• Call Us
  • +251465512106

የወላይታ ዞን አስተዳደር

በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/ት የወላይታ ዞን አስተዳደር

የወላይታ ዞን ገጽታ

ወላይታ ዞን በክልሉ ካሉ 14 ዞኖች አንዷ ትሆን ጂኦግራፊካል አቀማመጡ 6.51-7.35 ዲግሪ ሰሜን ላትቲውድ እና 37.23-38.14 ዲግሪ ምስራቃዊ ሎንግትዩድ መስመር ትገኛለች፡፡ ዞኑን ጋሞ ጎፋ ዞን በስተደቡብ፣ ዳውሮ ዞን በስተምዕራብ፤ ካምባታ ጣምባሮ ዞንና ሀዲያ ዞን ምዕራብ ባዳዋቾ ወረዳ በሰሜን፤ ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በስተሰሜናዊ ምስራቅ እና ሲዳማ ዞን በስተምስራቅ ያዋስናሉ፡፡ 

ዞኑ 16 የገጠር ወረዳዎች፤ 6 የከተማ አስተዳደር መዋቅሮች እና 372 ገጠርና ከተማ ቀበሌያት የተከፋፈለ ነው፡፡ ከዚህም 293 የገጠር እና 79 የከተማ ቀበሌያት ይገኙባታል፡፡ በዞኑ 6,664 የአ/አደር አደረጃጀት ልማት ቡድን፤ 42,322 የ1ለ5 አደረጃጀትና 349,224 አባላት፤ 9,558 የሴቶች አደረጃጀት ልማት ቡድን፤ 45,070 1ለ5 አደረጃጀትና 178,116 አባላት እና 2,199 የወጣቶች አደረጃጀት ልማት ቡድን፤ 12,379 1ለ5 አደረጃጀትና 185,687 አባላት መኖሩን መረጃ ይጠቁማል፡፡

የዞኑ ቆዳ ስፋት 451,170.7 ሄ/ር ወይም 4,511.7 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ነው፡፡ የዞኑ የመሬት አጠቃቀም ስልት በአብዛኛው ጥምር እርሻን የተከተለ የአስተራረስ ዘይቤ አለው፡፡ በአብዛኛው የእርሻ መሬት በዓመታዊና በቋሚ ሰብሎች የተያዘ ነው፡፡

የዞኑ የአየር ሁኔታ

ዞኑ የተለያየ የአየር ሁኔታ አለው፡፡ ከጠቅላላ ዞኑ ቆዳ ስፋት 157,909.5 (35%) ቆላ፣ 252,655.2 ሄ/ር (56%) ወይና ደጋ እና 40,605.3 ሄ/ር (9%) ደጋ የአየር ንብረት አለው፡፡ከዚህ የተነሳ የተለያዩ ሰብሎችን ለማምረት የተመቸ የአየር ጠባይ አለው፡፡ ዞኑ ከባህር ጠለል ያለው ከፍታ በዝቅተኛ 501 ሜትር በቢላቴ ጤና እና ከፍተኛ 2,958 ሜትር ዳሞታ ተራራ መሆኑን ነው፡፡ የዞኑ አማካይ ዓመታዊ የሙቀት መጠን 15.2-31.4 ዲግሪ ግሬድ ነው፡፡ ዓመታዊ የዝናብ መጠን በአማካይ ከ8ዐዐ-1,6ዐዐ ሚሜ ነው (ምንጭ፡ የክልሉ ፋይ/ኢ/ል/ቢሮ 2009 ዓ/ም ዓመታዊ አብስትራክት መረጃ መነሻ የወላይታ ዞን ፋይ/ኢ/ል/መምሪያ 2009 ዓ/ም ዓመታዊ አብስትራክት ዕትም)፡፡

በዞኑ አብዛኛው ሰብል ለማምረት የሚሆነው የዝናብ ውሃ ነው፡፡ ይሁንና ለመስኖ ምቹ የሆነ መሬት ያለው በመሆኑና ቋሚ ወንዞች ክረምት እስከ በጋ የማይደርቁ በመኖራቸው የዞኑ አ/አደር በባህላዊ እና በዘመናዊ ወንዞችን፤ ኩሬዎችን፤ የቤተሰብ ገንዳ እና የተለያዩ አነስተኛ/ ጥቃቅን የመስኖ አካላትን በመጠቀም እርሻውን ያለማል፡፡ በዞኑ የሚመረቱ ዋና ዋና ሰብሎችን በተመለከተ ቦቆሎ፤ ማሽላ፤ ጤፍ፤ ስንዴ፤ ገብስ፤ ቦሎቄ፤ አተር፤ ባቄላ፤ ጎደሬ፤ ስኳር ድንች፤ ድቡልቡል ድንች፤ ካሳቫ፤ እንሰት፤ አካዶ፤ ማንጎ፤ ሙዝ፤ ፓፓያ፤ ብርቱካን፤ አበሻ ጎመን፤ ቀይስር፤ ቲማቲም፤ ካሮት፤ ሽንኩርት፤ ቡና፤ ዝንጅብል በርበሬ እና ሌሎች ሰብሎችም ይመረታሉ፡፡

ራዕይ

በዞኑ ሰላምና ፀጥታ ተረጋግጦ እና መልካም አስተዳደር ሰፍኖ ዘላቂ ልማት በማምጣት ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ሆኖ ማየት፣፣

ተልዕኮ

 በዞኑ ያሉትን ሰብአዊና ተፈጥሮአዊ ሃብቶች አቀናጅቶ በመምራት፣ቀጣይነት ባለው መልኩ በስፋት ጥቅም ላይ በማዋልና የብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ህዝቦችን አንድነት በማጠናከር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትን በማፋጠን እና መልካም አስተዳደርና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ እንዲጎለብት ማድረግ

ዕሴቶች

ተገልጋይ ተኮርነት መለየችን ነው፡፡

መቻቻል ባህላችን ነው

ተሳትፎአዊነትና ሚዛናዊነት መመሪያችን ነው፡፡

የህግ የበላይነት መርሆአችን ነው፡፡

ልዩነታችን ውበታችን፣ውበታችን አንድነታችን ነው፡፡

ዓላማ

በክልሉ ሕገ-መንግስት ለዞን ዋና አስተዳዳሪና ለመስተዳደር ም/ቤቱ የተሰጣቸውን ስልጣንና ተግባር በአግባቡ እንዲፈፅሙ ተገቢውን ቴክኒካዊ ድጋፍ በመስጠት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት ማስመዝገብና መልካም አስተዳደር እንዲስፍን ማስቻል ነው፡፡

Testimonial

Wolaita Zone Administration