• Call Us
  • +251465512106

የዳሞት ጋሌ ወረዳ አስተዳደር

 አጠቃላይ ገጽታ      

የዳሞት ጋሌ ወረዳ ከዞኑ ርዕሰ መዲና ቦዲቲ በስተሰሜን በ18 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝና የቆዳ ስፋቱም 235.5 ካሬ ኪሜትር ሲሆን በ31 የገጠር ቀበሌዎች እና በ3 የማዘጋጃ ቤት ከተሞች የተዋቀረ ነው፡፡ በአስተዳደሩ የሚገኙ የኢንቨስትመንት አማራጮች፤ የማዕድን ሀብት ክምችትና የቱሪስት መስህቦች እንደሚከተለዉ ቀርበዋል፡፡

1.1 ከባህር ወለል ከፍታ             

ከባህር ወለል በላይ ከ1,501 እስከ 2,958 ሜትር ከፍታ ያላቸው የመሬት ገጾች አሉት፡፡

1.2 የአየር ንብረት

የወረዳው አግሮኢኮሎጂን በተመለከተ 27.8% ደጋ፤ እና  72.2% ወይና ደጋ ነዉ፡፡ የዓመቱ አማካይ የሙቀት መጠን 12.6--22.5 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ነው፡፡ አማካይ ዓመታዊ የዝናብ መጠን ከ1,001 እስከ 1,400 ሚሊ ሜትር ነው፡፡

1.3 ሥነ-ሕዝብ

በ2009 ዓ.ም ከዞኑ ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በተገኘው የስታትስቲክስ መረጃ መሠረት የወረዳው አጠቃላይ የሕዝብ ብዛት 157,612 ሲሆን የሕዝብ ጥግግት 689 በካሬ ኪ/ሜትር ነው፡፡

 

 

  . የመሠረተ ልማት አቅርቦት ሁኔታ     

2.1 መንገድ

ወረዳው ውስጥ 27 ኪ/ሜትር አስፋልት፣ 69 ኪ/ሜትር የጠጠር እና 625.55 ኪ/ሜትር ጥሪጊያ መንገዶች ሲኖሩት በአብዘኛው የወረዳው ቀበሌዎች ከዞንና ከክልል ብሎም ወረዳን ከወረዳ እንዲሁም እያንዳንዱን የገጠር ቀበሌም ጭምር በዋናና በውስጥ ለውስጥ መንገዶች እርስ በእርስ የተገናኘ ነው፡፡

2.2 ስልክ፣ ኢንተርኔት እና የፖስታ አገልግሎት

የሞባይልና የመደበኛ ስልክ አገልግሎት፣ እንዲሁም የኢንተርኔት አገልግሎት የሚሰጡ የግል ንግድ ማዕከላት እየተከፈቱ ይገኛሉ፡፡ አንድ የፖስታ አገልግሎት ሰጪ ተቋም በቦዲቲ ከተማ ይገኛል፡፡

2.3 መብራት

በወረዳው ውስጥ የሚገኙ የከተማ አከባቢዎች 24 ሰዓት የሃይደሮ ኤሌክትሪክ ኃይል መብራት አገልግሎት ያገኛሉ፡፡

2.4 የመጠጥ ውኃ አቅርቦት

የመጠጥ ውኃ አቅርቦትን በተመለከተ በእጅ ፓምፕ የሚሠራ የእጅ ጉድጓድ (                                    ) 4፣ በእጅ ፓምፕ የሚሠራ ጥልቅ ጉድጓድ (                                   ) 26፣ ጥልቅ ጉድጓድ ስርጭት (                       ) 8፣ የምንጭ ውኃ ስርጭት (                         ) 39 እና ምንጭ በቦታው ማጎልበት (           ) 56 ይገኛሉ፡፡ የወረዳው የመጠጥ ውኃ ሽፋን 71.21% ሲሆን በዘርፉ ያለውን ከፍተኛ ችግር ለማቃለል ተጨማሪ የውኃ ምንጮችን በማጎልበት የመጠጥ ውኃ ሽፋንን ከፍ ለማድረግ በተለያዩ ቀበሌዎች መስመር እየተዘረጋ ይገኛል፡፡

2.5 የገንዘብ ተቋማት፡-

የወረዳው ነዋሪዎች ዘመናዊ የባንክና ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት አገልግሎትን ከወረዳው ዋና ከተማ ቦዲቲ ውስጥ ከሚገኙ የፋይናንስ ተቋማት ያገኛሉ፡፡

   . የማህበራዊ አገልግሎት    

3.1 ጤና

  • ጤና ጣቢያ /             / ------------- 7
  • ጤና ኬላ /           / ------------------ 27
  • የመጀመሪያ ደረጃ ክሊንክ /      / --------- 4 (የግል)  
  • መድኃኒት ቤት /        / --------------- 7 (የመንግስት)
  • መድኃኒት መደብር (           ) ------ 1 (የግል)
  • ላቦራቶሪ ---------------------------------------  7 (የመንግስት)
  • የጤና ሽፋን -----------------------------------  105.8%

3.2 ትምህርት

መዋዕለ ሕጻናት ት/ቤት --------------------------- 3  

አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (1-4ኛ ክፍል) -------------- 1

አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (1-8ኛ ክፍል) -------------- 34

ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት (9-10ኛ ክፍል) ------------ 3

መሰናዶ (11-12ኛ ክፍል) --------------------------- 1

  . በመስኖ የሚለማ የእርሻ መሬት ሁኔታ                       

በወረዳው ውስጥ 1 የመስኖ ፕሮጀክት ተግባራዊ በመሆኑ የአከባቢው አርሶ አደር ተጠቃሚ ሲሆን ለአብነት ዳምጤ መስኖ (80 ሄ/ር) አገልግሎት እየሰጠ በመሆኑ ለአከባቢው ማህበረሰብ ምርትና ምርታማነት ከማሳደግ አንጻር አዎንታዊ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛል፡፡ ወረዳው ካለው የከርሰ ምድርና የገጸ ምድር ውኃ አቅርቦት ለአብነት ወንዞች (ጫራቄ፣ የቼ፣ ቡሻ፣ ኢጣና እና ወላጫ ወንዞች) ከመኖሩ አንጻር እስካሁን በመስኖ የለማው መሬት መጠን በጣም ዝቅተኛ ከመሆኑም ባሻገር ወረዳው ከፍተኛ ለመስኖ አገልግሎት ሊውል የሚችል የውኃ ፖቴንሻል እንዳለ፣ ከፍተኛ የዝናብ መጠን መኖሩ እና ለም ዐፈር መኖሩ ለእርሻ ኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡

 . በወረዳው የሚመረቱ ዋና ዋና ምርቶች    

5.1 ዓመታዊ ሰብሎች

በቆሎ፣ ጤፍ፣ ማሽላ፣ ስንዴ፣ ቦሎቄ፣ ገብስ፣ አኩሪ አተር፣ ሽንብራ፣ አተር፣ ባቄላ፣ የሥራ ሥር ሰብሎች (ድቡልቡል ድንች፣ ስኳር ድንች፣ ጎዳሬ)፣ አትክልት (ቀይ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርት፣ቲማትም)፣ ቅመማ ቅመም ምርት (በርበሬ)፣ ሸንኮራ አገዳ፣

5.2 ቋሚ ሰብሎች

ፍራፍሬ (ሙዝ፣ ማንጎ፣ አቮካዶ)፣ እንሰት፣ ቡና፣

  . ለኢንቨስትመንት የተዘጋጀ መሬት   

ወረዳው በዞናችን ውስጥ ካሉ ወረዳዎች በህዝብ ጥግግት ከፍተኛ ከሆኑት ውስጥ አንዱ በመሆኑ አርሶ አደሩ ገበያ ተኮር የሆኑ ምርቶች ምርታማነትን በማሳደግና በተፋሰስ የለሙ ቦታዎችን በአግባቡ ለአትክልትና ፍራፍሬ፣ ለንብ ማነብ፣ ለበግ ማሞከት፣ ለእንስሳት ዕርባታና ድለባ፣ እንዲሁም ለኢንዱስትሪ ግብዓት የሚሆኑ ምርቶችን በበቂ ሁኔታ ለማቅረብ ያሉትን ምቹ ሁኔታዎችን መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን ለእንስሳት ዕርባታ፣ ለበግ ማሞከት፣ ለዶሮ ዕርባታ፣ ሌሎች ሰፊ መሬትን የማይጠይቁ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ላይ የግል ባለሀብት እንዲሳተፍ ለማድረግ በአብዘኛው የወረዳው ቀበሌዎች ክስ ቦታዎች ያሉ ቢሆንም ከግልጸኝነት መጓደል የተነሳ የተደራጀ መረጃ ለማቅረብ አልተቻለም፡፡

   . ለኢንቨስትመንት ያለው አመቺነት

7.1 ለግብርና          

  • በወረዳው ውስጥ ዓመቱን ሙሉ የማይደርቁ ወንዞች በመኖራቸው እንዲሁም በተፋሰስ የለሙና የተካለሉ ሰፊ ቦታዎች ያሉት በመሆኑ በንብ ማነብ፣ በበሬ ድለባ፣ በበግ ማሞከት፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት፣ በዘመናዊ እንሰሳት ዕርባታ፣ ለዶሮ ዕርባታ ለማካሄድ ምቹ መሆኗ፣
  • በልማት ሥራ ላይ ለማዋል በቂ የሰው ኃይል /የተማረ እና የጉልበት/ መኖሩ፣
  • በለሙ ተፋሰሶች እና በአርሶ አደር ማሳ የተሻሻለ መኖ፣ ምጥን መኖ፣ የተለያዩ የሰብል ተረፈ ምርቶች፣ የተፈጥሮ ግጦሽ መኖ አቅርቦት መኖሩ፤
  • ዓመታዊ አማካይ የዝናብ መጠን ከፍተኛ መሆኑ፣
  • የተሻሻለ የእንስሳት ዝሪያ እየተስፋፋ መሆኑ (በሰው ሰራሽ ዘዴ በማዳቀል)፤
  • ከፍተኛ የሀገረሰብና የተሻሻለ የበግ እና የዶሮ አቅርቦት መኖሩ፤
  • ከፍተኛ የወተት ምርት፣ የወተት እና ተዋጽኦ ምርት ፍላጎት እንዲሁም የመስሪያ ቦታና የመሠረተ ልማት አቅርቦት መኖሩ ለኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ የተመቻቹ ሁኔታዎች ናቸው፡፡

7.2 ለአግሮ ኢንዱስትሪ

  • ከአርሶ አደሩ የሚገኙትን የግብርና ምርቶችን (በአውትግራውር ከአርሶ አደሩ ጋር ትስስር በመፍጠር) በጥሬ ዕቃነት ተጠቅሞ በማቀነባበር እስከ ውጪ ገበያ ድረስ ለሚያቀርቡ ባለሀብቶች መሬቱ አመቺነት ያለው በመሆኑ ያለውጣውርድ ማግኘት ይቻላል፤
  • ለተለያዩ ፋብሪካዎች በጥሬ ዕቃነት ሊያገለግሉ የሚችሉ የግብርና ምርቶች የሆኑ እንደ አቮካዶ፣ ቡና፣ ማንጎ፣ ድቡልቡል ድንች፣ ስኳር ድንች፣ ሙዝ፣ ቦሎቄ እና እንስሳት ሀብት በቅርብ መገኘታቸዉ፤
  • የወተት እና የወተት ተዋጽኦ ለማቀነባበር ከፍተኛ የወተት ምርት መኖሩ፣
  • የሥጋ ምርት (የዳልጋ ከብት፣ የዶሮ፣ ወዘተ) ለማቀነባበር የተሻሻሉ ዝሪያ፣ የተዳቀሉ እና የሀገረሰብ ዘር አቅርቦት መኖሩ፣
  • ምጥን የከብቶች መኖ ለማዘጋጀት በቂ የግብዓት አቅርቦት እና ከፍተኛ የምርት ፍላጎት መኖሩ፤ በአሁኑ ወቅት በተፋሰስ በለሙ ቦታዎች በስፋት እየተመረተ በመሆኑ እንዲሁም በቀላሉ ሊለማ የሚችልና በቂ የተዘጋጀ ቦታ መኖሩ፤   

7.3 ለማህበራዊ አገልግሎት

የወረዳው የጤና ሽፋን 105.8% የደረሰ ቢሆንም በላቦራቶሪ እና በግል ፋርማሲ ተቋማት ሽፋን ክፍተት መኖሩን ያሳያል፤

የመዋዕለ ሕጻናት እና የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ተቋማት ብዛት ዝቅተኛ መሆኑ እንዲሁም በከፍተኛ የት/ት ተቋማት ወይም ኮሌጆች በወረዳው ውስጥ ያለመኖር ለግል ባለሀብት በመስኩ መሰማራት አመችነቱን ይጠቁማል፡፡

7.4 ለሆቴል፣ ለሪዞርት፣ ለሎጅ፣ ለመዝነኛ ፓርክ እና ቱሪዝም አገልግሎት

  • በወረዳው ዋና ከተማም ሆነ በሌሎች አከባቢዎች ደረጃውን የጠበቀ ሆቴል፣ ፔንሲዮን እና የመዝነኛ ማዕከላት ያለመኖሩ በዘርፉ የገበያ ክፍተት መኖሩን ያሳያል፤
  • የቁም ትክል ድንጋይ፣ ታሪካዊ የሆኑ ዋሻዎች ለአብነት የንጉስ አማዶ ዋሻ፣ እንዲሁም በወረዳው ውስጥ ሌሎች ሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ የቱሪስት መስህቦች ስላሉ ቱሪስት የመሳብ አቅም ከፍተኛ ስለሆነ እንዲሁም ለዘርፉ ኢንቨስትመንት በቂ የተዘጋጀ በመሆኑ ባለሃብቱ ቢሠማራበት አዋጭ ነዉ፡፡

7.5 ለማዕድን፣ ኢነርጅ እና ለኮንስትራክሽን ዘርፍ

  • ለኮንስትራክሽን የሚያገለግሉ ጥሬ ዕቃዎች በአከባቢዉ መገኘታቸዉ፣ ነጭ ድንጋይ እና ጥቁር ድንጋይ (በሀርቶ ቆንጦላ፣ በሀርቶ ቡርቃቶ ቀበሌ እና በሌሎች ቀበሌዎች)፣ ሴሌክቲድ ማቴሪያል የመሳሰሉት በከፍተኛ መጠን መኖሩ፤

    . የኢንቨስትመንት አማራጭ ዕድሎች

8.1 በግብርና ዘር

  • አትክልትና ፍራፍሬ ልማት (ማንጎ፣ አቦካዶ፣ ሙዝ)፣
  • ቅመማ ቅመም (በርበሬ፣ ቃሪያ) ልማት፣
  • የወተትና ሥጋ ከብት ማርባትና የዳልጋ ከብት ማድለብ፣
  • የእንስሳት መኖ ዘር ማባዛትና ማልማት፣
  • በግ ማርባትና ማሞከት፣
  • በዶሮ ዕርባታና እንቁላል ምርት፣
  • የአገዳ ሰብሎችን ማምረት፣
  • ቡና እና ሌሎች ገበያ ተኮር ሰብሎችን ማምረት፣

 

 

8.2 በማህበራዊና በአገልግሎት ዘርፍ

  • በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ከካፌ እስከ ባለኮከብ ሆቴል
  • በትምህርት ዘርፍ ከመዋዕለ ህፃናት እስከ ኮሌጅ፤
  • በጤና ዘርፍ በክሊኒክ፣ ላቦራቶሪ፣ ፋርማሲ፣ በእንስሳት ህክምና ማዕከላት፣
  • በመዝነኛ አገልግሎት ዘርፍ፡- ሲኒማ ቤቶች፣ ፊልምና ቲያትር ቤቶች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ጂም ቤቶች እና ሌሎች

8.3 በኢንዱስትሪ ዘርፍ

 የኢንዱስትሪ ፖቴንሻል ሰርቨይ /   / ጥናት መሠረት በከተማው ውስጥ፡-

  • ለአትክልትና ፍራፍሬ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣
  • የእንስሳት መኖ ዘር ማባዣ፣ ማቀነባበሪያና ማሸጊያ ፋብሪካ፣
  • በቡና መፈልፈያና ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣
  • ድቡልቡል ድንች ማቀነባበር፣
  • ለምግብና ምግብ ውጤቶች ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣
  • ለሥጋና የሥጋ ውጤቶች ማቀነባበሪያ፣
  • የወተትና የወተት ውጤቶች ማቀነባበሪያ፣
  • የቤትና ቢሮ ዕቃ ማምረቻ፣