• Call Us
  • +251465512106

የዳሞት ሶሬ ወረዳ አስተዳደር

 አጠቃላይ ገጽታ    

የዳሞት ሶሬ ወረዳ ዋና ከተማ ጉኑኖ ከዞኑ ርዕሰ መዲና ሶዶ በስተ-ምዕራብ በ17 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኛና የቆዳ ስፋቱም 180.9 ካሬ ኪሜትር ሲሆን በ18 የገጠር ቀበሌዎች እና በ4 የማዘጋጃ ቤት ከተሞች የተዋቀረ ነው፡፡ በአስተዳደሩ የሚገኙ የኢንቨስትመንት አማራጮች፤ የማዕድን ሀብት ክምችትና የቱሪስት መስህቦች እንደሚከተለዉ ቀርበዋል፡፡

1.1 ከባህር ወለል ከፍታ

ከባህር ወለል በላይ ከ1,500 እስከ 2,500 ሜትር ከፍታ ያላቸው የመሬት ገጾች አሉት፡፡

1.2 የአየር ንብረት

የወረዳው አግሮኢኮሎጂን በተመለከተ 7% ደጋ፤ 87% ወይና ደጋ እና 6% ቆላ ነዉ፡፡ የዓመቱ አማካይ የሙቀት መጠን 17.6--22.5 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ነው፡፡ አማካይ ዓመታዊ የዝናብ መጠን ከ1200 እስከ 1,600 ሚሊ ሜትር ነው፡፡

1.3 ሥነ-ሕዝብ

በ2009 ዓ.ም ከዞኑ ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በተገኘው የስታትስቲክስ መረጃ መሠረት የወረዳው አጠቃላይ የሕዝብ ብዛት 134,804 ሲሆን የሕዝብ ጥግግት 723 በካሬ ኪ/ሜትር ነው፡፡

  . የመሠረተ ልማት አቅርቦት ሁኔታ   

2.1 መንገድ

ወረዳው ውስጥ 57 ኪ/ሜትር የጠጠር እና 365.5 ኪ/ሜትር ጥሪጊያ መንገዶች ሲኖሩት በአብዘኛው የወረዳው ቀበሌዎች ከዞንና ከክልል ብሎም ወረዳን ከወረዳ እንዲሁም እያንዳንዱን የገጠር ቀበሌም ጭምር በዋናና በውስጥ ለውስጥ መንገዶች እርስ በእርስ የተገናኘ ነው፡፡

2.2 ስልክ፣ ኢንተርኔት እና የፖስታ አገልግሎት

የሞባይልና የመደበኛ ስልክ አገልግሎት፣ እንዲሁም የኢንተርኔት አገልግሎት የሚሰጡ የግል ንግድ ማዕከሎች እየተከፈቱ ይገኛሉ፡፡ አንድ የፖስታ አገልግሎት ሰጪ ተቋም በጉኑኖ ከተማ ይገኛል፡፡

2.3 መብራት

በወረዳው ውስጥ የሚገኙ የከተማ አከባቢዎች 24 ሰዓት የሃይደሮ ኤሌክትሪክ ኃይል መብራት አገልግሎት ያገኛሉ፡፡

2.4 የመጠጥ ውኃ አቅርቦት

የመጠጥ ውኃ አቅርቦትን በተመለከተ በእጅ ፓምፕ የሚሠራ የእጅ ጉድጓድ (                                    ) 17፣ በእጅ ፓምፕ የሚሠራ ጥልቅ ጉድጓድ (                                   ) 43፣ ጥልቅ ጉድጓድ ስርጭት (                       ) 4፣ የምንጭ ውኃ ስርጭት (                         ) 3 እና ምንጭ በቦታው ማጎልበት (           ) 63 ይገኛሉ፡፡ የወረዳው የመጠጥ ውኃ ሽፋን 61.76% ሲሆን በዘርፉ ያለውን ከፍተኛ ችግር ለማቃለል የጥልቅ ጓድጓድ ውኃ አገልግሎት ለመስጠት በተለያዩ ቀበሌዎች መስመር እየተዘረጋ ይገኛል፡፡

2.5 የገንዘብ ተቋማት፡-

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም እንዲሁም ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት እየተከፈቱ ይገኛሉ፡፡

   . የማህበራዊ አገልግሎት     

3.1 ጤና

  • ጤና ጣቢያ /             / ------------- 5
  • ጤና ኬላ /           / ------------------ 17
  • የመጀመሪያ ደረጃ ክሊንክ /      / -------- 13 (የግል)  
  • መድኃኒት ቤት /        / --------------- 5 (የመንግስት)
  • መድኃኒት መደብር (           ) ------ 1 (የግል)
  • ላቦራቶሪ ---------------------------------------  5 (የመንግስት)
  • የጤና ሽፋን -----------------------------------  87%

3.2 ትምህርት

መዋዕለ ሕጻናት ት/ቤት --------------------------- 2   

አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (1-4ኛ ክፍል) -------------- 5

አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (1-8ኛ ክፍል) -------------- 20

ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት (9-10ኛ ክፍል) ------------ 3

መሰናዶ (11-12ኛ ክፍል) --------------------------- 1

  . በመስኖ የሚለማ የእርሻ መሬት ሁኔታ                        

በወረዳው ውስጥ 1 የመስኖ ፕሮጀክት ተግባራዊ በመሆኑ የአከባቢው አርሶ አደር ተጠቃሚ ሲሆን ለአብነት ብተቴ መስኖ በጉሩሞ ላዲሳ ቀበሌ (110 ሄ/ር) አገልግሎት እየሰጠ በመሆኑ ለአከባቢው ማህበረሰብ ምርትና ምርታማነት ከማሳደግ አንጻር አዎንታዊ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛል፡፡ ከዚሁ በተጨማሪ ወረዳው ካለው የከርሰ ምድርና የገጸ ምድር ውኃ አቅርቦት ለአብነት ወንዞች (ታካቻ፣ ማሬ፣ አክሪሳ እና ቁሌ ወንዞች) ከመኖሩ አንጻር እስካሁን በመስኖ የለማው መሬት መጠን በጣም ዝቅተኛ ከመሆኑም ባሻገር ወረዳው ከፍተኛ ለመስኖ አገልግሎት ሊውል የሚችል የውኃ ፖቴንሻል እንዳለ፣ ከፍተኛ የዝናብ መጠን መኖሩ እና ለም ዐፈር መኖሩ ለእርሻ ኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡

 

 . በወረዳው የሚመረቱ ዋና ዋና ምርቶች  

5.1 ዓመታዊ ሰብሎች

በቆሎ፣ ጤፍ፣ ማሽላ፣ ስንዴ፣ ቦሎቄ፣ ባቄላ፣ አተር፣ ገብስ፣ የሥራ ሥር ሰብሎች፣ አትክልት (ቀይ ሽንኩርት፣ ቲማትም)፣ ቅመማ ቅመም ምርት (ዝንጅብል፣ ዕርድ)፣

5.2 ቋሚ ሰብሎች

ፍራፍሬ (ሙዝ፣ ማንጎ፣ አቮካዶ፣ ፓፓያ፣ ብርቱካን)፣ እንሰት፣ ቡና፣

  . ለኢንቨስትመንት የተዘጋጀ መሬት፡-

ተ.

ለኢንዱስትሪ  

ለንግድ፣ ለአገልግሎት፣ ለሎጅ፣ ለሪል ስቴትና ለሌሎች  

ለከተማ ግብርና

ለማህበራዊ አገልግሎት  

1

 20 ሄ/

166 ሄ/

110.82 ሄ/

 24 ሄ/

     ምንጭ፡- ጉኑኖ ከተማ ማዘጋጃ ቤት እና የወረዳው እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽ/ቤት

ማሳሰቢያ፡- ከወረዳው ከተማ ልማት ጽ/ቤት እና ከጉኑኖ ማዘጋጃ በተገኘው መረጃ መሠረት ከ310 ሄ/ር በላይ መሬት ለተለያዩ አገልግሎቶች በከተማው መሠረታዊ ፕላን መሠረት የተዘጋጀ መሆኑን ታሳቢ ሊደረግ ይገባል፡፡

   . ለኢንቨስትመንት ያለው አመቺነት

7.1 ለግብርና          

  • ሰፊ በመስኖ የሚለማ የአርሶ አደር ማሳ እና የወል መሬት መኖሩ፣
  • ዓመታዊ አማካይ የዝናብ መጠን ከፍተኛ መሆኑ፣
  • በወረዳው ውስጥ ዓመቱን ሙሉ የማይደርቁ ወንዞች በመኖራቸው እንዲሁም በተፋሰስ የለሙና የተካለሉ ሰፊ ቦታዎች ያሉት በመሆኑ በንብ ማነብ፣ በበሬ ድለባ፣ በበግ ማሞከት፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት፣ በዘመናዊ እንሰሳት ዕርባታ፣ ለዶሮ ዕርባታ ለማካሄድ ምቹ መሆኗ፣
  • በልማት ሥራ ላይ ለማዋል በቂ የሰው ኃይል /የተማረ እና የጉልበት/ መኖሩ፣
  • በለሙ ተፋሰሶች እና በአርሶ አደር ማሳ የተሻሻለ መኖ፣ ምጥን መኖ፣ የተለያዩ የሰብል ተረፈ ምርቶች፣ የተፈጥሮ ግጦሽ መኖ አቅርቦት መኖሩ፤
  • እንስሳት ዕርባታ እና የዳልጋ ከብት ድለባ ለማካሄድ ከፍተኛ የቀንድ ከብት ክምችት፣ ውኃ እና የግብይት ማዕከላት መኖሩ፤ በዞን አቀፍም ሆነ ሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የገበያ ፍላጎት መኖሩ፣
  • የተሻሻለ የእንስሳት ዝሪያ እየተስፋፋ መሆኑ (በሰው ሰራሽ ዘዴ በማዳቀል)፤
  • ከፍተኛ የሀገረሰብና የተሻሻለ የበግ እና የዶሮ አቅርቦት መኖሩ፤
  • ለንብ አበባ ቀሰማ ምቹ የሆኑ የተፈጥሮ ደኖች፣ በለሙ ተፋሰሶች፣ የፍራፍሬ ዛፎች መኖራቸው፤
  • ከፍተኛ የወተት ምርት፣ የወተት እና ተዋጽኦ ምርት ፍላጎት እንዲሁም የመስሪያ ቦታና የመሠረተ ልማት አቅርቦት መኖሩ ለኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ የተመቻቹ ሁኔታዎች ናቸው፡፡

7.2 ለአግሮ ኢንዱስትሪ

  • ከአርሶ አደሩ የሚገኙትን የግብርና ምርቶችን (በአውትግራውር ከአርሶ አደሩ ጋር ትስስር በመፍጠር) በጥሬ ዕቃነት ተጠቅሞ በማቀነባበር እስከ ውጪ ገበያ ድረስ ለሚያቀርቡ ባለሀብቶች መሬቱ አመቺነት ያለው በመሆኑ ያለውጣውርድ ማግኘት ይቻላል፤
  • ለተለያዩ ፋብሪካዎች በጥሬ ዕቃነት ሊያገለግሉ የሚችሉ የግብርና ምርቶች የሆኑ እንደ አቮካዶ፣ ቡና፣ ዝንጅብል፣ ቲማቲም፣ ሙዝ፣ ቦሎቄ እና እንስሳት ሀብት በቅርብ መገኘታቸዉ፤
  • የወተት እና የወተት ተዋጽኦ ለማቀነባበር ከፍተኛ የወተት ምርት መኖሩ፣
  • የሥጋ ምርት (የዳልጋ ከብት፣ የዶሮ፣ ወዘተ) ለማቀነባበር የተሻሻሉ ዝሪያ፣ የተዳቀሉ እና የሀገረሰብ ዘር አቅርቦት መኖሩ፣
  • ምጥን የከብቶች መኖ ለማዘጋጀት በቂ የግብዓት አቅርቦት እና ከፍተኛ የምርት ፍላጎት መኖሩ፤ በአሁኑ ወቅት በተፋሰስ በለሙ ቦታዎች በስፋት እየተመረተ በመሆኑ እንዲሁም በቀላሉ ሊለማ የሚችልና በቂ የተዘጋጀ ቦታ መኖሩ፤   

7.3 ለማህበራዊ አገልግሎት

የወረዳው የጤና ሽፋን 87% ብቻ መሆኑ በተለይም በላቦራቶሪ እና በግል ፋርማሲ ተቋማት ሽፋን ክፍተት መኖሩን ያሳያል፤

የመዋዕለ ሕጻናት እና የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ተቋማት ብዛት ዝቅተኛ መሆኑ እንዲሁም በከፍተኛ የት/ት ተቋማት ወይም ኮሌጆች በወረዳው ውስጥ ያለመኖር ለግል ባለሀብት በመስኩ መሰማራት አመችነቱን ይጠቁማል፡፡

7.4 ለሆቴል፣ ለሪዞርት፣ ለሎጅ፣ ለመዝነኛ ፓርክ እና ቱሪዝም አገልግሎት

  • በወረዳው ዋና ከተማም ሆነ በሌሎች የማዘጋጃ ቤቶች ውስጥ ደረጃውን የጠበቀ ሆቴል፣ ፔንሲዮን እና የመዝነኛ ማዕከላት ያለመኖሩ በዘርፉ የገበያ ክፍተት መኖሩን ያሳያል፤
  • ታሪካዊ የሆኑ ዋሻዎች ለአብነት አክርሳ ዋሻ (በኮይሻ ነሬ ቀበሌ)፣ ዛምኔ ናሬ ዋሻ (ዛምኔ ናሬ ቀበሌ)፣ እንዲሁም በወረዳው ውስጥ ሌሎች ሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ የቱሪስት መስህቦች ስላሉ ቱሪስት የመሳብ አቅም ከፍተኛ ስለሆነ እንዲሁም ለዘርፉ ኢንቨስትመንት በቂ የተዘጋጀ በመሆኑ ባለሃብቱ ቢሠማራበት አዋጭ ነዉ፡፡

7.5 ለማዕድን፣ ኢነርጅ እና ለኮንስትራክሽን ዘርፍ

  • ለኮንስትራክሽን የሚያገለግሉ ጥሬ ዕቃዎች በአከባቢዉ መገኘታቸዉ፣ ነጭ ድንጋይ እና ጥቁር ድንጋይ (በሻምባ ቅለና፣ በዴንባ ዛምኔ፣ ዛምኔ ናሬ፣ አንጩቾ ጮካሬ፣ ጉሩሞ ላዲሳ፣ እና በጉኑኖ 01፣ 02፣ 03 ቀበሌዎች ውስጥ)፣ ሴሌክቲድ ማቴሪያል የመሳሰሉት በከፍተኛ መጠን መኖሩ፤

    . የኢንቨስትመንት አማራጭ ዕድሎች

8.1 ግብርና ዘርፍ

  • አትክልትና ፍራፍሬ ልማት (ማንጎ፣ አቦካዶ፣ ሙዝ)፣
  • ቅመማ ቅመም (ዝንጅብል፣ በርበሬ፣ ቃሪያ) ልማት፣+
  • የወተትና ሥጋ ከብት ማርባትና የዳልጋ ከብት ማድለብ፣
  • በዶሮ ዕርባታና እንቁላል ምርት፣
  • የእንስሳት መኖ ዘር ማባዛትና ማልማት፣
  • በንብ ማነብ፣ በበግ ማሞከት፣
  • የአገዳ ሰብሎችን ማምረት፣
  • ቡና እና ሌሎች ገበያ ተኮር ሰብሎችን ማምረት፣

8.2 በማህበራዊና በአገልግሎት ዘርፍ

  • በሆቴልና ቱሪዝም ከካፌ እስከ ባለኮከብ ሆቴል
  • ነዳጅ ማደያዎች እና ከፍተኛ ጋራዥ፣
  • ሱፐር ማርኬት /የገበያ ማዕከላት፣ ሪል ስቴት ገንብቶ ማከራየት፣
  • ላውንዴሪ አገልግሎት፣ የጅምላ ንግድ ማከፋፈያ፣
  • በትምህርት ዘርፍ ከመዋዕለ ህፃናት እስከ ኮሌጅ፤
  • በጤና ዘርፍ በክሊኒክ፣ ላቦራቶሪ፣ ፋርማሲ፣ በእንስሳት ህክምና ማዕከላት፣
  • በመዝነኛ አገልግሎት ዘርፍ፡- ሲኒማ ቤቶች፣ ፊልምና ቲያትር ቤቶች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ጂም ቤቶች እና ሌሎች
  • ለሎጅ፤ ለሪዞርትና መዝናኛ ማዕከል

8.3 በኢንዱስትሪ ዘርፍ፡- የኢንዱስትሪ ፖቴንሻል ሰርቨይ /   / ጥናት መሠረት በከተማው ውስጥ

  • የዝንጅብል እና ዕርድ ምርት ማቀነባባር፣ በቡና መፈልፈያና ማቀነባበሪያ፣
  • ለምግብና ምግብ ውጤቶች ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣
  • ለሥጋና የሥጋ ውጤቶች ማቀነባበሪያ፣ የወተትና የወተት ውጤቶች ማቀነባበሪያ፣
  • ለአትክልትና ፍራፍሬ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣
  • የእንስሳት መኖ ዘር ማባዣ፣ ማቀነባበሪያና ማሸጊያ ፋብሪካ፣