና ስታርች ማምረቻ፣
  • ከስኳር ድንች ስኳር ማምረቻ ፋብሪካ፣
  • ስታርች /                  / ማምረቻ ፋብሪካ፣
  • የበቆሎ ዘይት ማምረቻ ፋብሪካ፣
  • ከቅባት እህሎች /ሰሊጥ፣ ኑግ፣ ለውዝ፣ ወዘተ/ ዘይት ማምረቻ ፋብሪካ፣
  • የአፕል ጁውስና ሽሮፕ ማምረቻ ፋብሪካ፣
  • የቆዳ ጫማ፣ ቀበቶ፣ የእጅና የገንዘብ ቦርሳ ማምረቻ ፋብሪካ፣
  • የብረት ዚፕ /                / ማምረቻ፣
  • በእጅ የሚንቀሳቀሱ የዉሃ ፓምፕ ማምረቻ፣
  • ጂፕሰም /            / ማምረቻ ፋብሪካ፣
  • የትንባሆ ቅጠል ማቀነባበሪያ ማምረቻ ፋብሪካ፣
  • የብርጭቆ ወረቀት ማምረቻ፣
  • የጂንስ እና የተሰፉ የውስጥ ሱሪዎች ማምረቻ ፋብሪካ፣
  • የጥሪኝ ዕርባታና ዝባድ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣
  • የማዕድን ውኃ ማሸጊያ፣
  • የአዝርዕት ዘር ማቀነባበሪያ፣
  • የእንስሳት መኖ ዘር ማባዣ፣ ማቀነባበሪያና ማሸጊያ ፋብሪካ፣
  • ቅመማ ቅመም /ዝንጅብል፣ ዕርድ/ ማቀነባበርና ማሸግ፣
  • የሽፈራው /       / ዘይት ማምረቻ፣
  • የማርና ሰም ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣
  • የወባ መከላከያ ኬምካል ማቀነባበሪያ /                                      /
  • የቀርከሃ ቁሳቁሶች ማምረቻ፣
  • የሴራሚክስ ውጤቶችና የመፀዳጃ ቤት ዕቃዎች ማምረቻ፣

 

 

 

6.1.4 በቱሪዝም ዘርፍ

ለቱሪስት መረጃ ማዕከልነት፣ ለጉዞ ወኪልና መኪና አከራይ አገልግሎት፣ በአስመጭና ላኪነት ለሚሰማሩ ድርጅቶች፣

የዳሞት ተራራ እና የፑንዱኒያ ደን ሀብት ልማት፡- በከተማዋ ሰሜናዊ አቅጣጫ የሚገኘው የዳሞት ተራራ የወላይታ ዞን የከርሰምድርና የገጸምድር የውኃ ምንጭና ታርካዊ ፋይዳ ያላቸው በርካታ ቅርሶችን ያቀፈ ተራራ ከመሆኑም በተጨማሪ የልዩ ልዩ ዕጽዋት ዝርያዎች መገኛና በደን የተከበበ ስለሆነ የአከባቢው አየር ንብረት እንዲስተካከል ከማድረግ ባሻገር ለከተማዋ ግርማ ሞገስ አጎናጽፏታል፡፡ ከዚሁ ተራራ ዙሪያ ከሥሩ የሚነሱ ከ26 በላይ ወንዞች ለአከባቢው ጥቅም ከማዋል አልፎ ለጎረበት ወረዳዎችም ተራራው ጫፍ ወጥቶ አጠቃላይ የከተማዋን ገጽታ ጨምሮ የአባያ ሐይቅ እና ሌሎች አጎራባች ከተሞችን መመልከት በከፍተኛ ርቀት አይሮፕላን ላይ ሆኖ እንደማየት ይቆጠራል፡፡ በመሆኑም በተራራው አናት ላይ በሚገኘው ሜዳ ላይ ደረጃውን የጠበቀ የሆቴል፣ የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ የስልጠና ማዕከላት፣ የዱር አራዊት ፓርክ፣ የገመድ ትራንስፖርት /                             /፣ ወዘተ ጣምራ አገልግሎቶችን ሊሰጥ የሚችል ዘመናዊ ድርጅት ለመስራት ለሚፈልጉ ባለሀብቶች በሀገሪቱ ውስጥ የመጀመሪያ ተወዳዳሪ የማይገኝለት ምርጫቸው ሊሆን ይችላል፡፡

በተጨማሪም የሞቼና ቦራጎ ዋሻ፣ የፑንዱኒያ የባህር ዛፍ ደን ሀብት ልማት እና በዳሞት ተራራ ላይ የሚካሄደው የካርቦን ፕሮጀክት የከተማዋን የቱሪስት መስህብነት ደረጃውን ከፍ ያደርገዋል፡፡