• Call Us
  • +251465512106

የአረካ ከተማ አስተዳደር

 . አጠቃላይ ገጽታ

የአረካ ከተማ ከዞኑ ርዕሰ መዲና ሶዶ በስተሰሜን ምዕራብ በ29 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝና የቆዳ ስፋቱም 3,524 ሄክታር ሲሆን የአየር ንብረቱም 100% ወይና ደጋ ነዉ፡፡ የዓመቱ አማካይ የሙቀት መጠን 20 ዲ.ሴ. ሲሆን፣ አማካይ የዝናብ መጠን 1,400 ሚሊ ሜትር ይመዘገባል፡፡ በ2009 ዓ.ም የከተማዉ ህዝብ ብዛት 61,850 እንደሚሆን ከዞናችን ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ የተገኘዉ ስታስቲካዊ መረጃ ያመለክታል፡፡

  . የመሠረተ ልማት አቅርቦት ሁኔታ፤-

2.1 መንገድ

አስፋልት 7.5 ኪ/ሜ፣ ጠጠር መንገድ 5.98 ኪ/ሜ፣ ኮብል ስቶን 18.2 ኪ/ሜ፣ የጥርጊያ መንገድ 53.46 ኪ/ሜ

2.2 መብራት፡-

የከተማዉ አራቱም ቀበሌያት 24 ሰዓት የሃይደሮ ኤሌክትሪክ ኃይል መብራት አገልግሎት ያገኛሉ፡፡

2.3 ስልክ፣ ኢንተርኔት እና የፖስታ አገልግሎት

ማይክሮወቭ፣ የሞባይልና የመደበኛ ስልክ አገልግሎት፣ እንዲሁም የኢንተርኔት አገልግሎት የሚሰጡ በርካታ የግል ድርጅቶች ይገኛሉ፡፡ አንድ የፖስታ አገልግሎት ሰጪ ተቋም በከተማው ይገኛል፡፡

2.4 የገንዘብ ተቋማት፡-

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ ዳሸን ባንክ፣ ብርሃን ባንክ፣ ቪዥን ፈንድ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም፣ ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም እንዲሁም ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት እየተከፈቱ ይገኛሉ፡፡

   . የማህበራዊ አገልግሎት

3.1 ጤና

  • ሆስፒታል ---------------------------------1 (የመያድ)
  • ጤና ጣቢያ ----------------------------- 1
  • ጤና ኬላ -------------------------------- 0
  • የመጀመሪያ ደረጃ ክሊንክ -------------12 (የግል)   
  • መድኃኒት ቤት /        / --------- 2 (1 የመንግስት እና 1 የግል)
  • መድኃኒት መደብር ---------------------- 4 (የግል)
  • ላቦራቶሪ ----------------------------------- 6 (የመንግስት)
  • የጤና ሽፋን ------------------------------- 33.7%

3.2 ትምህርት ፡-

መዋዕለ ሕጻናት ት/ቤት -------------------------- 8

አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (1-4ኛ ክፍል) -------------- 3

አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (1-8ኛ ክፍል) -------------- 8

ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት (9-10ኛ ክፍል) ----------- 3

መሰናዶ (11-12ኛ ክፍል) -------------------------- 2

የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋም ---------------- 1

3.3 ለሆቴልና ቱሪዝም፤-

  • በከተማዉ ደረጃዉን የጠበቀ ባለ ኮኮብ ሆቴል፣ ፔንሲዮን፣ ሬስቶራንት ያለመኖር
  • በዘርፉ ለመሠማራት በቂ ቦታ የተዘጋጀ ስላለ ባለሃብቱ ቢሠማራበት አዋጭ ነዉ፡፡

3.4 ማዕድን፡-

  • ለኮንስትራክሽን የሚሆን በቂ የአሸዋ ክምችት መኖሩ፣
  • የማዕድን ወሃ ክምችት መኖሩ፣

3.5 የመጠጥ ውኃ፡- የመጠጥ ዉሃ ሽፋን፡ 22.8%

  . ለኢንቨስትመንት የተዘጋጀ መሬት፡-

የኢንዱስትሪ ዞን ከአዲስ አበባ ወደ ዞኑ ከተማ ሶዶ አቋርጦ በሚያልፈዉ በዋናዉ አስፋልት መንገድ ዳር ላይ መሠረተ ልማት ተሟልቶለት ተዘጋጅቷል፡፡  

የከተማ መሬት

ተ.

ለኢንዱስተሪ ዞን የተዘጋጀ መሬት

ለኮኮብ ሆቴል፣ ለሪል ስቴትና ለሌሎች አገልግሎት ተቋሞች የተዘጋጀ መሬት

ለከተማ ግብርና

1

100 ሄ/

387.64 ሄ/

572 ሄ/

  ምንጭ፡- አረካ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ዋና ሥራ ሂደት

 . ለኢንቨስትመንት ያለዉ አመችነት

  • የመሠረተ ልማት ደረጃዉ አስተማማኝ መሆኑ፣
  • የሰዉ ኃይልና ገበያ ማግኘት መቻሉ፣
  • ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ የሚካሄድባት ከተማ መሆኗ፣
  • የከተማዉን ዳርቻ ተከትሎ ዓመቱን ሙሉ የማይደርቁ ወንዞች ማለትም የወይቦ ወንዝ እና ቁሌ ወንዝ ያሉት በመሆኑ በንብ ማነብ፣ በበሬ ድለባ፣ በበግ ማሞከት፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት፣ በዘመናዊ እንሰሳት ዕርባታ እና በዶሮ ዕርባታ ዘርፍ  ለመሠማራት ምቹ መሆኗ፣
  • ለኮንስትራክሽን የሚያገለግሉ ጥሬ ዕቃዎች በአከባቢዉ በበቂ ሁኔታ መገኘታቸዉ፣
  • ለተለያዩ ፋብሪካዎች በጥሬ ዕቃነት ሊያገለግሉ የሚችሉ የግብርና ዉጤቶች የሆኑ አንደ ቦቆሎ፣ ቡና፣ አቮካዶ፣ ማንጎ፣ ብርቱካን፣ ቲማቲም እና እንሰሳት ሀብት በቅርብ መገኘታቸዉ፡፡

  . የኢንቨስትመንት አማራጭ ዕድሎች

6.1 በከተማ ግብርና ዘርፍ

  • አትክልትና ፍራፍሬ ልማት፣ የወተትና ሥጋ ከብት ማርባትና ማድለብ፣ በዶሮ እርባታ፣ በንብ ማነብ፣ በበግ ማሞከት፣

6.2 በማህበራዊና በአገልግሎት ዘርፍ

  • በትምህርት ዘርፍ ከመዋዕለ ህፃናት እስከ ኮሌጅ፤
  • በጤና ዘርፍ ከክሊኒክ እስከ ሆስፒታል
  • በመዝነኛ አገልግሎት ዘርፍ፡- ሲኒማ ቤቶች፣ ፊልምና ቲያትር ቤቶች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ጂም ቤቶች እና ሌሎች
  • በሆቴልና ቱሪዝም ከካፌ እስከ ባለኮከብ ሆቴል ግንባታ፣
  • ለሎጅ፤ ለሪዞርትና መዝናኛ ማዕከል ግንባታ፣

6.3 በኢንዱስትሪ ዘርፍ-፡ የኢንዱስትሪ ፖቴንሻል ሰርቨይ /   / ጥናት መሠረት በከተማው ውስጥ፡-

  • ለምግብና ምግብ ውጤቶች ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣
  • ለሥጋና ሥጋ ውጤቶች ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣
  • ለምግብና ምግብ ውጤቶች ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣
  • ለሳሙናና ሌሎች የውቤትና ንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች ፋብሪካ፣
  • ለህንጻ ግንባታ ዕቃዎች ማምረቻ ፋብሪካ፣
  • ለአትክልትና ፍራፍሬ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣
  • ለቡና መፈልፈያና ማበጠሪያ እና የተፈጨ ቡና ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣
  • ለቤትና ቢሮ ዕቃዎች ማምረቻ ፋብሪካ፣
  • የሐር ክር /ድርና ማግ/ ማምረቻ ፋብሪካ፣
  • ለቅመማ ቅመም (ዝንጅብል፣ ዕርድ) ማቀነባበሪያ፣
  • ከካሳቫ፣ ጎዳሬ እና ሀረግ ቦዬ የአልኮልና ስታርች ማምረቻ፣
  • የፍራፍሬ እና የአትክልት ዘር ማቀነባበሪያ፣
  • የደረቅ አትክልትና ፋራፍሬ ማሸጊያ፣
  • የመኖ ዘር ማባዣ፣ ማቀነባበሪያና ማሸጊያ፣
  • የቡና ገለፈትና ገለባ ማቀነባበሪያ፣