ሀሩሮና ዋሻ
ይህ ታሪካዊ ዋሻ በወላይታ ዞን ዉስጥ ከሚገኙ ታዋቅ ዋሻዎች አንዱ ሲሆን የሚገኘዉም በኦፋ ወረዳ በጢዳ ቀበሌ ገ/ማህበር በወዮ ወንዝ አጠገብ ዉስጥ ከወረዳው ዋና ከተማ ከገሱባ ከተማ በ18 ኪ.ሜ ላይ ይገኛል፡፡
ዋሻውን ለመጎብኘት የሚሄድ ሰው ወዮን ወነዝ ከተሸገረ በኃላ ወደ ቀበሌ ከሚወስደው የበጋ መኪና መንገድ ወደ ደቡብ አቅጣጫ 2.5 ኪ.ሜ ከዎዮ ወንዝ በስተቀኝ በኩል ነው፡፡
የዋሻው ውጫዊ ገጽታ ሲንመለከት እንደቆርቆሮ ቤት ከዝናብና ከፀሐይ የሚከላከል በረንዳ ያለው ሆኖ ወደ ውስጥ ሲገባ እንደሳሎን ሰፊ ክፍል በ2 መስኮቶች ጋር ነው ያለው፡፡
ወደ ጓዳ ለመግባት በጠባብ በር በእንብርክክ ወደ 2 ሜትር ያህል ካስገባ በኋላ የሕዝብ አደራሽ የሚያህል ትልቅና ሰፊ ክፍል አለ፡፡
የአከባቢ ሽማግሌዎች ሲናገሩ ውስጥ ለውስጥ 3 ኪ.ሜትር ወደ ቀበሌ ጉተራ የሚያስወጣ መንገድ አለ ይላሉ፡፡
የጣሊያን የአርክዮሎጅስቶችና ጆሎጅስቶች ጥናት እንደሚስረዳው የወላይታ ጠናታዊ ሥልጣኔ ገላጭ የሆኑ ከ60 ሺህ ዓመት በፈት በዋሻ ውስጥ ይኖር የነበሩ ሰዎች የተጠቀሙበት ከድንጋይና ባልጩት የተሰሩ መዶሻዎችና የማምረቻ መሳሪዎች እንዲሁም የአጥንት ቅሪት አካላትና አለት ያነደዱበት ከስዕልና ሌሎች መረጃዎች ተገኝቷል፡፡
በዋሻው በረንዳ በርካታ ጥንታዊ የዋሻ ስዕሎችና ቅርፃቅርፆች ያሉበት ሆኖ የበረንዳው መግቢያ በር፣መስከቶች፣ ሰፊ ሳሎንና ጓዳ ያለው ሲሆን ሳሎኑ እስከ 500 ሰው መስተናገድ እንደሚችል ተጠንቷል፡፡
ይህ ዋሻ በዞናችን በረካታ የቅድሜ ታርክና የታርክ ዘመን ቅርሶች የሚገኙበት ታሪካዊ ዋሻ(ታሪካዊ የቱሪስት መስህብ) ስለሆነ ዋሻውን በማልማትና በማከባከብ ቅርሶችን ባሉበት ጠብቆ ከትውልድ ወደ ትውልድ በማስተላለፍ ከቱሪዝም ዘርፍ የሚገኘውን ገቢ ማሳደግ የግድ ይለናል፡፡
ሳአ ቱሳ እና ጮፎሾ ዋሻ
እነዝህ የተፈጥሮ ቱሪስት መስህቦች የሚገኙት በኦፋ ወረዳ በኮዶ ቀበሌ በጮፎሾ ቀጠና( መንደር) ከወረዳው ዋና ከተማ ገሱባ በ2.5 ኪ.ሜትር ይገኛሉ፡፡ የመስህቡን ታሪካዊነት በተመለከተ እግዘር ምድርን ከዘረጋበት ጊዜ ጀምሮ ያለ መስህቦች ናቸው ብለው ይናገራሉ የአከባቢ ታርክ አዋቂዎች፡፡
ሳአ ቱሳ በቁጥር 2 ሲሆኑ ሪዝመቱ ከመሬት ወደ ላይ 50 ሜትር ከፍታ ያለው ሆኖ በአጠገቡ የሚገኘው ዋሻ ጋር ለሚያይና ለሚጎብኝ ሰው እጀግ የሚግምና የሚያስደንቅ የእግ/ር ሥራ ነው በማለት ይደነቃል፡፡
እነዝህን የቱሪስት መስህቦች የሚጎብኝ ቱሪስት የእግዘር ሥራ በማየት እጅግ በመደነቅና በመዝናናት አእምሩዋቸውን አስደስቶ ይመለሳሉ፡፡
Mochena Borago Cave
Mochena Borago Cave is a very amazing cave that is found in wolaita zone sodo zuria woreda at the foot of mount Damota. It is located at a distance of 12 k.m away from sodo town via Hossana-Adiss Ababa to the right side from the main road.
The cave located at 2340 meter above sea level. The cave has 33 meters high roof and is 50 meters width. The wall of the cave naturally built with hard rocks around the cave Rock Wajja falling down from the top of the cave gives whitish color to the natural scenic view of green attraction. Currently the site is becoming interesting site for American, French and German archeologists.
The recent archeological excavation revealed that man lived in the cave before 58,000 to 70,000 years.
Copyrights 2019. . All Rights Reserved.
Developed by SNNPRS-SITB & SNNPRS-wza