አጠቃላይ ገጽታ
የዳሞት ወይዴ ወረዳ ዋና ከተማ በዴሳ ከዞኑ ርዕሰ መዲና ሶዶ በስተምስራቅ በ25 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝና የቆዳ ስፋቱም 352 ካሬ ኪ/ሜትር ሲሆን በ23 የገጠር ቀበሌዎች እና በ4 የማዘጋጃ ቤት ከተሞች የተዋቀረ ነው፡፡ በአስተዳደሩ የሚገኙ የኢንቨስትመንት አማራጮች፤ የማዕድን ሀብት ክምችትና የቱሪስት መስህቦች እንደሚከተለዉ ቀርበዋል፡፡
1.1 ከባህር ወለል ከፍታ
ከባህር ወለል በላይ ከ1,001 እስከ 2,500 ሜትር ከፍታ ያላቸው የመሬት ገጾች አሉት፡፡
1.2 የአየር ንብረት
የወረዳው አግሮኢኮሎጂን በተመለከተ 5% ደጋ፣ 60% ወይና ደጋ እና 35% ቆላ ነዉ፡፡ የዓመቱ አማካይ የሙቀት መጠን 17.6--25 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ነው፡፡ አማካይ ዓመታዊ የዝናብ መጠን ከ1,001 እስከ 1,400 ሚሊ ሜትር ነው፡፡
1.3 ሥነ-ሕዝብ
በ2009 ዓ.ም ከዞኑ ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በተገኘው የስታትስቲክስ መረጃ መሠረት የወረዳው አጠቃላይ የሕዝብ ብዛት 124,784 ሲሆን የሕዝብ ጥግግት 337 በስኳየር ኪ/ሜትር ነው፡፡
. የመሠረተ ልማት አቅርቦት ሁኔታ
2.1 መንገድ
የወረዳውን ዋና ከተማ በዴሳ ከሶዶ-ሐዋሳ አቋርጦ የሚያልፍ 26 ኪሎ ሜትር አስፋልት መንገድ የተዘረጋ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ 41 ኪ/ሜትር የጠጠር እና 960 ኪ/ሜትር ጥሪጊያ መንገድ የተለያዩ የወረዳ ቀበሌዎችን እና አጎራባች ወረዳዎችን እርስ በርስ የሚያገናኝ መንገዶች አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
2.2 ስልክ፣ ኢንተርኔት እና የፖስታ አገልግሎት
የሞባይልና የመደበኛ ስልክ አገልግሎት፣ እንዲሁም የኢንተርኔት አገልግሎት የሚሰጡ የግል ንግድ ማዕከሎች እየተከፈቱ ይገኛሉ፡፡ አንድ የፖስታ አገልግሎት ሰጪ ተቋም በበዴሳ ከተማ ይገኛል፡፡
2.3 መብራት
በወረዳው ውስጥ የሚገኙ የከተማ አከባቢዎች 24 ሰዓት የሃይደሮ ኤሌክትሪክ ኃይል መብራት አገልግሎት ያገኛሉ፡፡
2.4 የመጠጥ ውኃ አቅርቦት
የመጠጥ ውኃ አቅርቦትን በተመለከተ የጥልቅ ጉድጓድ ስርጭት ( ) 2፣ የምንጭ ውኃ ስርጭት ( ) 3፣ ምንጭ ማጎልበት ( ) 10 ይገኛሉ፡፡ የወረዳው የመጠጥ ውኃ ሽፋን 57.84% ሲሆን በዘርፉ ያለውን ከፍተኛ ችግር ለማቃለል የጥልቅ ጓድጓድ ውኃ አገልግሎት ለመስጠት በተለያዩ ቀበሌዎች መስመር እየተዘረጋ ይገኛል፡፡
2.5 የገንዘብ ተቋማት፡-
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ለወረዳው ነዋሪዎች አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡
. የማህበራዊ አገልግሎት
3.1 ጤና
3.2 ትምህርት
መዋዕለ ሕጻናት ት/ቤት -------------------------- 3
አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (1-4ኛ ክፍል) -------------- 2
አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (1-8ኛ ክፍል) -------------- 31
ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት (9-10ኛ ክፍል) ------------ 3
መሰናዶ (11-12ኛ ክፍል) --------------------------- 1
የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ፖሊቴክኒክ ----------- 1 (አገልግሎት መስጠት ያልጀመረ)
. በመስኖ የሚለማ የእርሻ መሬት ሁኔታ
በወረዳው ውስጥ 2 የመስኖ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ በመሆናቸው የአከባቢው አርሶ አደር ተጠቃሚ ሲሆን ለአብነት ቢሳሬ መስኖ (180.58 ሄ/ር) እና በዴሳ መስኖ (80 ሄ/ር) የመስኖ ፕሮጀክቶች 100% አገልግሎት መስጠት ባይጀምሩም ለአከባቢው ማህበረሰብ ምርትና ምርታማነት ከማሳደግ አንጻር አዎንታዊ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ ወረዳው ካለው የከርሰ ምድርና የገጸ ምድር ውኃ አቅርቦት ለአብነት ወንዞች (ቢሳሬ ወንዝ እና በዴሳ ወንዝ) ከመኖሩ አንጻር እስካሁን በመስኖ የለማው መሬት መጠን በጣም ዝቅተኛ ከመሆኑም ባሻገር ወረዳው ከፍተኛ ለመስኖ አገልግሎት ሊውል የሚችል የውኃ ፖቴንሻል እንዳለ፣ ከፍተኛ የዝናብ መጠን መኖሩ እና ለም ዐፈር መኖሩ ለእርሻ ኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡
. በወረዳው የሚመረቱ ዋና ዋና ምርቶች
5.1 ዓመታዊ ሰብሎች
በቆሎ፣ ጤፍ፣ ማሽላ፣ ስንዴ፣ ቦሎቄ፣ ባቄላ፣ አተር፣ ሽንብራ፣ ገብስ፣ የሥራ ሥር ሰብሎች፣ ጥጥ፣ አትክልት (ቀይ ሽንኩርት፣ ቲማትም)፣ ቅመማ ቅመም ምርት፣
5.2 ቋሚ ሰብሎች
ፍራፍሬ (ሙዝ፣ ማንጎ፣ አቮካዶ፣ ፓፓያ፣ ብርቱካን፣ ሎሚ)፣ ሽፈራው/ሞሪንጋ፣ ካሳቫ፣ እንሰት፣ ቡና፣ ጫት፣ ሾንኮራ አገዳ፣
. ለኢንቨስትመንት የተዘጋጀ መሬት
ተ.ቁ
ለኢንዱስትሪ
በሄ/ር
ለንግድ እና ለማህበራዊ አገልግሎት በሄ/ር
ለከተማ ግብርና በሄ/ር
ለገጠር እርሻ ልማት በሄ/ር
1
138.7
22.9
85.34
550 ሄ/ር
ምንጭ፡- በዴሣ ከተማ ማዘጋጃ ቤት እና የወረዳው እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽ/ቤት
ማሳሰቢያ፡- ለገጠር እርሻ ኢንቨስትመንት የተለዩ ቦታዎችን በተመለከተ በኤሎ ኤራሾ ቀበሌ ቀበሌ 550 ሄ/ር መሬት ከባለሀብቶች የተቀማ እና የተቀነሰ መሬት በተጨማሪ በወረዳዉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽ/ቤት አማካይነት በተፋሰስ ሊለሙ የሚችሉ በ23 ቀበሌዎች የወል መሬት ሰርቨይ ተደርጎ የተካለለው ለአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ሊውል የሚችል ሲሆን ከበዴሣ ማዘጋጃ ቤት በተገኘው መረጃ መሠረት ከ246 ሄ/ር በላይ መሬት ለተለያዩ አገልግሎቶች በከተማው መሠረታዊ ፕላን መሠረት የተዘጋጀ መሆኑን ታሳቢ ሊደረግ ይገባል፡፡
. ለኢንቨስትመንት ያለው አመቺነት
7.1 ለግብርና
7.2 ለአግሮ ኢንዱስትሪ
7.3 ለማህበራዊ አገልግሎት
የወረዳው የጤና ሽፋን 85.79% ደረሰ ቢሆንም በላቦራቶሪ እና በግል ፋርማሲ ተቋማት ሽፋን ክፍተት መኖሩን ያሳያል፤
የመዋዕለ ሕጻናት እና የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ተቋማት ብዛት ዝቅተኛ መሆኑ እንዲሁም በከፍተኛ የት/ት ተቋማት ወይም ኮሌጆች በወረዳው ውስጥ ያለመኖር ለግል ባለሀብት በመስኩ መሰማራት አመችነቱን ይጠቁማል፡፡
7.4 ለሆቴል፣ ለሪዞርት፣ ለሎጅ፣ ለመዝነኛ ፓርክ እና ቱሪዝም አገልግሎት
7.5 ለማዕድን፣ ኢነርጅ እና ለኮንስትራክሽን ዘርፍ
. የኢንቨስትመንት አማራጭ ዕድሎች ባለሀብቶች
8.1 ግብርና ዘርፍ
8.2 በማህበራዊና በአገልግሎት ዘርፍ
8.3 በኢንዱስትሪ ዘርፍ፡- የኢንዱስትሪ ፖቴንሻል ሰርቨይ / / ጥናት መሠረት በከተማው ውስጥ
Copyrights 2019. . All Rights Reserved.
Developed by SNNPRS-SITB & SNNPRS-wza