አጠቃላይ ገጽታ
የዱጉና ፋንጎ ወረዳ ዋና ከተማ ቢጣና ከዞኑ ርዕሰ መዲና ሶዶ በስተምስራቅ በ46 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝና የቆዳ ስፋቱም 402 ካሬ ኪ.ሜትር ሲሆን በ27 የገጠር ቀበሌዎች እና በ6 የማዘጋጃ ቤት ከተሞች የተዋቀረ ነው፡፡ በአስተዳደሩ የሚገኙ የኢንቨስትመንት አማራጮች፤ የማዕድን ሀብት ክምችትና የቱሪስት መስህቦች እንደሚከተለዉ ቀርበዋል፡፡
1.1 ከባህር ወለል ከፍታ
ከባህር ወለል በላይ ከ1000 እስከ 2,500 ሜትር ከፍታ ያላቸው የመሬት ገጾች አሉት፡፡
1.2 የአየር ንብረት
የወረዳው አግሮኢኮሎጂን በተመለከተ 22.5% ደጋ፣ 23.4% ወይና ደጋ እና 54.1% ቆላ ነዉ፡፡ የዓመቱ አማካይ የሙቀት መጠን 17.6--22.5 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ነው፡፡ አማካይ ዓመታዊ የዝናብ መጠን ከ800 እስከ 1,200 ሚሊ ሜትር ነው፡፡
1.3 ሥነ-ሕዝብ
በ2009 ዓ.ም ከዞኑ ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በተገኘው የስታትስቲክስ መረጃ መሠረት የወረዳው አጠቃላይ የሕዝብ ብዛት 127,971 ሲሆን የሕዝብ ጥግግት 310 በስኳየር ኪ/ሜትር ነው፡፡
. የመሠረተ ልማት አቅርቦት ሁኔታ
2.1 መንገድ
የወረዳውን 3 ከተሞችን (ቀርጨጨ፣ ቢጠና እና ዲምቱ) ከሶዶ-ሐዋሳ አቋርጦ የሚያልፍ አስፋልት መንገድ እየተዘረጋ ያለ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ 36.5 ኪ/ሜትር የጠጠር እና 398.57 ኪ/ሜትር ጥሪጊያ መንገድ የተለያዩ የወረዳ ቀበሌዎችን እና አጎራባች ወረዳዎችን እርስ በርስ የሚያገናኝ መንገዶች አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
2.2 ስልክ፣ ኢንተርኔት እና የፖስታ አገልግሎት
በወረዳው ዋና ከተማ የሞባይልና የመደበኛ ስልክ አገልግሎት፣ እንዲሁም የኢንተርኔት አገልግሎት የሚሰጡ የግል ንግድ ማዕከላት እየተከፈቱ ይገኛሉ፡፡ አንድ የፖስታ አገልግሎት ሰጪ ተቋም በቢጠና ከተማ ይገኛል፡፡
2.3 መብራት
በወረዳው ውስጥ የሚገኙ የከተማ አከባቢዎች 24 ሰዓት የሃይደሮ ኤሌክትሪክ ኃይል መብራት አገልግሎት ያገኛሉ፡፡
2.4 የመጠጥ ውኃ አቅርቦት
የመጠጥ ውኃ አቅርቦትን በተመለከተ በእጅ ፓምፕ የሚሠራ የእጅ ጉድጓድ ( ) 3፣ ጥልቅ ጉድጓድ ስርጭት ( ) 7፣ የምንጭ ውኃ ስርጭት ( ) 1፣ ምንጭ ማጎልበት ( ) 5 ይገኛሉ፡፡ የወረዳው የመጠጥ ውኃ ሽፋን 36.407% ሲሆን በዘርፉ ያለውን ከፍተኛ ችግር ለማቃለል የጥልቅ ጓድጓድ ውኃ አገልግሎት ለመስጠት በተለያዩ ቀበሌዎች መስመር እየተዘረጋ ይገኛል፡፡
2.5 የገንዘብ ተቋማት፡-
የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ብቻ ለወረዳው ነዋሪዎች አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት ለመክፈት በዝግጅት ላይ ይገኛሉ፡፡
. የማህበራዊ አገልግሎት
3.1 ጤና
3.2 ትምህርት
መዋዕለ ሕጻናት ት/ቤት -------------------------- 4
አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (1-4ኛ ክፍል) ------ -------- 8
አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (1-8ኛ ክፍል) -------------- 39
ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት (9-10ኛ ክፍል) ------------ 7
መሰናዶ (11-12ኛ ክፍል) --------------------------- 2
. በመስኖ የሚለማ የእርሻ መሬት ሁኔታ
በወረዳው ውስጥ 3 የመስኖ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ በመሆናቸው የአከባቢው አርሶ አደር ተጠቃሚ ሲሆን ለአብነት ቢላቴ ኤታ መስኖ (627.77 ሄ/ር)፣ ብላቴ ጨርቾ መስኖ (859.17 ሄ/ር) እና ፋንጎ ቢጆ መስኖ (120 ሄ/ር) የመስኖ ፕሮጀክቶች ምርትና ምርታማነት ከማሳደግ አልፎ ለሀገርቱ ኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ ወረዳው ካለው የከርሰምድርና የገጸምድር ውኃ አቅርቦት ለአብነት ወንዞች (ብላቴ ወንዝ እና ጫራቄ ወንዝ) ከመኖሩ አንጻር እስካሁን በመስኖ የለማው መሬት መጠን በጣም ዝቅተኛ ከመሆኑም ባሻገር ወረዳው ከፍተኛ ለመስኖ አገልግሎት ሊውል የሚችል የውኃ ፖቴንሻል እንዳለ፣ ከፍተኛ የዝናብ መጠን መኖሩ እና ለም ዐፈር መኖሩ ለእርሻ ኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡
. በወረዳው የሚመረቱ ዋና ዋና ምርቶች
5.1 ዓመታዊ ሰብሎች
በቆሎ፣ ጤፍ፣ ማሽላ፣ ስንዴ፣ ቦሎቄ፣ ባቄላ፣ አተር፣ ሽንብራ፣ ገብስ፣ የሥራ ሥር ሰብሎች፣ ጥጥ፣ አትክልት (ቀይ ሽንኩርት፣ ቲማትም)፣ ቅመማ ቅመም (በርበሬ፣ ነጭ ሽንኩርት) ምርት፣
5.2 ቋሚ ሰብሎች
ፍራፍሬ (ሙዝ፣ ማንጎ፣ አቮካዶ፣ ፓፓያ)፣ ሽፈራው፣ ካሳቫ፣ እንሰት፣ ቡና፣ ጫት፣ ሾንኮራ አገዳ፣
. ለኢንቨስትመንት የተዘጋጀ መሬት
ተ.ቁ
ለማንፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ
ለንግድ እና ለማህበራዊ አገልግሎት
ለከተማ ግብርና
ለገጠር እርሻ ልማት
1
55.6 ሄ/ር
6 ሄ/ር
26 ሄ/ር
300 ሄ/ር
ምንጭ፡- ቢጣና ከተማ ማዘጋጃ ቤት እና የወረዳው እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽ/ቤት
ማሳሰቢያ፡- ለገጠር እርሻ ኢንቨስትመንት የተለዩ ቦታዎችን በተመለከተ በብላቴ ቀበሌ 300 ሄ/ር መሬት ከአቶ ዮናስ ሰርጎብርሃን ከተባለው ባለሀብት የተቀማ እንዲሁም በወረዳዉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽ/ቤት አማካይነት በተፋሰስ ሊለሙ የሚችሉ በ26 ቀበሌዎች የወል መሬት ሰርቨይ ተደርጎ የተካለለ ሲሆን ከቢጣና ማዘጋጃ ቤት በተገኘው መረጃ መሠረት 87.6 ሄ/ር ለተለያዩ አገልግሎቶች በከተማው መሠረታዊ ፕላን መሠረት የተዘጋጀ መሆኑን ታሳቢ ሊደረግ ይገባል፡፡
. ለኢንቨስትመንት ያለው አመቺነት
7.1 ለግብርና
7.2 ለአግሮ ኢንዱስትሪ
7.3 ለማህበራዊ አገልግሎት
የወረዳው የጤና ሽፋን 122.63% ቢሆንም በላቦራቶሪ እና በግል ፋርማሲ ተቋማት ሽፋን ክፍተት መኖሩን ያሳያል፤
የመዋዕለ ሕጻናት እና የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ተቋማት ብዛት ዝቅተኛ መሆኑ እንዲሁም በከፍተኛ የት/ት ተቋማት ወይም ኮሌጆች በወረዳው ውስጥ ያለመኖር ለግል ባለሀብት በመስኩ መሰማራት አመችነቱን ይጠቁማል፡፡
7.4 ለሆቴል፣ ለሪዞርት፣ ለሎጅ፣ ለመዝነኛ ፓርክ እና ቱሪዝም አገልግሎት
7.5 ለማዕድን፣ ኢነርጅ እና ለኮንስትራክሽን ዘርፍ
. የኢንቨስትመንት አማራጭ ዕድሎች
8.1 ግብርና ዘርፍ
8.2 በማህበራዊና በአገልግሎት ዘርፍ
8.3 በኢንዱስትሪ ዘርፍ
የኢንዱስትሪ ፖቴንሻል ሰርቨይ / / ጥናት መሠረት በከተማው ውስጥ
Copyrights 2019. . All Rights Reserved.
Developed by SNNPRS-SITB & SNNPRS-wza