• Call Us
  • +251465512106

የኪንዶ ኮይሻ ወረዳ አስተዳደር

 . አጠቃላይ ገጽታ

የኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ዋና ከተማ በሌ ከዞኑ ርዕሰ መዲና ሶዶ በስተምዕራብ በ37 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝና የቆዳ ስፋቱም 526.3 ካሬ ኪሜትር ሲሆን በ23 የገጠር ቀበሌዎች እና በሦስት የማዘጋጃ ቤት ከተሞች (በሌ፣ ሃናዜ እና ሶርቶ ማዘጋጃ ቤት) የተዋቀረ ነው፡፡ በአስተዳደሩ የሚገኙ የኢንቨስትመንት አማራጮች፤ የማዕድን ሀብት ክምችትና የቱሪስት መስህቦች እንደሚከተለዉ ቀርበዋል፡፡

1.1 ከባህር ወለል ከፍታ

ከባህር ወለል በላይ ከ600 እስከ 2,280 ሜትር ከፍታ ያላቸው የመሬት ገጾች አሉት፡፡

1.2 የአየር ንብረት

የወረዳው አግሮኢኮሎጂን በተመለከተ 72% ቆላ፣ 20% ወይና ደጋ እና 8% ደጋ ነዉ፡፡ የዓመቱ አማካይ የሙቀት መጠን 12.6--25 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ነው፡፡ አማካይ ዓመታዊ የዝናብ መጠን ከ1,401 እስከ 1,600 ሚሊ ሜትር ነው፡፡

1.3 ሥነ-ሕዝብ

በ2009 ዓ.ም ከዞኑ ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በተገኘው የስታትስቲክስ መረጃ መሠረት የወረዳው አጠቃላይ የሕዝብ ብዛት 139,662 ሲሆን የሕዝብ ጥግግት 258 በስኳየር ኪ/ሜትር ነው፡፡

  . የመሠረተ ልማት አቅርቦት ሁኔታ

2.1 መንገድ

የወረዳውን ዋና ከተማ በሌ ከሶዶ- ዳውሮ ታርጫ አቋርጦ የሚያልፍ የአስፋልት መንገድ የተዘረጋ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ 59.9 ኪ/ሜትር የጠጠር እና 496 ኪ/ሜትር ጥሪጊያ መንገድ የተለያዩ የወረዳ ቀበሌዎችን እና አጎራባች ወረዳዎችን እርስ በርስ የሚያገናኝ መንገዶች አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡   

2.2 ስልክ፣ ኢንተርኔት እና የፖስታ አገልግሎት

የሞባይልና የመደበኛ ስልክ አገልግሎት፣ እንዲሁም የኢንተርኔት አገልግሎት የሚሰጡ የግል ንግድ ማዕከላት እየተከፈቱ ይገኛሉ፡፡ አንድ የፖስታ አገልግሎት ሰጪ ተቋም በበሌ ከተማ ይገኛል፡፡

2.3 መብራት

በወረዳው ውስጥ የሚገኙ የከተማና ማዘጋጃ ቤት ያላቸው ቀበሌ አስተዳደር አከባቢዎች 24 ሰዓት የሃይደሮ ኤሌክትሪክ ኃይል መብራት አገልግሎት ያገኛሉ፡፡

2.4 የመጠጥ ውኃ አቅርቦት

የመጠጥ ውኃ አቅርቦትን በተመለከተ በእጅ ፓምፕ የሚሠራ በእጅ ፓምፕ የሚሠራ ጥልቅ ጉድጓድ (                                   ) 1፣ ጥልቅ ጉድጓድ ስርጭት (                       ) 1፣ የምንጭ ውኃ ስርጭት (                         ) 40፣ ምንጭ ማጎልበት (           ) 38 ይገኛሉ፡፡ የወረዳው የመጠጥ ውኃ ሽፋን 82.45% ነው፡፡

2.5 የገንዘብ ተቋማት፡-

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም እንዲሁም ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት እየተከፈቱ ይገኛሉ፡፡

   . የማህበራዊ አገልግሎት

3.1 ጤና

  • ሆስፒታል /        / ------------------------ 1
  • ጤና ጣቢያ /             / ------------- 4
  • ጤና ኬላ /           / ------------------ 30
  • የመጀመሪያ ደረጃ ክሊንክ /      / -------  8 (የግል)  
  • መድኃኒት ቤት /        / --------------- 5 (የመንግስት)
  • መድኃኒት መደብር --------------------------- 2 (1 የግል እና 1 የመያድ)
  • ላቦራቶሪ --------------------------------------- 5 (የመንግስት)
  • የጤና ሽፋን ----------------------------------- 93.90%

3.2 ትምህርት

መዋዕለ ሕጻናት ት/ቤት -------------------------- 2

አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (1-4ኛ ክፍል) -------------- 3

አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (1-8ኛ ክፍል) -------------- 40

ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት (9-10ኛ ክፍል) ------------ 4

መሰናዶ (11-12ኛ ክፍል) --------------------------- 1

የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋም------ ----------- 1

  . በመስኖ የሚለማ የእርሻ መሬት ሁኔታ

በወረዳው ውስጥ 3 የመስኖ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ በመሆናቸው የአከባቢው አርሶ አደር ተጠቃሚ ሲሆን ለአብነት ኦንጎቶ መስኖ በቦርኮሼ ቀበሌ (70 ሄ/ር)፣ ባሊያ መስኖ በሞልቲቾ ቀበሌ (100 ሄ/ር) እና ለፍያ መስኖ በሙንዴና ቀበሌ (560 ሄ/ር) የመስኖ ፕሮጀክቶች ምርትና ምርታማነት ከማሳደግ አልፎ ለሀገርቱ ኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ፡፡ ይሁን እንጂ ወረዳው ካለው የከርሰምድርና የገጸምድር ውኃ አቅርቦት ለአብነት ወንዞች (ኦሞ፣ ጋሙዋ፣ ጋጉራ፣ ኬላ፣ ፍንቻዋ፣ ኦንጎቶ፣ ባሊያ እና ሳንኩራ) ከመኖሩ አንጻር እስካሁን በመስኖ የለማው መሬት መጠን በጣም ዝቅተኛ ከመሆኑም ባሻገር ወረዳው ከፍተኛ ለመስኖ አገልግሎት ሊውል የሚችል የውኃ ፖቴንሻል እንዳለ፣ ከፍተኛ የዝናብ መጠን መኖሩ እና ለም ዐፈር መኖሩ ለእርሻ ኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡

 . በወረዳው የሚመረቱ ዋና ዋና ምርቶች

5.1 ዓመታዊ ሰብሎች

በቆሎ፣ ማሽላ፣ ጤፍ፣ ስንዴ፣ ሰሊጥ፣ ገብስ፣ ቦሎቄ፣ ባቄላ፣ አተር፣ ማሾ፣ የሥራ ሥር ሰብሎች፣ አትክልት (ቀይ ሽንኩርት፣ ቲማትም)፣ ቅመማ ቅመም (ዝንጅብል፣ በርበሬ)

5.2 ቋሚ ሰብሎች

ፍራፍሬ (ሙዝ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ፣ አቮካዶ)፣ ካሳቫ፣ ሽፈራው፣ ጃትሮፓ (ቆቦ)፣ እንሰት፣ ቡና፣

 

 

 

 

 

  . ለኢንቨስትመንት የተዘጋጀ መሬት በሄ/ር

ተ.

የቀበሌው ስም

(ልዩ መንደር)

ለኢንዱስትሪ  

ለንግድ፣ ለማህበራዊ አገልግሎት  

ለገጠር እርሻ ልማት ሊውል የሚችል መሬ

1

በሌ ከተማ

50 ሄ/

16.7 ሄ/

------

2

ማንአራ ቀበ

------

-----

400 (ለሰብል ልማት)

3

ፋጀና ማታ ቀበ

------

-----

150 (ለሰብል ልማት)

4

ሀናዜ ቀበ

------

-----

170 (ለሰብል ልማት)

5

ኪንዶ ሀንጋላ ቀበ

------

-----

140 (ለሰብል ልማት)

6

ሙንዴና ቀበ

------

-----

220 (ለሰብል ልማት)

7

ፈጨና ቀበ

------

-----

430 (ለአትክልትና ፍራፍሬ ልማት)

8

ባዴ ወይ

------

-----

250  >

9

ሶር

------

-----

280  >

10

ጨራ

------

-----

230  >

11

ሴሬ አታላ

------

-----

293  >

ድም

50

16.7

2,563 ሄ/

  ምንጭ፡- በሌ ከተማ ማዘጋጃ ቤት እና የወረዳው እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽ/ቤት

ማሳሰቢያ፡- ለገጠር እርሻ ኢንቨስትመንት የተለዩ ቦታዎችን በተመለከተ ከወረዳዉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽ/ቤት ለኢንቨስትመንት ሊዉል የሚችል የወል መሬት ከላይ በሠንጠረዡ የተመለከተው ሰርቨይ ተደርጎ የተካለለ ሲሆን ከበሌ ማዘጋጃ ቤት በተገኘው መረጃ መሠረት 66.7 ሄ/ር ለተለያዩ አገልግሎቶች በከተማው መሠረታዊ ፕላን መሠረት የተዘጋጀ መሆኑን ታሳቢ ሊደረግ ይገባል፡፡

   . ለኢንቨስትመንት ያለው አመቺነት

7.1 ለግብርና

  • ሰፊ በመስኖ የሚለማ የአርሶ አደር ማሳ እና የወል መሬት መኖሩ፣
  • ዓመታዊ አማካይ የዝናብ መጠን ከፍተኛ መሆኑ፣
  • በወረዳው ዓመቱን ሙሉ የማይደርቁ ወንዞች ማለትም የኦሞ፣ ጋሙዋ፣ ጋጉራ፣ ኬላ፣ ፍንቻዋ፣ ኦንጎቶ፣ ባሊያ እና የሳንኩራ ወንዝ እንዲሁም በተፋሰስ የለሙና የተካለሉ ሰፊ ቦታዎች ያሉት በመሆኑ በንብ ማነብ፣ በበሬ ድለባ፣ በበግ ማሞከት፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት፣ በዘመናዊ እንሰሳት ዕርባታ፣ ለዶሮ ዕርባታ እንዲሁም ዓሳ ዕርባታ ከኦሞ የሰው ሠራሽ ሐይቅ እና በሰው ሰራሽ ኩሬ ለማካሄድ ምቹ መሆኑ፣
  • በልማት ሥራ ላይ ለማዋል በቂ የሰው ኃይል /የተማረ እና የጉልበት/ መኖሩ፣
  • በለሙ ተፋሰሶች እና በአርሶ አደር ማሳ የተሻሻለ መኖ፣ ምጥን መኖ፣ የተለያዩ የሰብል ተረፈ ምርቶች፣ የተፈጥሮ ግጦሽ መኖ አቅርቦት መኖሩ፤
  • እንስሳት ዕርባታ እና ድለባ ለማካሄድ ከፍተኛ የቀንድ ከብት ክምችት፣ ውኃ እና የግብይት ማዕከላት መኖሩ፤ በዞን አቀፍም ሆነ ሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የገበያ ፍላጎት መኖሩ፤
  • ለፍየሎች የቅንጠባ መኖዎች ያለባቸው ሰፋፊ የተፈጥሮ ደኖች መኖራቸው፤
  • የተሻሻለ የእንስሳት ዝሪያ እየተስፋፋ መሆኑ (በሰው ሰራሽ ዘዴ በማዳቀል)፤
  • ከፍተኛ የሀገረሰብና የተሻሻለ የበግ፣ የፍየል እና የዶሮ አቅርቦት መኖሩ፤
  • ለንብ አበባ ቀሰማ ምቹ የሆኑ የተፈጥሮ ደኖች፣ በለሙ ተፋሰሶች፣ የፍራፍሬ ዛፎች መኖራቸው፤

7.2 ለአግሮ ኢንዱስትሪ

  • ከአርሶ አደሩ የሚገኙትን የግብርና ምርቶችን (በአውትግራውር ከአርሶ አደሩ ጋር ትስስር በመፍጠር) በጥሬ ዕቃነት ተጠቅሞ በማቀነባበር እስከ ውጪ ገበያ ድረስ ለሚያቀርቡ ባለሀብቶች መሬቱ አመቺነት ያለው በመሆኑ ያለውጣውርድ ማግኘት ይቻላል፤
  • ለተለያዩ ፋብሪካዎች በጥሬ ዕቃነት ሊያገለግሉ የሚችሉ የግብርና ምርቶች የሆኑ እንደ ቦቆሎ፣ ሰሊጥ፣ ማሾ፣ ቦሎቄ፣ ቡና፣ ሾንኮራ አገዳ፣ አቮካዶ፣ ማንጎ፣ ቲማቲም፣ ሙዝ እና እንስሳት ሀብት በቅርበትና በበቂ ሁኔታ መገኘታቸዉ፤
  • ለእንስሳት መኖ ዝግጅት ምቹ ሁኔታ (የተፈጥሮ ሣር፣ አልፋአልፋ፣ ሉሲኒያ፣ ላብላብ፣ አኩሪ አተር፣ የርግብ አተር፣ ኤሌፈንት ሳር፣ ዴሾ ሣር፣ ወዘተ በአሁኑ ወቅት በተፋሰስ በለሙ ቦታዎች እና በአርሶ አደር ማሳ በስፋት እየተመረተ በመሆኑ እንዲሁም በቀላሉ ሊለማ የሚችልና በቂ የተዘጋጀ ቦታ በመኖሩ፣

7.3 ለማህበራዊ አገልግሎት

የወረዳው የጤና ሽፋን 93.90% ቢሆንም በላቦራቶሪ እና በግል ፋርማሲ ተቋማት ሽፋን ክፍተት መኖሩን ያሳያል፤

የመዋዕለ ሕጻናት እና የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ተቋማት ብዛት ዝቅተኛ መሆኑ እንዲሁም በከፍተኛ የት/ት ተቋማት ወይም ኮሌጆች በወረዳው ውስጥ ያለመኖር ለግል ባለሀብት በመስኩ መሰማራት አመችነቱን ይጠቁማል፡፡

 

 

7.4 ለሆቴል፣ ለሪዞርት፣ ለሎጅ፣ ለመዝነኛ ፓርክ እና ቱሪዝም አገልግሎት

  • በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ የሆነው የግልገል ጊቤ 3 የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ከኃይል ማመንጫነቱ ባለፈ ለቱሪስት መስህብነት፣ ለዓሳ ሀብት ልማት፣ ለትራንስፖርቴሸን እንዲሁም ዘመናዊ የጀልባ አገልግሎት በመስጠት የመዝነኛ ሥራዎችን በስፋት ለማካሄድ እጅግ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል፡፡
  • አሪኰሎጂ ጥናትና ምርምር ሊውሉ የሚችሉ ታርካዊ የሆኑ ዋሻዎች ለአብነት ፑላሳ አምባ አሩጂያ ዋሻ (በሚኖ ዋራዛ ቀበሌ)፣ አምቤ አከርሣ ዋሻ (በዛምኔ ቀበሌ)፣ ወጪ ዋሻ (በሶርቶ ቀበሌ)፣ ዛሬዋ ዋሻ (በጉሩሞ ዋዜ ቀበሌ)፣ አሩጂያ ዋሻ (በጋሌ ዋርጎ ቀበሌ) እና ኪንዶ አንጋላ ዋሻ (በኪ/አንጋላ ቀበሌ)፤ በጣም ሰፊና ታርካዊ የሆነ የአለት ድንጋይ (በፈጫና/በሶርቶ ቀበሌ)፣  ሰው ሠራሽ ትክል ድንጋይ (በሶሬ ዋሙራ፣ በዶጌ ላሮሶ፣ በዛምኔ ነሬ፣ በኦይዱ ጫማ እና በቱልቻ ሆምኣ ቀበሌ) በወረዳው ውስጥ የሚገኙ በመሆናቸው የቱሪስት መስህብነት ደረጃውን ከፍ ያደርጋሉ፡፡
  • በወረዳው ዋና ከተማም ሆነ በሌሎች የማዘጋጃ ቤቶች ውስጥ ደረጃውን የጠበቀ ሆቴል፣ ሎጅ፣ ሪዞርት፣ ፔንሲዮን እና የመዝነኛ ማዕከላት ያለመኖሩ በዘርፉ የገበያ ክፍተት መኖሩን ያሳያል፡፡    

7.5 ለማዕድን፣ ኢነርጂ እና ለኮንስትራክሽን ዘርፍ

ለኮንስትራክሽን የሚያገለግሉ ጥሬ ዕቃዎች በአከባቢዉ በበቂ ሁኔታ መገኘታቸዉ፣ ግራናይት፣ ነጭ ድንጋይ ለግንባታ አገልግሎት የሚውል በሞልቲቾ እና ፋጀና ማታ ቀበሌ፣ ጥቁር ድንጋይ ለጠጠር ምርት የሚሆን በሶርቶ ቀበሌ፣ ትራካይት እና ባዛልትክ ድንጋይ /ለኮብል ስቶንና ለኮንክሪት አገልግሎት/ የሚሆን ድንጋይ በሙንዴና ቀበሌ፣ የመሳሰሉት በከፍተኛ መጠን መኖሩ፤

    . የኢንቨስትመንት አማራጭ ዕድሎች

8.1 ግብርና ዘርፍ

  • አትክልትና ፍራፍሬ ልማት (ማንጎ፣ አቦካዶ፣ ሙዝ፣ ፓፓያ)፣
  • ቅመማ ቅመም (ዝንጅብል፣ ዕርድ፣ በርበሬ) ልማት፣
  • የወተትና ሥጋ ከብት ማርባትና ማድለብ፣
  • በዶሮ ዕርባታና እንቁላል ምርት፣
  • በንብ ማነብ፣ በበግና ፍየል ማሞከት፣
  • የእንስሳት መኖ ዘር ማባዛትና ማልማት፣
  • የቅባት እህሎች ማልማት (ሰሊጥ)
  • የአገዳ ሰብሎችን ማምረት፣
  • ለባዮ ዲዝል ምርት የሚሆን የጃትሮፋ ተክል ማልማት፣

8.2 በማህበራዊና በአገልግሎት ዘርፍ

  • በትምህርት ዘርፍ ከመዋዕለ ህፃናት እስከ ኮሌጅ፤
  • በጤና ዘርፍ በከፍተኛ ክሊኒክ፣ ላቦራቶሪ፣ ፋርማሲ፣ በእንስሳት ህክምና ማዕከላት
  • በመዝነኛ አገልግሎት ዘርፍ፡- ሲኒማ ቤቶች፣ ፊልምና ቲያትር ቤቶች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ጂም ቤቶች እና ሌሎች
  • በሆቴልና ቱሪዝም ከካፊቴሪያ፣ ግሮሰሪ፣ ፔንሲዮን እስከ ባለኮከብ ሆቴል
  • ለሎጅ፤ ለሪዞርትና መዝናኛ ማዕከል፣
  • ነዳጅ ማደያዎች እና ከፍተኛ ጋራዥ፣
  • ሱፐር ማርኬት /የገበያ ማዕከላት፣ ሪል ስቴት ገንብቶ ማከራየት፣
  • ላውንዴሪ አገልግሎት፣
  • የጅምላ ንግድ ማከፋፈያ፣

8.3 በኢንዱስትሪ ዘርፍ፡- የኢንዱስትሪ ፖቴንሻል ሰርቨይ /   / ጥናት መሠረት በከተማው ውስጥ

  • ለምግብና ምግብ ውጤቶች ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣
  • ለሥጋና የሥጋ ውጤቶች ማቀነባበሪያ፣
  • የወተትና የወተት ውጤቶች ማቀነባበሪያ፣
  • ለአትክልትና ፍራፍሬ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣
  • ከቅባት እህሎች /ሰሊጥ/ ማምረቻ ፋብሪካ፣
  • የእንስሳት መኖ ዘር ማባዣ፣ ማቀነባበሪያና ማሸጊያ ፋብሪካ፣
  • የማርና ሰም ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣
  • የብሎኬት እና የጠጠር ማምረቻ፣