• Call Us
  • +251465512106

የሶዶ ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር

 አጠቃላይ ገጽታ     

የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ከዞኑ ርዕሰ መዲና ሶዶ ከተማን አዋስኖ የሚገኝና የቆዳ ስፋቱም 347.8 ካሬ ኪሎ ሜትር ሲሆን በ31 የገጠር ቀበሌዎች እና በ6 የማዘጋጃ ቤት ከተሞች የተዋቀረ ነው፡፡ በአስተዳደሩ የሚገኙ የኢንቨስትመንት አማራጮች፤ የማዕድን ሀብት ክምችትና የቱሪስት መስህቦች እንደሚከተለዉ ቀርበዋል፡፡

1.1 ከባህር ወለል  ከፍታ

ከባህር ወለል በላይ ከ1,501 እስከ 2,958 ሜትር ከፍታ ያላቸው የመሬት ገጾች አሉት፡፡

1.2 የአየር ንብረት

የወረዳው አግሮኢኮሎጂን በተመለከተ 13% ደጋ እና 87% ወይና ደጋ ነዉ፡፡ የዓመቱ አማካይ የሙቀት መጠን 12.6--27.5 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ነው፡፡ አማካይ ዓመታዊ የዝናብ መጠን ከ1,201 እስከ 1,600 ሚሊ ሜትር ነው፡፡

1.3 ሥነ-ሕዝብ

በ2009 ዓ.ም ከዞኑ ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በተገኘው የስታትስቲክስ መረጃ መሠረት የወረዳው አጠቃላይ የሕዝብ ብዛት 179,109 ሲሆን የሕዝብ ጥግግት 600 በስኳየር ኪ/ሜትር ነው፡፡

  . የመሠረተ ልማት አቅርቦት ሁኔታ  

2.1 መንገድ

ወረዳው ውስጥ 36.5 ኪሎ ሜትር አስፋልት መንገድ፣ 18 ኪ/ሜትር የጠጠር እና 642.3 ኪ/ሜትር ጥሪጊያ መንገዶች ሲኖረው በአብዘኛው የወረዳው ቀበሌዎች ከዞንና ከክልል ብሎም ወረዳን ከወረዳ እንዲሁም እያንዳንዱን የገጠር ቀበሌም ጭምር በዋናና በውስጥ ለውስጥ መንገዶች እርስ በእርስ የተገናኘ ነው፡፡

2.2 ስልክ፣ ኢንተርኔት እና የፖስታ አገልግሎት

የሞባይልና የመደበኛ ስልክ አገልግሎት፣ እንዲሁም የኢንተርኔት አገልግሎት የሚሰጡ የግል ንግድ ማዕከላት እየተከፈቱ ይገኛሉ፡፡ አንድ የፖስታ አገልግሎት ሰጪ ተቋም በሶዶ ከተማ ይገኛል፡፡

2.3 መብራት

በወረዳው ውስጥ የሚገኙ የከተማ አከባቢዎች 24 ሰዓት የሃይደሮ ኤሌክትሪክ ኃይል መብራት አገልግሎት ያገኛሉ፡፡

 

2.4 የመጠጥ ውኃ አቅርቦት

የመጠጥ ውኃ አቅርቦትን በተመለከተ በእጅ ፓምፕ የሚሠራ የእጅ ጉድጓድ (                                    ) 28፣ በእጅ ፓምፕ የሚሠራ ጥልቅ ጉድጓድ (                                   ) 35፣ ጥልቅ ጉድጓድ ስርጭት (                       ) 5፣ የምንጭ ውኃ ስርጭት (                         ) 12፣ ምንጭ በቦታው ማጎልበት (           ) 54 ይገኛሉ፡፡ የወረዳው የመጠጥ ውኃ ሽፋን 65.84% ሲሆን በዘርፉ ያለውን ከፍተኛ ችግር ለማቃለል የጥልቅ ጓድጓድ ውኃ አገልግሎት ለመስጠት በተለያዩ ቀበሌዎች መስመር እየተዘረጋ ይገኛል፡፡

2.5 የገንዘብ ተቋማት፡-

የወረዳው ነዋሪዎች ዘመናዊ የባንክና ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት አገልግሎትን ከወረዳው ዋና ከተማ ሶዶ ውስጥ ከሚገኙ የፋይናንስ ተቋማት ያገኛሉ፡፡

   . የማህበራዊ አገልግሎት  

3.1 ጤና

  • ጤና ጣቢያ /             / ------------- 8
  • ጤና ኬላ /           / ------------------ 38
  • የመጀመሪያ ደረጃ ክሊንክ /      / ------- 18 (የግል)  
  • መድኃኒት ቤት /        / --------------- 9 (8 የመንግስት እና 1 የመያድ)
  • ላቦራቶሪ --------------------------------------- 9 (8 የመንግስት እና 1 የመያድ)
  • የጤና ሽፋን ----------------------------------- 104.6%

3.2 ትምህርት

መዋዕለ ሕጻናት ት/ቤት -------------------------- 6

አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (1-4ኛ ክፍል) -------------- 2

አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (1-8ኛ ክፍል) -------------- 34

ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት (9-10ኛ ክፍል) ------------ 4

መሰናዶ (11-12ኛ ክፍል) --------------------------- 1

  . በመስኖ የሚለማ የእርሻ መሬት ሁኔታ

በወረዳው ውስጥ 5 የመስኖ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ በመሆናቸው የአከባቢው አርሶ አደር ተጠቃሚ ሲሆን ለአብነት ኮተገንት መስኖ በሼላ ቦርኮሼ ቀበሌ (60 ሄ/ር)፣ ጫሬ ሀማሳ መስኖ በቦሳ ቃጫ ቀበሌ (25.18 ሄ/ር)፣ ታካቻ መስኖ በሼላ ኮዶ ቀበሌ (150 ሄ/ር)፣ ታንዶ መስኖ በዛላ ሻሻ ቀበሌ (35 ሄ/ር)፣ እና ቡሻ መስኖ በቡሻ ቀበሌ (25 ሄ/ር) የመስኖ ፕሮጀክቶች 100% አገልግሎት መስጠት ባይጀምሩም ለአከባቢው ማህበረሰብ ምርትና ምርታማነት ከማሳደግ አንጻር አዎንታዊ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ ወረዳው ካለው የከርሰ ምድርና የገጸ ምድር ውኃ አቅርቦት ለአብነት ወንዞች (ሀማሳ ወንዝ፣ ሊንታላ፣ ዋጃ፣ ቢሳሬ፣ ታካቻ እና ልቂምሴ ወንዝ) ከመኖሩ አንጻር እስካሁን በመስኖ የለማው መሬት መጠን በጣም ዝቅተኛ ከመሆኑም ባሻገር ወረዳው ከፍተኛ ለመስኖ አገልግሎት ሊውል የሚችል የውኃ ፖቴንሻል እንዳለ፣ ከፍተኛ የዝናብ መጠን መኖሩ እና ለም ዐፈር መኖሩ ለእርሻ ኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡

 . በወረዳው የሚመረቱ ዋና ዋና ምርቶች

5.1 ዓመታዊ ሰብሎች

በቆሎ፣ ጤፍ፣ ማሽላ፣ ስንዴ፣ ቦሎቄ፣ ባቄላ፣ አተር፣ ሽንብራ፣ ገብስ፣ የሥራ ሥር ሰብሎች፣ አትክልት (ቀይ ሽንኩርት፣ ቲማትም)፣ ቅመማ ቅመም ምርት፣

5.2 ቋሚ ሰብሎች

ፍራፍሬ (ሙዝ፣ ማንጎ፣ አቮካዶ፣ ፓፓያ፣ ብርቱካን)፣ እንሰት፣ ቡና፣  

  . ለኢንቨስትመንት የተዘጋጀ መሬት

ተ.

የቀበሌው  

ለኢንዱስትሪ በሄ/ር  

ለንግድና አገልግሎት በሄ/ር  

ለማህበራዊ አገልግሎት በሄ/ር

ለገጠር እርሻ ልማት በሄ/ር

1

ዳልቦ ከተ

3.51 ሄ/

774.54

13.25 ሄ/

------

2

ሀባ ገረራ

 ---

------

-----

130 ሄ/ር

  ምንጭ፡- ዳልቦ ከተማ ማዘጋጃ ቤት እና የወረዳው እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽ/ቤት

ማሳሰቢያ፡- ለገጠር እርሻ ኢንቨስትመንት የተለዩ ቦታዎችን በተመለከተ በሀባ ገሬራ ቀበሌ ቀበሌ 130 ሄ/ር መሬት በተጨማሪ በወረዳዉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽ/ቤት አማካይነት በተፋሰስ ሊለሙ የሚችሉ በተለያዩ ቀበሌዎች የወል መሬት ሰርቨይ ተደርጎ የተካለለው ለአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ሊውል የሚችል ሲሆን ከዳልቦ ማዘጋጃ ቤት በተገኘው መረጃ መሠረት ከ791 ሄ/ር በላይ መሬት ለተለያዩ አገልግሎቶች በከተማው መሠረታዊ ፕላን መሠረት የተዘጋጀ መሆኑን ታሳቢ ሊደረግ ይገባል፡፡

   . ለኢንቨስትመንት ያለው አመቺነት

7.1 ለግብርና

  • ሰፊ በመስኖ የሚለማ የአርሶ አደር ማሳ እና የወል መሬት መኖሩ፣
  • ዓመታዊ አማካይ የዝናብ መጠን ከፍተኛ መሆኑ፣
  • በወረዳው ውስጥ ዓመቱን ሙሉ የማይደርቁ ወንዞች በመኖራቸው እንዲሁም በተፋሰስ የለሙና የተካለሉ ሰፊ ቦታዎች ያሉት በመሆኑ በንብ ማነብ፣ በበሬ ድለባ፣ በበግ ማሞከት፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት፣ በዘመናዊ እንሰሳት ዕርባታ፣ ለዶሮ ዕርባታ ለማካሄድ ምቹ መሆኗ፣
  • በልማት ሥራ ላይ ለማዋል በቂ የሰው ኃይል /የተማረ እና የጉልበት/ መኖሩ፣
  • በለሙ ተፋሰሶች እና በአርሶ አደር ማሳ የተሻሻለ መኖ፣ ምጥን መኖ፣ የተለያዩ የሰብል ተረፈ ምርቶች፣ የተፈጥሮ ግጦሽ መኖ አቅርቦት መኖሩ፤
  • እንስሳት ዕርባታ እና የዳልጋ ከብት ድለባ ለማካሄድ ከፍተኛ የቀንድ ከብት ክምችት፣ ውኃ እና የግብይት ማዕከላት መኖሩ፤ በዞን አቀፍም ሆነ ሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የገበያ ፍላጎት መኖሩ፣
  • የተሻሻለ የእንስሳት ዝሪያ እየተስፋፋ መሆኑ (በሰው ሰራሽ ዘዴ በማዳቀል)፤
  • ከፍተኛ የሀገረሰብና የተሻሻለ የበግ እና የዶሮ አቅርቦት መኖሩ፤
  • ለንብ አበባ ቀሰማ ምቹ የሆኑ የተፈጥሮ ደኖች፣ በለሙ ተፋሰሶች፣ የፍራፍሬ ዛፎች መኖራቸው፤
  • ከፍተኛ የወተት ምርት፣ የወተት እና ተዋጽኦ ምርት ፍላጎት እንዲሁም የመስሪያ ቦታና የመሠረተ ልማት አቅርቦት መኖሩ ለኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ የተመቻቹ ሁኔታዎች ናቸው፡፡

7.2 ለአግሮ ኢንዱስትሪ

  • ከአርሶ አደሩ የሚገኙትን የግብርና ምርቶችን (በአውትግራውር ከአርሶ አደሩ ጋር ትስስር በመፍጠር) በጥሬ ዕቃነት ተጠቅሞ በማቀነባበር እስከ ውጪ ገበያ ድረስ ለሚያቀርቡ ባለሀብቶች መሬቱ አመቺነት ያለው በመሆኑ ያለውጣውርድ ማግኘት ይቻላል፤
  • ለተለያዩ ፋብሪካዎች በጥሬ ዕቃነት ሊያገለግሉ የሚችሉ የግብርና ምርቶች የሆኑ እንደ አቮካዶ፣ ቡና፣ ቲማቲም፣ ሙዝ፣ ቦሎቄ እና እንስሳት ሀብት በቅርብ መገኘታቸዉ፤
  • የወተት እና የወተት ተዋጽኦ ለማቀነባበር ከፍተኛ የወተት ምርት መኖሩ፣
  • የሥጋ ምርት (የዳልጋ ከብት፣ የዶሮ፣ ወዘተ) ለማቀነባበር የተሻሻሉ ዝሪያ፣ የተዳቀሉ እና የሀገረሰብ ዘር አቅርቦት መኖሩ፣
  • ምጥን የከብቶች መኖ ለማዘጋጀት በቂ የግብዓት አቅርቦት እና ከፍተኛ የምርት ፍላጎት መኖሩ፤ በአሁኑ ወቅት በተፋሰስ በለሙ ቦታዎች በስፋት እየተመረተ በመሆኑ እንዲሁም በቀላሉ ሊለማ የሚችልና በቂ የተዘጋጀ ቦታ መኖሩ፤   

 

7.3 ለማህበራዊ አገልግሎት

የወረዳው የጤና ሽፋን 104.6% የደረሰ ቢሆንም በላቦራቶሪ እና በግል ፋርማሲ ተቋማት ሽፋን ክፍተት መኖሩን ያሳያል፤

የመዋዕለ ሕጻናት እና የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ተቋማት ብዛት ዝቅተኛ መሆኑ እንዲሁም በከፍተኛ የት/ት ተቋማት ወይም ኮሌጆች በወረዳው ውስጥ ያለመኖር ለግል ባለሀብት በመስኩ መሰማራት አመችነቱን ይጠቁማል፡፡

7.4 ለሆቴል፣ ለሪዞርት፣ ለሎጅ፣ ለመዝነኛ ፓርክ እና ቱሪዝም አገልግሎት

  • በወረዳው ዋና ከተማም ሆነ በሌሎች የማዘጋጃ ቤቶች ውስጥ ደረጃውን የጠበቀ ሆቴል፣ ፔንሲዮን እና የመዝነኛ ማዕከላት ያለመኖሩ በዘርፉ የገበያ ክፍተት መኖሩን ያሳያል፤
  • በቁጥር በዛ ያሉ የቁም ትክል ድንጋይ (ቦሳ ቃጫ ቀበሌ፣ ጉሩሙ ወይዴ፣ ኦፋ ሴሬ፣ ሶዶ ቦላ ዱፓ ቀበሌ፣ ቦቄና ሶዶ፣ ዋጭቃ ቡሻ፣ ሶሬ ዋሙራ እና በዳልቦ ወገኔ ቀበሌ የሚገኙ)፣
  • ዳሞት ተራራ እና የካርቦን ፕሮጀክት (በዳሞት ዋጃ ቀበሌ) ለሎጅ ግንባታ፣ ለማራኪ እይታ /ለፓናሮሚክ ቪዉ/፣ ለአድቬንቸር ቱሪዝም እና ለመዝነኛ አገልግሎት፣  
  • ፏፏቴዎች (የአሚጎዳ ፏፏቴ)፣ እንዲሁም ዋሻዎች (ሞቼና ቦራጎ ዋሻ እና ኤሊ ዋሻ ) ለቱሪስት መስህብነት ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡
  • በወረዳው የሚገኙ ሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ የቱሪስት መስህቦች ቁጥር በርካታ በመሆኑ ቱሪስት የመሳብ አቅም ከፍተኛ ስለሆነ እንዲሁም ለዘርፉ ኢንቨስትመንት በቂ የለማ ቦታ የተዘጋጀ በመሆኑ ባለሃብቱ ቢሠማራበት አዋጭ ነዉ፡፡

7.5 ለማዕድን፣ ኢነርጅ እና ለኮንስትራክሽን ዘርፍ

  • ለኮንስትራክሽን የሚያገለግሉ ጥሬ ዕቃዎች በአከባቢዉ መገኘታቸዉ፣ ነጭ ድንጋይ፣ ጥቁር ድንጋይ፣ ሴሌክቲድ ማቴሪያል የመሳሰሉት በከፍተኛ መጠን መኖሩ፤
  • ትራካይት የሚባል የኢንዱስትሪ ማዕድን በጉሩሞ ወይዴ ቀበሌ በከፍተኛ ክምችት መኖሩ፣
  • የታሸገ የማዕድን ውኃ ለማምረት በቂ የከርሰ ምድር ውኃ ምንጮች መኖሩ፤

    . የኢንቨስትመንት አማራጭ ዕድሎች

8.1 ግብርና ዘርፍ

  • የወተትና ሥጋ ከብት ማርባትና የዳልጋ ከብት ማድለብ፣
  • በዶሮ ዕርባታና እንቁላል ምርት፣
  • የእንስሳት መኖ ዘር ማባዛትና ማልማት፣
  • አትክልትና ፍራፍሬ ልማት (ማንጎ፣ አቦካዶ፣ ሙዝ)፣
  • ቅመማ ቅመም (ነጭ ሽንኩርት፣ በርበሬ/ቃሪያ) ልማት፣
  • በንብ ማነብ፣ በበግ ማሞከት፣
  • የአገዳ ሰብሎችን ማምረት፣
  • ቡና እና ሌሎች ገበያ ተኮር ሰብሎች ማምረት፣

8.2 በማህበራዊና በአገልግሎት ዘርፍ

  • በሆቴልና ቱሪዝም ከካፌ እስከ ባለኮከብ ሆቴል
  • በትምህርት ዘርፍ ከመዋዕለ ህፃናት እስከ ኮሌጅ፤
  • በጤና ዘርፍ በክሊኒክ፣ ላቦራቶሪ፣ ፋርማሲ፣ በእንስሳት ህክምና ማዕከላት፣
  • ለሎጅ፤ ለሪዞርትና መዝናኛ ማዕከል

8.3 በኢንዱስትሪ ዘርፍ

የኢንዱስትሪ ፖቴንሻል ሰርቨይ /   / ጥናት መሠረት በከተማው ውስጥ

  • ለምግብና ምግብ ውጤቶች ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣
  • ለሥጋና የሥጋ ውጤቶች ማቀነባበሪያ፣
  • የወተትና የወተት ውጤቶች ማቀነባበሪያ፣
  • ለአትክልትና ፍራፍሬ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣
  • የእንስሳት መኖ ዘር ማባዣ፣ ማቀነባበሪያና ማሸጊያ ፋብሪካ፣
  • የማዕድን ውኃ ማሸጊያ ፋብሪካ፣
  • በቡና መፈልፈያና ማቀነባበሪያ፣
  • ትራካይት የሚባል የኢንዱስትሪ ማዕድን ማምረት