• Call Us
  • +251465512106

የቦዲቲ ከተማ አስተዳደር

  1. አጠቃላይ ገጽታ

የቦዲቲ ከተማ ከዞኑ ርዕሰ መዲና ሶዶ በስተሰሜን በ18 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝና የቆዳ ስፋቱም 2000 ሄ/ር ሲሆን የአየር ንብረቱም 100% ወይና ደጋ ነዉ፡፡ የዓመቱ አማካይ የሙቀት መጠን 17.55 ዲ.ሴ ሲሆን አማካይ የዝናብ መጠን 1201-1600 ሚሊሜትር ይመዘገባል፡፡ በ2009 ዓ.ም የከተማዉ ህዝብ ብዛት 48,018 እንደሚሆን ከዞናችን ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ የተገኘዉ ስታስቲካዊ መረጃ ያመለክታል፡፡

  1. የመሠረተ ልማት አቅርቦት ሁኔታ፤-
    1. መንገድ

አስፋልት 7 ኪ/ሜ፣ ጠጠር መንገድ 9 ኪ/ሜ፣ ኮብል ስቶን 16 ኪ/ሜ፣ በተጨማሪም ክረምት ከበጋ የሚያገኛኝ ውስጥ ለውስጥ የጥርጊያ መንገድ በሰፊው ተሠርቷል፡፡

    1. መብራት፡-

የከተማዉ አራቱም ቀበሊያት 24 ሠዓት የሃይደሮ ኤሌክትሪክ ኃይል መብራት አገልግሎት ያገኛሉ፡፡

    1. ስልክ፣ ኢንተርኔት እና የፖስታ አገልግሎት

ማይክሮወቭ፣ የሞባይልና የመደበኛ ስልክ አገልግሎት፣ እንዲሁም የኢንተርኔት አገልግሎት የሚሰጡ በርካታ የግል ድርጅቶች ይገኛሉ፡፡ አንድ የፖስታ አገልግሎት ሰጪ ተቋም በከተማው ይገኛል፡፡

    1. የገንዘብ ተቋማት፡-

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ ዳሸን ባንክ፣ ብርሃን ባንክ፣ ቪዥን ፈንድ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም፣ ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም እንዲሁም ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት እየተከፈቱ ይገኛሉ፡፡

  1. የማህበራዊ አገልግሎት
    1. ጤና
  • ሆስፒታል -----------------------------------1 /በግንባታ ላይ ያለና ያልተጠናቀቀ/
  • ጤና ጣቢያ -------------------------------- 1
  • ጤና ኬላ ----------------------------------- 4
  • የመጀመሪያ ደረጃ ክሊንክ -----------------12 (የግል)   
  • መድኃኒት ቤት /        / ------------ 1 (የመንግስት)
  • መድኃኒት መደብር ------------------------ 1 (የግል)
  • ላቦራቶሪ ------------------------------------- 2 (1 የመንግስት እና 1 የግል)
  • የጤና ሽፋን ---------------------------------- 83.9%
    1. ትምህርት

መዋዕለ ሕጻናት ት/ቤት -------------------------- 11

አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (1-4ኛ ክፍል) -------------- 1

አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (1-8ኛ ክፍል) -------------- 7

ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት (9-10ኛ ክፍል) ----------- 2

መሰናዶ (11-12ኛ ክፍል) -------------------------- 1

የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋም ---------------- 1

 3.3 ለሆቴልና ቱሪዝም፤-

  • በከተማው ደረጃውን የጠበቀ ሆቴል፣ ፔንሲዮን እና የመዝነኛ ማዕከላት ያለመኖሩ በዘርፉ የገበያ ክፍተት መኖሩን ያሳያል፤
  • በዘርፉ ለመሠማራት በቂ ቦታ የተዘጋጀ ስላለ ባለሃብቱ ቢሠማራበት አዋጭ ነዉ፡፡

3.4 ዉሃ፣ ማዕድን እና ኢነርጂ

  • ታሽጎ ለመጠጥ ውኃ ሊውል የሚችል የማዕድን ወሃ ክምችት መኖሩ፣
  • የመጠጥ ዉሃ ሽፋን 40.17% ብቻ መሆኑ በዘርፉ ሰፊ ሥራ እንደሚጠበቅ ያመላክታል፡፡

  . ለኢንቨስትመንት የተዘጋጀ መሬት

የኢንዱስትሪ ዞን ከአዲስ አበባ ወደ ዞኑ ከተማ ሶዶ አቋርጦ በሚያልፈዉ በዋናዉ አስፋልት መንገድ ዳር ላይ መሠረተ ልማት ተሟልቶለት ተዘጋጅቷል፡፡  

ተ.

ለኢንዱስትሪ ዞን የተዘጋጀ መሬት

ለኮኮብ ሆቴል፣ ለሪል ስቴትና ለሌሎች ማህበራዊ አገልግሎት ተቋሞች የተዘጋጀ መሬት

ለከተማ ግብርና

1

34.8 ሄ/

121.3 ሄ/

109 ሄ/

    ምንጭ፡- ቦዲቲ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ዋና ሥራ ሂደት

 . ለኢንቨስትመንት ያለዉ አመችነት

  • የመሠረተ ልማት አውታሮች ዝርጋታ ያለበት ደረጃ አስተማማኝ መሆኑ፣
  • የሰዉ ኃይልና ገበያ ማግኘት መቻሉ፣
  • ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ የሚካሄድባት ከተማ መሆኗ፣
  • የከተማዉን ዳርቻ ተከትሎ ዓመቱን ሙሉ የማይደርቁ ወንዞች ማለትም የዋላጫ ወንዝ እና ቦሎ ወንዝ ያሉት በመሆኑ በንብ ማነብ፣ በበሬ ድለባ፣ በበግ ማሞከት፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት፣ በዘመናዊ እንሰሳት ዕርባታ እና በዶሮ ዕርባታ ዘርፍ ለመሠማራት ምቹ መሆኗ፣
  • ለኮንስትራክሽን የሚያገለግሉ ጥሬ ዕቃዎች በአከባቢዉ በበቂ ሁኔታ መገኘታቸዉ፣
  • ለተለያዩ ፋብሪካዎች በጥሬ ዕቃነት ሊያገለግሉ የሚችሉ የግብርና ዉጤቶች የሆኑ እንደ ቦቆሎ፣ ቡና፣ አቮካዶ፣ ማንጎ፣ ብርቱካን፣ ቲማቲም እና እንሰሳት ሀብት በቅርብ መገኘታቸዉ፡፡

  . የኢንቨስትመንት አማራጭ ዕድሎች

6.1 በከተማ ግብርና ዘርፍ

  • አትክልትና ፍራፍሬ ልማት፣ የወተትና ሥጋ ከብት ማርባትና ማድለብ፣ በዶሮ ዕርባታ፣ በንብ ማነብ፣ በበግ ማሞከት፣

6.2 በማህበራዊና በአገልግሎት ዘርፍ

  • በትምህርት ዘርፍ ከመዋዕለ ህፃናት እስከ ኮሌጅ፤
  • በጤና ዘርፍ ከክሊኒክ እስከ ሆስፒታል
  • በመዝነኛ አገልግሎት ዘርፍ፡- ሲኒማ ቤቶች፣ ፊልምና ቲያትር ቤቶች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ጂም ቤቶች እና ሌሎች
  • በሆቴልና ቱሪዝም ከካፌ እስከ ባለኮከብ ሆቴል
  • ለሎጅ፤ ለሪዞርትና መዝናኛ ማዕከል ግንባታ የሚሆኑ ቦታዎች መዘጋጀታቸው

6.3 በኢንዱስትሪ ዘርፍ፡- የኢንዱስትሪ ፖቴንሻል ሰርቨይ /   / ጥናት መሠረት በከተማው ውስጥ

  • ለምግብና ምግብ ውጤቶች ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣
  • ለሥጋና የሥጋ ውጤቶች ማቀነባበሪያ፣
  • ለአትክልትና ፍራፍሬ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣
  • ለቡና መፈልፈያና ማበጠሪያ እና የተፈጨ ቡና ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣
  • ለዘይት መጭመቂያ ፋብሪካ፣
  • ለሳሙና፣ ለዴተሪጀንት እና ሌሎች የውቤትና ንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች ፋብሪካ፣
  • ለህንጻ ቁሳቁሶች /ቆርቆሮ፣ ምስማር፣ ሽቦ፣ ብረታብረት፣ ወዘተ/ ማምረቻ ፋብሪካ፣
  • ለቤትና ቢሮ ዕቃዎች ማምረቻ ፋብሪካ፣
  • የሐር ክር /ድርና ማግ/ ማምረቻ ፋብሪካ፣
  • ከስኳር ድንች ስኳር ማምረቻ ፋብሪካ፣ የበቆሎ ዘይት ማምረቻ ፋብሪካ፣
  • የትንባሆ ቅጠል ማቀነባበሪያ ማምረቻ ፋብሪካ፣