አጠቃላይ ገጽታ
የቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ዋና ከተማ ቦምቤ ከዞኑ ርዕሰ መዲና ሶዶ በስተሰሜን ምዕራብ በ56 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝና የቆዳ ስፋቱም 272.2 ካሬ ኪሜትር ሲሆን በ17 የገጠር ቀበሌዎች እና በሁለት የማዘጋጃ ቤት ከተሞች (ቦምቤ እና ሞሌ ማዘጋጃ ቤት) የተዋቀረ ነው፡፡ በአስተዳደሩ የሚገኙ የኢንቨስትሜንት አማራጮች፤ የማዕድን ሀብት ክምችትና የቱሪስት መስህቦች እንደሚከተለዉ ቀርበዋል፡፡
1.1 ከባህር ወለል ከፍታ
ከባህር ወለል በላይ ከ1,500 እስከ 2,5000 ሜትር ከፍታ ያላቸው የመሬት ገጾች አሉት፡፡
1.2 የአየር ንብረት
የወረዳው አግሮኢኮሎጂን በተመለከተ 40% ቆላ፣ 45% ወይና ደጋ እና 15% ደጋ ነዉ፡፡ የዓመቱ አማካይ የሙቀት መጠን 12.6--25 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ነው፡፡ አማካይ ዓመታዊ የዝናብ መጠን ከ1,200 እስከ 1,600 ሚሊ ሜትር ነው፡፡
1.3 ሥነ-ሕዝብ
በ2009 ዓ.ም ከዞኑ ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በተገኘው የስታትስቲክስ መረጃ መሠረት የወረዳው አጠቃላይ የሕዝብ ብዛት 116,226 ሲሆን የሕዝብ ጥግግት 415 በስኳየር ኪ/ሜትር ነው፡፡
. የመሠረተ ልማት አቅርቦት ሁኔታ
2.1 መንገድ
የወረዳውን ዋና ከተማ ቦምቤን ከአረካ ከተማ እና ከሞሌ መንኢሳ የሚያገናኝ የጠጠር መንገድ የተዘረጋ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ 70.4 ኪ/ሜትር የጠጠር እና 459 ኪ/ሜትር ጥሪጊያ መንገድ የተለያዩ የወረዳ ቀበሌዎችን እና አጎራባች ወረዳዎችን እርስ በርስ የሚያገናኝ መንገዶች አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
2.2 ስልክ፣ ኢንተርኔት እና የፖስታ አገልግሎት
የመደበኛ ስልክ አገልግሎት በቦምቤ እና በሞሌ ከተሞች ያለ ሲሆን የሞባይል አገልግሎት ሁሉም ቀበሌዎች ያገኛሉ፡፡ አንድ የፖስታ አገልግሎት ሰጪ ተቋም በቦምቤ ከተማ ይገኛል፡፡
2.3 መብራት
በወረዳው ውስጥ የሚገኙ የቦምቤ እና ፋራዎቻ ከተማ አከባቢዎች 24 ሰዓት የሃይደሮ ኤሌክትሪክ ኃይል መብራት አገልግሎት ያገኛሉ፡፡
2.4 የመጠጥ ውኃ አቅርቦት
የመጠጥ ውኃ አቅርቦትን በተመለከተ በእጅ ፓምፕ የሚሠራ በእጅ ፓምፕ የሚሠራ የእጅ ጉድጓድ ( ) 6፣ በእጅ ፓምፕ የሚሠራ ጥልቅ ጉድጓድ ( ) 49፣ ጥልቅ ጉድጓድ ስርጭት ( ) 1፣ የምንጭ ውኃ ስርጭት ( ) 3፣ ምንጭ በቦታው ማጎልበት ( ) 18 ይገኛሉ፡፡ የወረዳው የመጠጥ ውኃ ሽፋን 56.74% ነው፡፡
2.5 የገንዘብ ተቋማት፡-
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም እንዲሁም ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት እየተከፈቱ ይገኛሉ፡፡
. የማህበራዊ አገልግሎት
3.1 ጤና
3.2 ትምህርት
መዋዕለ ሕጻናት ት/ቤት -------------------------- 4
አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (1-4ኛ ክፍል) ------------- 9
አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (1-8ኛ ክፍል) -------------- 25
ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት (9-10ኛ ክፍል) ------------ 2
መሰናዶ (11-12ኛ ክፍል) --------------------------- 1
. በመስኖ የሚለማ የእርሻ መሬት ሁኔታ
በወረዳው ውስጥ 2 የመስኖ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ በመሆናቸው የአከባቢው አርሶ አደር ተጠቃሚ ሲሆን ለአብነት ማጌራ መስኖ በፋራዎቻ ቀበሌ (150 ሄ/ር) እና ወይቦ መስኖ በአጆራ ቀበሌ (190 ሄ/ር) የመስኖ ፕሮጀክቶች ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ወደ ሥራ የተገባ ቢሆንም 100% ተግባራዊ ባለመሆኑ የታለመውን ግብ ሊመታ አልቻለም፡፡ ይሁን እንጂ ወረዳው ካለው የከርሰምድርና የገጸምድር ውኃ አቅርቦት ለአብነት ወንዞች (ወይቦ፣ ማጌራ፣ ባሊሺያ እና ኦሞ ወንዝ) ከመኖራቸው አንጻር እስካሁን በመስኖ የለማው መሬት መጠን በጣም ዝቅተኛ ከመሆኑም ባሻገር ወረዳው ከፍተኛ ለመስኖ አገልግሎት ሊውል የሚችል የውኃ ፖቴንሻል እንዳለ፣ ከፍተኛ የዝናብ መጠን መኖሩ እና ለም ዐፈር መኖሩ ለእርሻ ኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡
. በወረዳው የሚመረቱ ዋና ዋና ምርቶች
5.1 ዓመታዊ ሰብሎች
የአገዳ ሰብሎች (በቆሎ፣)፣ የጥራጥሬ ሰብሎች (ቦሎቄ፣ ባቄላ፣ አተር፣ አኩሪ አተር)፣ የብርዕ ሰብሎች (ጤፍ፣ ስንዴ፣ ገብስ)፣ የሥራ ሥር ሰብሎች (ስኳር ድንች፣ ካሳቫ፣ ጎዳሬ)፣ አትክልት (ቀይ ሽንኩርት፣ ቲማትም)፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ቅመማ ቅመም (ዝንጅብል፣ ዕርድ፣ በርበሬ/ቃሪያ)፣
5.2 ቋሚ ሰብሎች
ፍራፍሬ (ሙዝ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ፣ አቮካዶ፣ አፕል)፣ ሽፈራው/ሞሪንጋ፣ እንሰት፣ ቡና፣ ጫት
. ለኢንቨስትመንት የተዘጋጀ መሬት በሄ/ር
ተ.ቁ
የቀበሌው ስም
(ልዩ መንደር)
ለኢንዱስትሪ
ለንግድ እና ለማህበራዊ አገልግሎት
ለከተማ ግብርና
ለገጠር እርሻ ልማት ሊውል የሚችል መሬት
1
ቦምቤ ከተማ
89.977ሄ/ር
11.7 ሄ/ር
42.4378
------
2
ባዳዬ ቀበሌ (ሶልኮ)
-----
50ሄ/ር (ለዝንጅብል፣ ዕርድ)
3
ባዳዬ ቀበሌ (ቂርቆ)
242 ሄ/ር (ለዝንጅል)
4
አዲላ ቀበሌ
2 ሄ/ር
ለቡና/ዝንጅብል ማቀነባበር
ምንጭ፡- ቦምቤ ከተማ ማዘጋጃ ቤት እና የወረዳው እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽ/ቤት
ማሳሰቢያ፡- ለገጠር እርሻ ኢንቨስትመንት የተለዩ ቦታዎችን በተመለከተ በኢንቨስትመንት መሬት ባንክ ውስጥ ተመዝግቦና ተካልሎ በባዳዬ ቀበሌ የሚገኘው 292 ሄ/ር በተጨማሪ ከወረዳዉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽ/ቤት በተፋሰስ ሊለሙ የሚችሉ የወል መሬት ሰርቨይ ተደርጎ የተካለለ ሲሆን ከቦምቤ ማዘጋጃ ቤት በተገኘው መረጃ መሠረት 144.11 ሄ/ር ለተለያዩ አገልግሎቶች በከተማው መሠረታዊ ፕላን መሠረት የተዘጋጀ መሆኑን ታሳቢ ሊደረግ ይገባል፡፡
. ለኢንቨስትመንት ያለው አመቺነት
7.1 ለግብርና
7.2 ለአግሮ ኢንዱስትሪ
7.3 ለማህበራዊ አገልግሎት
የወረዳው የጤና ሽፋን 90% የደረሰ ቢሆንም በላቦራቶሪ እና በግል ፋርማሲ ተቋማት ሽፋን ክፍተት መኖሩን ያሳያል፤
ከመዋዕለ ሕጻናት እስከ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ተቋማት ብዛት ዝቅተኛ መሆኑ እንዲሁም በከፍተኛ የት/ት ተቋማት ወይም ኮሌጆች በወረዳው ውስጥ ያለመኖር ለግል ባለሀብት በመስኩ መሰማራት አመችነቱን ይጠቁማል፡፡
7.4 ለሆቴል፣ ለሪዞርት፣ ለሎጅ፣ ለመዝነኛ ፓርክ እና ቱሪዝም አገልግሎት
7.5 ለማዕድን፣ ኢነርጂ እና ለኮንስትራክሽን ዘርፍ
ለኮንስትራክሽን የሚያገለግሉ ጥሬ ዕቃዎች በአከባቢዉ በበቂ ሁኔታ መገኘታቸዉ፣ ነጭ ድንጋይ ለግንባታ አገልግሎት የሚውል በ13 የገጠር ቀበሌዎች ውስጥ፣ ጥቁር ድንጋይ ለጠጠር ማምረት የሚሆን ሲኖር በተለያዩ ቀበሌዎች ነጭ ድንጋይ ( ) የመሳሰሉት በከፍተኛ መጠን መኖሩ፤
. የኢንቨስትመንት አማራጭ ዕድሎች
8.1 ግብርና ዘርፍ
8.2 በማህበራዊና በአገልግሎት ዘርፍ
8.3 በኢንዱስትሪ ዘርፍ
የኢንዱስትሪ ፖቴንሻል ሰርቨይ / / ጥናት መሠረት በከተማው ውስጥ
Copyrights 2019. . All Rights Reserved.
Developed by SNNPRS-SITB & SNNPRS-wza