• Call Us
  • +251465512106

ፏፏቴዎች

አጆራ መንትያ ፏፏቴ     Ajora twins

በዞናችን አገልግሎት እየሰጡ ካሉ ባህላዊ፣ታሪካዊና ተፈጥሯዊ የቱሪስት መስህቦች መካከል አንደኛ ሲሆን በወላይታ ዞን በቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ አጆራ ቀበሌ የሚገኝ የተፈጥሯዊ መስህብ ነው፡፡ ይህ ተፈጥሮ መስህብ ውብና ማራኪ የሆነ የሰውን ልጅ ከሚያማልለ ከተፈጥሮ ፀጋዎች ተርታ የሚጠሩ ለአገር ውስጥም ሆነ ለውጪ አገር ቱሪስቶች ቀልብ የሚስብ ለጎብኚዎች በሚመች መልኩ ከአዲስ አበባ በሆሳዕና መንገድ 320 ኪ.ሜ ከአዲስ አበባ በሻሸመኔ መንገድ 435 ኪ.ሜ ከክልሉ ከተማ ሀዋሳ በ212 ኪ.ሜ፣ከዞናችን ርዕሰ ከተማ ሶዶ በ56 ኪ.ሜ፣ከወረዳው ከተማ ቦምቤ በ5 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡

አጆራ ፏፏቴ ሶኬ እና አጃንቾ ከሚባሉ ትላልቅ ወንዞች የሚፈጠሩ መንትያ ፏፏቴዎች ናቸው፡፡  የወንዞቹ መነሻ አጃንቾ በአጠቃላይ በወላይታ በኩል ሲሆን ሶኬ በወላይታና ካንባታ ድንበር መሃል ነው፡፡ ስያሜያቸውን ያገኙት ፏፏቴዎቹ ከሚወርዱበት ትልቅ ገደል ውስጥ ለረዥም ጊዜ ሲኖሩ ከነበረው አጆራ ከሚባለው ጎሣዎች ስያሜ ነው፡፡

ሁለቱ ፏፏቴዎች 400 ሜትር ተራርቀው ገደል እየተምዘገዘጉ የሚወርዱ አጃንቾ 210 ሜትር ወደ ትልቁ ገደል ጢሰ መስሎ ሲወርድ በተመሳሳይ ሶከ 170 ሜትር ቀልቁል የሚወረወር ድንቅ የተፈጥሮ ስጦታዎች ናቸው፡፡

ከፏፏቴዎቹ በተጨማሪ ሌሎች በርካታ የዱር እንስሳትም መኖርያ ነው፡፡በተላይም ጉሬዛ፣ድኩላ፣ከርከሮ፣ዝንጆሮ፣ነብር፣አጋዘን፣ጦጣ እና የተፈጥሮ የዕፅዋት ዝሪያዎች በአከባቢው የተለያየ ስያሜ የሚሰጣቸው ከመኖራቸውም አልፎ በምግብነት የሚጠቀም ቦይና/ጎዳሬ የሚባለውና ሌሎች ሥራ ሥር  ተክል በብዛት ይገኛሉ፡፡

ስለዚህ ይህንን ተፈጥሯዊ የቱሪስት መስህብ ልዩ የሚያደርገው፡-

  • ፏፏቴው በሚገርም ሁኔታ የተለያዩ ወንዞች መንትያ ሆነው መውረድ
  • ፏፏቴዎች በ400 ሜትር ተራሪቀው ጎን ለጎን መፈሰሳቸው
  • ፏፏቴው ብቻ አይደለም አከባቢው በተለያዩ የዱር እንስሳትና የዕፅዋት ዝሪያዎች በመኖሩ የቱሪስቶችን ልብ መሳብ የሚችሉ መሆኑ፡፡

አጃንቾ ፏፏቴ

አጃንቾ ፏፏቴ

አጃንቾ ፏፏቴ የሚገኘው በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ አቹራ ቀበሌ ከአጃንቾ ወንዝ የሚፈጠረ ልዩና ተፈጥሯዊ የነሆነ ፏፏቴ ነው፡፡ፏፏቴው ከወረዳ ዋና ከተማ አረካ በ13 ኪ.ሚ ርቀት ላይ የሚገኝ ከቀበሌ ማዘጋጃ ቤት በ1 ኪ.ሜ ርቀት የሚገኝ እጅግ ውብና ለማየትም ሆነ ለመዝናናት ምቹ የሆነ ፏፏቴ ነው፡፡ እስኬ ፏፏቴው ድረስ ጎብኚዎች ሄደው እንዲጎብኙ በህብረተሰብ ተሳትፎ የጥሪጊያ መንገድ የተስተካከለና ለቀጣይ በዞናችን ትልቅ የቱሪስት መስህብ ስፍራ የሚሆን ፏፏቴ ነው፡፡የፏፏቴው የውሃ ምንጭ አጃንቾ ወንዝ ሲሆን ይዘቱ በበጋ በመጠነኛ መጠን ያለው ሆኖ በክርምት ከፍተኛ ውሃ ይዘት ባሻገር የውሃው አወራረድ አግራሞትን የሚጭር ነው፡፡

የፏፏቴው ውጫዊም ሆነ ውስጣዊ ክፍል የሚኖሩ የተለያዩ የዕፅዋት ዓይነቶች፣የዱር እንስሳትና የአእዋፍ ዝሪያዎች የቱሪስቶችን ቀልብ የሚስቡ ናቸው፡፡

ይህም ብቻ አይደልም በፏፏቴው አከባቢ በአከባቢ ህብረተሰብ የተተከሉ ችግኞች ለፏፏቴው ውበትን ያጎናፅፋል፡፡

ፏፏቴው በዙሪያውና በአከባቢው በድንቅ እይታ ውስጥ ያሉ ገደልና አነስተኛ ኮረብታ የከበበው ሆነው የፏፏቴው ርዝመት 50 ሜትር ወደ ቁልቁል ጢስ መስሎ ይወርዳል፡፡

ፏፏቴው ላይ የመሰረተ ልማት ሥራዎችና ሌሎች የቱሪስቶች ማረፊያ ሎጅ ብሰራ ለውጪ ሀገርና ለአገር ውስጥ ቱሪስቶች የሚሆን ተፈጥሯዊ የሆነ የቱሪስት መስህብ ቦታ ነው፡፡

ወይቦ ፏፏቴ 

ወይቦ ፏፏቴ

ይህ ፏፏቴ የሚገኘው በወላይታ ዞን ውስጥ ከሚገኙ 3 ሪፖርም ከተማ አስተዳደሮች አንዱ በሆነው አረካ ከተማ ወሩሙማ ቀበሌ ከከተማው 3 ኪ.ሜ ሪቀት ላይ የሚገኝ ተፈጥሯዊ ፏፏቴ ነው፡፡

የፏፏቴው የውሃ ምንጭ ወይቦ ወንዝ ሲሆን የፏፏቴው ርዝመት 30 ሜትር ይሆናል፡፡ የፏፏቴው ውስጣዊ ገፅታ በተለያዩ የዕፅዋት ዓይነቶች የተሞላና የተለያዩ የዱር እንስሳት ሚገኙበት በዞናችን ልዩ የቱሪስት መስህብ ነው፡፡

 

የፏፏቴው ውጫዊ ክፍል በተመለከተ ከግለሰብ ይዞታ ጋር ተያይዞ ያለው ቢሆንም ለቱሪስቶች በቂ አገልግሎት እንዲሰጥ መንግስት ለቦታው ትኩረት ሰጥቶ ብያለማው ምቹ የቱሪስቶች መዝነኛ ስፍራ ይሆናል፡፡

 

የፏፏቴው መንገድ ሁኔታ ከወላይታ ሶዶ ሆሳዕና የሚወስደው መንገድ አጠገብ የሚገኝና ዞኑ የማልማት ሥራ ብሰራበት በቂ የማስተዋወቅ ሥራ ብሰራ ለውጪ ሀገር ቱሪስቶችና ለሀገር ውስጥ ቱሪስቶች መዝነኛ ስፍራ ይሆናል፡፡

ሲኒያ ፏፏቴሲኒያ ፏፏቴ

 በወላይታ ዞን በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ በማጣላ ሄምበቾ እና በሹዬ ሆምባ ቀበሌ መሀል የሚገኝ ሲኒያ ፏፏቴ ስሆን መስህቡ ከወረዳው ዋና ከተማ ከአረካ በ14 ኪ/ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ መስህብ ነው፡፡

መስህቡ በሁለት ቦታ ተሰንጥቆ መንቲያ ፏፏቴ ፈንሮ ተመዘግዝጎ ከመውረዱ ባሻገር ውሃው ከላይ እስከ ታች የምወርደው ርቀት

በግምት 40 ሜትር  ያክል ይሆናል፡፡

ፏፏቴው የተፈትሮ መስህብ ስሆን የመስህቡ ገፅጻ መንፈስን የሚያረካ እና ነፋሻማ አየር ከመኖሩ የተነሳ በመስህቡ አከባቢ የተለያዩ የዱር እንስሳቶች ይገኙበታል

ለምሳሌ፡-ጅብ፣ጦጣ፣ዝንጀሮ፣ዲቪ፣ነብር፣ወዘተ……..ከ10 ባለይ የተለያዩ የዱር እንስሳት ይገኙበታል፡፡

መስህቡ ያለበት ቦታ በሄክታር ስለካ  53.123 ሄክታር መረት ላይ ይገኛል

መስህቡ ስያመን በተመለከተ ሲኒያ ፏፏቴ የተባለበት ምክንያት በመስህቡ አከባቢ ሲኒያ መዳ ተብሎ የምጠራ መዳ ስላለ መስህቡ ሲኒያ ፏፏቴ ተብሎ ይጠራል፡፡

የመስህቡ ዙርያ በተፈጥር ድንጋይ ከመገንባቱ የተነሳ ከላይ ወደታች የተመዘገዘገ የምወርደው ውሃ   ለመስህቡን የበለጠ ውበት እንድኖረው ያደርጋል፡፡

ሳንጋና ፏፏቴ

ሳንጋና ፏፏቴበቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ቦምቤ /ማህበር ቀበሌ ከአዲስ አበባ ሻሸመኔ መንገድ በኩል 448 .ሜትር ርቀትና አዲስ አበባ ሆሳዕና መንገድ 328 .ሜትር ርቀት ይገኛል፡፡

ከሀዋሳ 228 .ሜትር ከዞኑ ዋና ከተማ ሶዶ 58 .ሜትር ከወረዳው ዋና ከተማ ቦምቤ 7 .ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ተፈጥሯዊ መስህብ ነው፡፡

ይህ ፏፏቴ ከአጆራ ቀጥሎ 2 ደረጃ የሚገኝ ሲሆንከፊትና ከኃላ ሆኖ እየተመዘገዘገ በሳንጋና ገደል ሲወርድ የሚያስደንቅ ነው፡፡

ፏፏቴውን ልዩ የሚያደረገው በግምት 150 ሜትር ያህል ጥልቀት ከወረደ በኃላ ወደፊት 40 ሜትር ያህል ጥልቀት ገደል መውረድ ብቻ ሳይሆን ከፊት ለፊት እና ከጎን የሚታዩ ውበት ያላቸው የተፈጥሮ ኮርብታዎች በኦሞ ሸለቆ ውስጥ የተፈጠረው የጊል ጊል ጊቤ-3 ሰው ሰራሽ ሐይቅ በፏፏቴው አጠገብ ቆሞ ማየት ለአእምሮ የመንፈስ እርካታ ይሰጣል፡፡

 ከዚህም በላይ መስህቡ ገደል ውስጥ በረዥሙ ቁመት ጭስ መስሎ ሲወርድ ማየት ብቻ ሳይሆን ወደ ፏፏቴው እየተጠጉ ሲሄድ የሚያማምሩ አእዋፍት፣የዱር እንስሳት፣ጥቅጥቅ ያሉ ደኖችን ማየት አእምሮ በማደስ ደስታን ይፈጥራል፡፡

ስለዚህ ይህን ተፈጥሯአዊ መስህብ ሄደው እንዲያዩ እንጋብዞታለን፡፡