• Call Us
  • +251465512106

በሁምቦ ወረዳ አስተዳደር

በሁምቦ ወረዳ አስተዳደር

 . አጠቃላይ ገጽታ

የሁምቦ ወረዳ ዋና ከተማ ጠበላ ከዞኑ ርዕሰ መዲና ሶዶ በስተደቡብ በ18 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝና የቆዳ ስፋቱም 859.4 ካሬ ኪ.ሜትር ሲሆን በ45 የገጠር ቀበሌዎች እና በ6 የማዘጋጃ ቤት ከተሞች (ጠበላ፣ ሆብቻ፣ ፋራቾ፣ አባያ፣ ጉሪቾ፣ ቆሊሾቦ፣ እና ጉቱቶ ማዘጋጃ ቤት) የተዋቀረ ነው፡፡

1.1 ከባህር ወለል ከፍታ

ከባህር ወለል በላይ ከ1,001 እስከ 2,500 ሜትር ከፍታ ያላቸው የመሬት ገጾች አሉት፡፡

1.2 የአየር ንብረት

የወረዳው አግሮኢኮሎጂን በተመለከተ 30% ወይና ደጋ እና 70% ቆላ ነዉ፡፡ የዓመቱ አማካይ የሙቀት መጠን 12.6--20 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ነው፡፡ አማካይ ዓመታዊ የዝናብ መጠን ከ1,000 እስከ 1,600 ሚሊ ሜትር ነው፡፡

1.3 ሥነ-ሕዝብ

በ2009 ዓ.ም ከዞኑ ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በተገኘው የስታትስቲክስ መረጃ መሠረት የወረዳው አጠቃላይ የሕዝብ ብዛት 167,099 ሲሆን የሕዝብ ጥግግት 189 በስኳየር ኪ/ሜትር ነው፡፡

  . መሠረተ ልማት አቅርቦት ሁኔታ

2.1 መንገድ

የወረዳውን ዋና ከተማ ጠበላ ከአዲስ አበባ-ሶዶ-አርባምንጭ አቋርጦ የሚያልፍ 36.5 ኪ.ሜትር አስፋልት የተዘረጋ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ 204 ኪ/ሜትር የጠጠር እና 696 ኪ/ሜትር ጥሪጊያ መንገድ የተለያዩ የወረዳ ቀበሌዎችን እና አጎራባች ወረዳዎችን እርስ በርስ የሚያገናኝ መንገዶች አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡   

2.2 ስልክ፣ ኢንተርኔት እና የፖስታ አገልግሎት

ማይክሮወቭ፣ የሞባይልና የመደበኛ ስልክ አገልግሎት፣ እንዲሁም የኢንተርኔት አገልግሎት የሚሰጡ የግል ንግድ ማዕከላት እየተከፈቱ ይገኛሉ፡፡ አንድ የፖስታ አገልግሎት ሰጪ ተቋም በጠበላ ከተማ ይገኛል፡፡

2.3 መብራት

በወረዳው ውስጥ የሚገኙ የከተማ ማዘጋጃ ቤት አስተዳደር መዋቅሮች 24 ሰዓት የሃይደሮ ኤሌክትሪክ ኃይል መብራት አገልግሎት ያገኛሉ፡፡

 

2.4 የመጠጥ ውኃ አቅርቦት

የመጠጥ ውኃ አቅርቦትን በተመለከተ በእጅ ፓምፕ የሚሠራ የእጅ ጉድጓድ (                                    ) 6፣ በእጅ ፓምፕ የሚሠራ ጥልቅ ጉድጓድ (                                   ) 12፣ ጥልቅ ጉድጓድ ስርጭት (                       ) 13፣ የምንጭ ውኃ ስርጭት (                         ) 3፣ ምንጭ በቦታው ማጎልበት (           ) 9 ይገኛሉ፡፡ የወረዳው የመጠጥ ውኃ ሽፋን 54.45% ሲሆን በዘርፉ ያለውን ከፍተኛ ችግር ለማቃለል የጥልቅ ጓድጓድ ውኃ አገልግሎት ለመስጠት በተለያዩ ቀበሌዎች መስመር እየተዘረጋ ይገኛል፡፡

2.5 የገንዘብ ተቋማት፡-

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ቪዥን ፈንድ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም፣ ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም እንዲሁም ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት እየተከፈቱ ይገኛሉ፡፡

   . የማህበራዊ አገልግሎት

3.1 ጤና

  • ሆስፒታል /        / ------------------------ 1 (በግንባታ ላይ ያለ)
  • ጤና ጣቢያ /             / ------------- 6
  • ጤና ኬላ /           / ------------------ 39
  • የመጀመሪያ ደረጃ ክሊንክ /      / ------  19 (የግል)
  • መድኃኒት ቤት /        / --------------- 9 (6 የመንግስት እና 3 የግል)
  • መድኃኒት መደብር --------------------------- 1 (የግል)
  • ላቦራቶሪ --------------------------------------- 6 (የመንግስት)
  • የጤና ሽፋን ----------------------------------- 94.11%

3.2 ትምህርት

መዋዕለ ሕጻናት ት/ቤት --------------------------  3

አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (1-4ኛ ክፍል) -------------- 1

አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (1-8ኛ ክፍል) -------------- 53

ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት (9-10ኛ ክፍል) ------------ 6

መሰናዶ (11-12ኛ ክፍል) -------------------------- 2

የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋም   ------------- 1

 

 

  . በመስኖ የሚለማ የእርሻ መሬት ሁኔታ

በወረዳው ውስጥ 6 የመስኖ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ በመሆናቸው የአከባቢው አርሶ አደር ተጠቃሚ ሲሆን ለአብነት የአባያ ቢሳሬ (300 ሄ/ር)፣ ኤላ (210 ሄ/ር)፣ ሊንታላ (90 ሄ/ር)፣ ቦሳ (100 ሄ/ር)፣ ላሾ (320 ሄ/ር)፣ እና አባላ ፋራቾ (100 ሄ/ር) የመስኖ ፕሮጀክቶች ምርትና ምርታማነት ከማሳደግ አልፎ ለሀገርቱ ኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ፡፡ ይሁን እንጂ ወረዳው ካለው የከርሰ ምድርና የገጸ ምድር ውኃ አቅርቦት ለአብነት ወንዞች (ኤላ፣ ላሾ፣ ሊንታላ፣ ቢሳሬ፣ ዶንቦባ፣ ቢላቴ፣ ፋራቾ) እንዲሁም የአባያ ሐይቅ ከመኖሩ አንጻር እስካሁን በመስኖ የለማው መሬት መጠን እጅግ በጣም ዝቅተኛ ከመሆኑም ባሻገር ወረዳው ከፍተኛ ለመስኖ አገልግሎት ሊውል የሚችል የውኃ ፖቴንሻል እንዳለ፣ ከፍተኛ የዝናብ መጠን መኖሩ እና ለም ዐፈር መኖሩ ለእርሻ ኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡

 . በወረዳው የሚመረቱ ዋና ዋና ምርቶች

5.1 ዓመታዊ ሰብሎች

በቆሎ፣ ማሽላ፣ ጤፍ፣ ማሾ፣ ሰሊጥ፣ ስንዴ፣ ገብስ፣ ቦሎቄ፣ ባቄላ፣ ሽንብራ፣ የርግብ አተር፣ ለውዝ፣ የሥራ ሥር ሰብሎች፣ አትክልት (ቀይ ሽንኩርት፣ ቲማትም)፣ ጥጥ፣ ቅመማ ቅመም (በርበሬ)

5.2 ቋሚ ሰብሎች

እንሰት፣ ፍራፍሬ (ሙዝ፣ ማንጎ፣)፣ ካሳቫ፣ ሽፈራው፣ ጃትሮፓ (ቆቦ)

  . ለኢንቨስትመንት የተዘጋጀ መሬት

ተ.

ለኢንዱስትሪ በሄ/ር

ለንግድ፣ ለአገልግሎት፣

ለማህበራዊ አገልግሎት በሄ/ር

ለገጠር እርሻ ልማት በሄ/

1

59.53 ሄ/

20.71

1810

      ምንጭ፡- ጠበላ ከተማ ማዘጋጃ ቤት እና የወረዳው እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ጽ/ቤት

ማሳሰቢያ፡- ለገጠር እርሻ ኢንቨስትመንት የተለዩ ቦታዎችን በተመለከተ በአባላ ማራቃ ቀበሌ ለ4 ባለሀብቶች ከማስፋፊያም ጭምር የታሰበ 300 ሄ/ር፣ በአባያ ቢሳሬ ቀበሌ በአሁኑ ወቅት ነጻ የሆነ 300 ሄ/ር፣ በአባያ ብላቴ ቀበሌ በአሁኑ ወቅት በህገ ወጥ ሰፋሪዎች እየተወረረ ያለ ከ1000 ሄ/ር በላይ መሬት፣ በአባያ ጮካሬ ቀበሌ 70 ሄ/ር፣ በፋንጎ ገልጨጫ ቀበሌ 50 ሄ/ር፣ በአንካ ኦቻ ቀበሌ 40 ሄ/ር፣ በሴሬ ጣውራታ ቀበሌ 25 ሄ/ር እንዲሁም በደንባ ሎሜ ቀበሌ 25 ሄ/ር ሰርቨይ ተደርጎ ለኢንቨስትመንት አገልግሎት ለማዋል ታሳቢ የተደረገ ነው፡፡

   . ለኢንቨስትመንት ያለው አመቺነት

7.1 ለግብርና

  • ሰፊ በመስኖ የሚለማ የአርሶ አደር እርሻ እና የወል መሬት መኖሩ፣
  • ምቹ የአየር ፀባይ መኖሩና ዓመታዊ አማካይ የዝናብ መጠን ከፍተኛ መሆኑ፣
  • በልማት ሥራ ላይ ለማዋል በቂ የሰው ኃይል /የተማረ እና የጉልበት/ መኖሩ፣
  • በወረዳው ዓመቱን ሙሉ የማይደርቁ ወንዞች ማለትም ኤላ ወንዝ፣ ላሾ ወንዝ፣ ሊንታላ ወንዝ፣ ቢሳሬ ወንዝ፣ ዶንቦባ ወንዝ፣ ቢላቴ ወንዝ እና ፋራቾ ወንዝ ያሉት በመሆኑ በንብ ማነብ፣ በበሬ ድለባ፣ በበግ ማሞከት፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት፣ በዘመናዊ እንሰሳት ዕርባታ፣ ለዶሮ ዕርባታ እንዲሁም ዓሳ ዕርባታ ከአባያ ሐይቅ እና በሰው ሰራሽ ኩሬ ለማካሄድ ምቹ መሆኗ፣
  • በለሙ ተፋሰሶች እና በአርሶ አደር ማሳ የተሻሻለ መኖ፣ ምጥን መኖ፣ የተለያዩ የሰብል ተረፈ ምርቶች፣ የተፈጥሮ ግጦሽ መኖ አቅርቦት መኖሩ፤
  • እንስሳት ዕርባታ እና ድለባ ለማካሄድ ከፍተኛ የቀንድ ከብት ክምችት፣ ውኃ እና የግብይት ማዕከላት መኖሩ፤ በዞን አቀፍም ሆነ ሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የገበያ ፍላጎት መኖሩ፤
  • ለፍየሎች የቅንጠባ መኖዎች ያለባቸው ሰፋፊ የተፈጥሮ ደኖች መኖራቸው፤
  • የሀገረሰብና የተሻሻለ የዳልጋ ከብት፣ የበግ እና የፍየል ዝሪያ እየተስፋፋ መሆኑ (በሰው ሰራሽ ዘዴ በማዳቀል)፤
  • ለንብ አበባ ቀሰማ ምቹ የሆኑ የተፈጥሮ ደኖች፣ በለሙ ተፋሰሶች፣ የፍራፍሬ ዛፎች መኖራቸው፤
  • ከፍተኛ የአሞሌ ጨው ክምችት መኖሩ፣
  • በአስፋልት መንገድ ከአዲስ አበባ እና ከዞኑ ማዕከል ሶዶ የሚገናኝ በመሆኑ የተሻለ የገበያ ትስስርና ግንኙነት ይፈጥራል፡፡
  • በአባያ ሐይቅ ውስጥ የተለያዩ የዓሳ ዝርያዎች እና አዞ ስለሚገኝ ለዓሳና አዞ ዕርባታ ለማካሄድ ምቹ መሆኑ፣ ከአባያ ሀይቅ ጋር በተገናኘ ዓሣ ማምረት የሚቻል ሲሆን በሐይቁ ውስጥ ስከ 26 የሚጠጉ የተለያዩ የዓሣ ያዎች ንደሚገኙና ዓመ የማምረት አቅሙ ስከ 600 ቶን ንደሚደርስ ይገመ ል፡፡ ቀጣይነት ባለው መልኩ የልማት ሥራዎች ቢካሄዱ የዓሣዎቹን ከመጠበቅና ከማልማት ባሻገር ለአካባቢው ሕብረተሰብ የተሻለ ጥቅም ማስገኘት ይቻላል፡፡
  • የተለያዩ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ሰብሎችን በመስኖ ማልማት የሚችሉ ወንዞች መኖራቸው ለኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ የተመቻቹ ሁኔታዎች ናቸው፡፡

 

7.2 ለአግሮ ኢንዱስትሪ

  • ከአርሶ አደሩ የሚገኙትን የግብርና ምርቶችን (በአውትግራውር ከአርሶ አደሩ ጋር ትስስር በመፍጠር) በጥሬ ዕቃነት ተጠቅሞ በማቀነባበር እስከ ውጪ ገበያ ድረስ ለሚያቀርቡ ባለሀብቶች መሬቱ አመቺነት ያለው በመሆኑ ያለውጣውርድ ማግኘት ይቻላል፤
  • ለተለያዩ ፋብሪካዎች በጥሬ ዕቃነት ሊያገለግሉ የሚችሉ የግብርና ዉጤቶች የሆኑ እንደ ቦቆሎ፣ ቡና፣ አቮካዶ፣ ማንጎ፣ ብርቱካን፣ ቲማቲም፣ ጥጥ፣ ሙዝ፣ ቦሎቄ፣ ቅመማ ቅመም እና እንስሳት ሀብት በቅርብ መገኘታቸዉ፤
  • ለእንስሳት መኖ ዝግጅት ምቹ ሁኔታ (አልፋአልፋ፣ ሉሲኒያ፣ ላብላብ፣ አኩሪ አተር፣ የእርግብ አተር፣ ኤሌፈንት ሳር፣ ዴሾ ሣር፣ ወዘተ በአሁኑ ወቅት በወረዳው ውስጥ በሚገኙ ወጣቶች በስፋት እየተመረተ በመሆኑ፣ በቀላሉ ሊለማ የሚችልና በቂ የተዘጋጀ ቦታ በመኖሩ

7.3 ለማህበራዊ አገልግሎት

የወረዳው የጤና ሽፋን 94.11% ቢሆንም በላቦራቶሪ እና በግል ፋርማሲ ተቋማት ሽፋን ክፍተት መኖሩን ያሳያል፤

በትምህርት መስክ በመዋዕለ ሕጻናት፣ በ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች፣ እና በከፍተኛ የት/ት ተቋማትና ኮሌጆች፣ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋም ከማስፋፋት አንጻር ያሉትን ክፍተቶች ለመሙላት የግል ባለሀብት በመስኩ ለመሰማራት አመችነቱን ይጠቁማል፡፡

7.4 ለሆቴል፣ ለሪዞርት፣ ለሎጅ፣ ለመዝነኛ ፓርክ እና ቱሪዝም አገልግሎት

  • በዓለም ከቻይና ቀጥሎ 2ኛ እንዲሁም በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው የሁምቦ ካርቦን ፕሮጀክት 8 ቀበሌያትን የሚያካልል፣ በስፋትም 2,800 ሄክታር የሚሸፍነውና በአሁኑ ወቅት ከ5,200 በላይ ለሚሆኑ ለአከባቢው ማህበረሰብ የሥራ ዕድል የፈጠረ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ አሳሳቢነቱ እየጨመረ የመጣውን የካርቦን ልቀት ለመቀነስ ታስቦ እየለማና እየተጠበቀ ከመሆኑም ባለፈ ለቱሪስት መስህብነት ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፡፡
  • የአባያ ሐይቅ በውስጡ የያዘውን ሀብት በዘመናዊ መልክ አቀነጅቶ ለመጠቀም፣ የተለያዩ ለምግብነትና ለመድኃኒት ቅመማ ሊውሉ የሚችሉ ምርጥ የዓሳ ዝርያዎች (ኮደ /       /፣ ነጭ ዓሳ /          /፣ ከርከሮ /            /፣ አምበዛ /       /፣ ኮቼ /          /፣ ባለባንድራ /          /፣ ሾጣጣ /        / እና በርቦ /     /) ሀብት ጥቅም ላይ በማዋል፣ ዘመናዊ የጀልባ አገልግሎት በመስጠት የመዝነኛ ሥራዎችን በስፋት ለማካሄድ፣ እንዲሁም የባህር ዳር መናፈሻ /     / አዘጋጅቶ አገልግሎት ለመስጠት እጅግ ምቹ በሆነ ሁኔታ ተፈጥሮ ያደለው ሐይቅ በመሆኑ በዘርፉ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች አዋጭነቱ ከፍተኛ እንደሚሆን ይታመናል፡፡  
  • የጡባ ኢኮ-ቱሪዝም በወረዳው አባላ ማራቃ ቀበሌ የተንጣለለውን የአባያ ሐይቅን አጅቦ ለቱሪስቶች የአዕምሮ ዕርካታን የሚሰጥ፣ በውስጡ የተለያዩ የዱር እንስሳት ለአብነት አንበሳ፣ ነብር፣ አጋዘን፣ ጉሬዛ፣ ዝንጀሮ፣ ጦጣ፣ ተኩላና ዘንዶ እንዲሁም በሐይቁ ውስጥ 26 ዓይነት የተለያዩ የዓሳ ዝያዎች፣ አዞ እና ጉማሬ በስፋት የሚገኝበት በአሁኑ ወቅት መንገድ የተከፈተለት፣ የውኃ መስመር እና የመብራት ዝርጋታ እየተጠናቀቀ ያለ በመሆኑ ከመሠረተ ልማት አቅርቦት አንጻር ችግር የሌለበት መሆኑ፤
  • በአባያ ሐይቅ አጠገብ ከተለያዩ በሽታዎች በፈዋሽነት የሚታወቀውን የእንፋሎት ጭስ ፍል ውኃ በቀትርም ጭምር የሚንቦለቦለውን ለመጎበኘትና ለመዝናናት ወደ መስህቡ የሚያደርስና ከጡባ ጋር የሚያገናኝ 16 ኪ.ሜትር መንገድ በሐይቁ ዳርቻ እየተከፈተ መሆኑ፣
  • የተፈጥሮ ዋሻ (በሆብቻ ጋዋ ቀበሌ)፣ ትክል ድንጋይ (በኮዶ ቃንቆ፣ ፋንጎ ገልጨጫ እና በኮይሻ ጎላ ቀበሌ)፣ አማዶ ካብ (ፋንጎ ገልጨጫ፣ ፋንጎ ሎሜ፣ አባያ፣ ሴሬ ጣውራታ እና በአንካ ኦቻ ቀበሌ)፣ ሐመሳ ፏፏቴ (በአባላ ማራቃ ቀበሌ) እና የደን ልማት (ኮይሻ ኦጎዳማ እና ሾጮራ አጎዳማ ቀበሌ) በወረዳው ውስጥ የሚገኙ በመሆናቸው የቱሪስት መስህብነት ደረጃውን የላቀ ያደርጋሉ፡፡
  • በወረዳው ዋና ከተማም ሆነ በሌሎች የማዘጋጃ ቤቶች ውስጥ ደረጃውን የጠበቀ ሆቴል፣ ሎጅ፣ ሪዞርት፣ ፔንሲዮን እና የመዝነኛ ማዕከላት ያለመኖሩ በዘርፉ የገበያ ክፍተት መኖሩን ያሳያል፤   
  • በወረዳው የሚገኙ ሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ የቱሪስት መስህቦች ቁጥር በርካታ በመሆኑ ቱሪስት የመሳብ አቅም ከፍተኛ ስለሆነ እንዲሁም ለዘርፉ ኢንቨስትመንት በቂ የለማ ቦታ የተዘጋጀ በመሆኑ ባለሃብቱ ቢሠማራበት አዋጭ ነዉ፡፡

7.5 ለማዕድን፣ ኢነርጂ እና ለኮንስትራክሽን ዘርፍ

  • ለኮንስትራክሽን የሚያገለግሉ ጥሬ ዕቃዎች በአከባቢዉ በበቂ ሁኔታ መገኘታቸዉ፣ ነጭ ድንጋይ (9.7 ሄ/ር)፣ ጥቁር ድንጋይ (10 ሄ/ር)፣ አሸዋ (2 ሄ/ር)፣ ጠጠር፣ ቀይ ቀላል ጋራጋንቲ (6 ሄ/ር)፣ የኖራ /      / ድንጋይ (1230 ሄር) በአባያ ቢሳሬ ቀበሌ የመሳሰሉት በከፍተኛ መጠን መኖሩ፤
  • ለብሎኬት ማምረቻ አገልግሎት የሚዉል ፑሚስ ወይም ኮምቼ (10 ሄ/ር)፣
  • ለመስተዋት ሥራ የሚያገለግል አብዚድያን፣
  • ለግንባታ ሥራ የሚያገለግል ራዮላይት፣
  • ለመንገድ ግንባታ የሚዉል ስኮሪያ፣
  • ለሴራሚክስ ምርት የሚሆን ባልጩት ድንጋይ፣
  • ለግንባታ አገልግሎትና ለኮብል ስቶን ሥራ ሊዉል የሚችል ባዛልትክ ድንጋይ፣
  • ለጂኦቴርማል የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ሊውል የሚችል ከፍተኛ የሙቀት መጠን ያላቸው ፍል ውኃዎች በአባላ ማራቃ ቀበሌ፣ በአባያ ቢሳሬ፣ በአባያ ጮካሬ እና አባያ ብላቴ ቀበሌ ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውና በአሁኑ ወቅት ጥናት እየተካሄደባቸው መሆኑ፤

    . የኢንቨስትመንት አማራጭ ዕድሎች

8.1 ግብርና ዘርፍ

  • አትክልትና ፍራፍሬ ልማት፣ ቅመማ ቅመም ልማት፣
  • የወተትና ሥጋ ከብት ማርባትና ማድለብ፣
  • በዶሮ ዕርባታና እንቁላል ምርት፣ በንብ ማነብ፣ በበግና ፍየል ማሞከት፣
  • ከአባያ ሐይቅ እና በሰው ሠራሽ ኩሬዎች ዓሳ እና አዞ ዕርባታ ማካሄድ፣
  • የእንስሳት መኖ ዘር ማባዛትና ማልማት፣
  • ለባዮ ዲዝል ምርት የሚሆን የጃትሮፋ ተክል ማልማት፣

8.2 በማህበራዊና በአገልግሎት ዘርፍ

  • በትምህርት ዘርፍ ከመዋዕለ ህፃናት እስከ ኮሌጅ፤
  • በጤና ዘርፍ በክሊኒክ፣ ላቦራቶሪ፣ ፋርማሲ፣ ሆስፒታል፣ በእንስሳት ህክምና ማዕከላት
  • በመዝነኛ አገልግሎት ዘርፍ፡- ሲኒማ ቤቶች፣ ፊልምና ቲያትር ቤቶች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ጂም ቤቶች እና ሌሎች
  • በሆቴልና ቱሪዝም ከካፊቴሪያ፣ ግሮሰሪ፣ ፔንሲዮን እስከ ባለኮከብ ሆቴል
  • ለሎጅ፤ ለሪዞርትና መዝናኛ ማዕከል፣
  • በፍል ውኃ አከባቢ ፊዝዮቴራፒ አገልግሎት የሚሰጥ መታጠቢያ

8.3 በኢንዱስትሪ ዘርፍ፡- በኢንዱስትሪ ፖቴንሻል ሰርቨይ /   / ጥናት መሠረት በከተማው ውስጥ፡-

  • ለምግብና ምግብ ውጤቶች ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣
  • ለሥጋ ምርት ማቀነባበር (የዶሮ፣ የዓሳ፣ የበግ፣ የፍየል እና የቀንድ ከብት ሥጋ ማዘጋጀት፣ ማሸግ፣ ወደ ውጭ ሀገር መላክ)፣
  • የወተትና የወተት ውጤቶች ማቀነባበሪያ፣
  • ለአትክልትና ፍራፍሬ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣
  • ለቤትና ቢሮ ዕቃዎች ማምረቻ ፋብሪካ፣ የንብ ቀፎ ፍሬም ማምረቻ፣
  • ከቃጫ ጆኒያ እና ከረጢት ማምረቻ ፋብሪካ፣
  • ከቅባት እህሎች /ሰሊጥ፣ ኑግ፣ ለውዝ፣ ወዘተ/ ዘይት ማምረቻ ፋብሪካ፣
  • የኖራ ድንጋይ /ጂፕሰም /            / ማምረቻ ፋብሪካ፣
  • የእንስሳት መኖ ዘር ማባዣ፣ ማቀነባበሪያና ማሸጊያ ፋብሪካ፣
  • የማዕድን ውኃ ማሸጊያ፣
  • የአዝርዕት ዘር ማቀነባበሪያ፣
  • የሽፈራው /       / ዘይት ማምረቻ፣  
  • የማርና ሰም ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣
  • የአሞሌ ጨው ማቀነባበሪያ፣       
  • የብሎኬት እና የጠጠር ማምረቻ፣
  • መስተዋት ማምረቻ፣            
  • ሶዲየም ሲሊኬት ማምረቻ፣
  • የሴራሚክስ ውጤቶችና የመፀዳጃ ቤት ዕቃዎች ማምረቻ፣
  • ለግንባታ አገልግሎት የሚውሉ አብዜዲያን፣ ራዮላይት፣ ሰኮሪያ እና ሌሎችን ማምረት
  • በጂኦቴርማል ኢነርጂ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት፣
  • ኢፒተርማል የወርቅ ማዕድን ማምረት፣